Connect with us

ክብርት ከንቲባ ሆይ አመሰግንዎታለኹ

ክብርት ከንቲባ ሆይ አመሰግንዎታለኹ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ክብርት ከንቲባ ሆይ አመሰግንዎታለኹ

ክብርት ከንቲባ ሆይ አመሰግንዎታለኹ

በማለዳ የሰማኹት ዜና እንዲህ ይላል፡፡

“አባቱን በጦር ሜዳ የተነጠቀው ታዳጊ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ባለሁለት መኝታ ኮንደሚኒየም መኖሪያ ቤት አስረከበውታል፡፡ ቤቱ ከእነሙሉ ዕቃው መሆኑ ደግሞ ይበልጥ የሚያስደስት ነው፡፡”

ክብርት ከንቲባ ሆይ ያደረጉት መልካም ተግባር በምድርም በሰማይም የሚያስመሰግንዎት ነው፡፡ የእኔ ከንቲባ ስለሆኑም በግሌ ኮርቼብዎታለሁ፡፡

ነገርግን ወንበዴው ቡድን ያደረሰው ጥፋት በቃላት አይገለጽም፡፡ እንዲህ ያሉ በጦርነት ቤተሰቦቻቸው ያጡ ወገኖቻችን(ታዳጊዎች) እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ታዳጊ ወጣቶች ያለአሳዳጊ ሜዳ ላይ እንዳይቀሩ መንግስት ኃላፊነት አለበት፡፡ ምግባረ ሰናይ ተቋማትና በጎ አድራጊ ግለሰቦችን በማስተባበር አንድ የተጎጂ ቤተሰቦች ልጆች የሚያድጉበት  ማዕከል በአዲስአበባ እንዲቋቋም ያደርጉ ዘንድ እንደአንድ ጉዳዩ እንደሚያገባው ኢትዮጵያዊ አሳስባለኹ፡፡ ስላደረጉት ኹሉ በድጋሚ አመሰግንዎታለኹ፡፡

አክባሪዎ

እሱባለው ካሳ

…………..

የአዲስአበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት እነሆ

ለ 40 ቀን በአባቱ እቅፍ ዉስጥ  ሆኖ ለኢትዮጵያ የተዋጋዉን ህፃን ቢኒያም ጌታቸውን እና አሳዳጊ አክስቶቹን ዛሬ በአካል አግኝቻቸዋለሁ ።

የጀግናው መቶ አለቃ ጌታቸው ሞረዳ ልጅ በእዚህ የጨቅላነት ዕድሜው ማየት የማይገባውን አይቷል። የኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆች ለአገራቸው ሲዋደቁ በልጅነት አይኑ፣ በህፃን አእምሮዉ ቀርፆ አስቀምጧል።

ጀግና አባቱ በጀግንነት ለኢትዮጵያ ክብር ተሰዉቷል። ህፃን ቢኒያም አሁን ላይ በአእምሮው ምን እንደሚመላለስ መገመት አያዳግትም። በመሆኑም በፍጥነት ትምህርት እንዲጀምር አስፈላጊው የስነልቦና ድጋፍና ክትትል እንዲደረግለት፣ አሳዳጊዎቹም በተረጋጋ ሁኔታ ቢኒያምን እንዲያሳድጉ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር አድርገናል ።

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር  በቀጣይም  ነዋሪነታቸው አዲስአበባ የሆኑ  ህይወታቸውን ለአገራቸዉ ሲሉ ለሰዉ የሰራዊቱ አባል ቤተሰቦች   አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ለኢትዮጵያ የወደቁ ጀግኖች ልጆችን መንከባከብ፣ “አለንላችሁ” ማለት ከሁላችንም ይጠበቃልና  ይህ ተግባር ችሮታ ሳይሆን ግዴታችን በመሆኑም መሰል ተግባራት በክልሎችም እንደሚተገበሩ ተስፋ አደርጋለሁ ።

ለቢኒያም አሳዳጊዎች በ2013 ዓ/ም ባጣራነዉ መሰረት በህገወጥ ተይዘው ከተገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዉስጥ አንዱን አስረክበናቸዋል።

በዚህ ሂደት ዉስጥ አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ ልጁ ራሱን እስከሚችል አመታዊ ወጪዉን ለመሸፈን ዛሬ በተግባር የጀመሩትን አቶ ሳቢር አረጋዉንና የጂብሰን ትምህርት ቤትን ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top