Connect with us

ከየትኛውም ድርድር በፊት ልክ እንደ እነ ስብሃት ነጋ ቀሪዎቹም የሕወሓት የጦር ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!

ከየትኛውም ድርድር በፊት ልክ እንደ እነ ስብሃት ነጋ ቀሪዎቹም የሕወሓት የጦር ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!
ሕወሓት

ነፃ ሃሳብ

ከየትኛውም ድርድር በፊት ልክ እንደ እነ ስብሃት ነጋ ቀሪዎቹም የሕወሓት የጦር ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!

ከየትኛውም ድርድር በፊት ልክ እንደ እነ ስብሃት ነጋ ቀሪዎቹም የሕወሓት የጦር ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!

(ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ)

  ጦርነቱን በተመለከተ እንደ ሕወሓት አመራሮች መረጃ ያቀበለን የለም…ለዚያውም በድምፅና በምስል የተደገፈ ማስረጃ! ለምሣሌ ጦርነቱን የጀመሩት ራሳቸው እንደሆኑ በወቅቱ ቃል አቀባያቸው ሴኮ ቱሬ ሳንጠይቃቸው ይፋ አደረጉልን። በመቀጠልም ጦርነቱን በበላይነት ቢያጠናቅቁ ኖሮ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ገና ከደሴ ሆነው በፃዲቃን፣ በደብረፂዮን እና በጌታቸው ረዳ በምስልና በድምፅ በተደገፈ ማስረጃ ይፋ አደረጉልን። ሕወሓት አዲስአበባን ተቆጣጥራ ጦርነቱን በበላይነት ብታጠናቅቅ ኖሮ፦

  1. ድርድር የሚባል ነገር ፈፅሞ እንደማትቀበል
  2. የብልፅግናን አመራሮችን ማለትም ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድን፣ ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤን፣ ጨምሮ ሌሎችንም ወደ ሕግ እንደምታቀርባቸው በጌታቸው ረዳ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል። እንዲያውም አዲስአበባ እንደገቡ ዘብጢያ የሚያወርዱትን ወደ 300 የብልፅግና ሰዎች ስም ዝርዝር ሁሉ በሚዲያ አሳውቃ ነበር።

 ነገሩ ሁሉ ተገልብጦ ሕወሓት ሸሽታ መቀሌ ከገባች በኋላ ተሸንፋም ራሷን እንደ አሸናፊ በመቁጠር የድርድር መስፈርቶችን እያስቀመጠች ነው። የኃይል ሚዛኑ ወደ ሕወሓት ያጋደለ በመሰለው ጊዜ ፃዲቃን እጃችን በገባው የምስልና የድምፅ ማስረጃ ምን ነበር ያለው?

“ጦርነቱ አልቋል ፤ ከማን ጋር ነው የምንደረደረው? ቀጣዩ ጉዞአችን የሽግግር መንግስት አቋቁመን ሪፍረንደም ማካሄድ ነው” ነበር ያለው።

  እነርሱ የሚያሸንፉ ሲመስላቸው “ከማን ጋር ነው የምንደራደረው?” ይላሉ፤ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ክንድን    ቀምሰው ወደ መቀሌ መፈርጠጥ ሲጀምሩ “እንደራደር” የሚለው ቁማር ምናልባት የትግራይንና በሩቅ ያለውን ዓለም አቀፍ ማህበረሰብን ለማታለልና ለማጭበርበር ይጠቅማቸው ይሆናል እንጂ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፈፅሞ መሸወድ አይችሉም።

  ለመሆኑ በዓለም አቀፍ የጦርነት ሕግ ጦርነቱን የለኮሰው አካል የሚጠብቀው ፍርድ ምን ይሆን? ደሴ ላይ ሆነው እነርሱ በሕዝብ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስት ወደ ዘብጢያ እናወርደዋለን በማለት ያስተላለፉት ውሳኔ ዛሬ በእነርሱ ላይ ተፈፃሚ የማይሆንበት ምክንያት ምንድነው? ከየትኛውም ድርድር በፊት የሕወሓት የጦር ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!

ፎቶ:- ህወሓቶች ለወረራ ካርታ ዘርግተው ሲመካከሩ

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top