Connect with us
Social media

ነፃ ሃሳብ

#ተኩላው

#ተኩላው

(ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት)

ተኩላ በጎችን ሁለት ጊዜ ነው የሚያጠቃቸው፡፡ በሩቁና በቅርቡ፡፡ በሩቁ፣ ተራራ ላይ ወጥቶ መጥፎውን ጠረኑን ወደ ታች በነፋሱ መምጫ በኩል ይለቅባቸዋል፡፡ በጎቹም ጠረኑን ስለሚያውቁት በፍርሃት ይርበደበዳሉ፡፡

በዚህ መጣ በዚያ መጣ የሚለውን ግን ስለማይለዩት ፍርሃቱ ይተርፋቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ በጠረኑ ሽታ ፈርተው አካባቢውን ጥለው ይጠፋሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ግራ ተጋብተው ባሉበት መስክ መረጋጋት ይሳናቸዋል፡፡ በተለይም ደግሞ ገላግልቱ ልምድ ስለሌላቸው በጣም ይሸበራሉ፡፡

በዚህ አጋጣሚ በተነዛው ሽታ ተደናግጠው መስኩን ጥለው ከሚፈረጥጡት ገላግልት የተወሰኑትን ተኩላው ያለ ድካም ይነጥቃል፡፡ የተኩላውን ጠባይ ያላወቁት ጠቦቶቹ በአካባቢያቸው ያገኙትን የራሳቸውን ወገን ተኩላ እየመሰላቸው መውጋት ይጀመራሉ፡፡ በዚህ መሐል ተወግቶና ተዳክሞ የሚወድቅ ጠቦት ይገኛል፡፡ አትራፊው ግን ያው ተኩላ ብቻ ነው፡፡

ሽብር በመንዛት በበቂ ሁኔታ ያልተሳካለት ከሆነ ደግሞ፣ ተኩላው ተራራው ላይ ሆኖ ይመለከትና ቁልቁል ወደ መስኩ ከሰሜን ወደ ደቡብ ይሸመጥጣል፡፡ ያን ጊዜ በጎቹ በፍርሃት ለሁለት ይከፈላሉ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ይሸመጥጣል፡፡ አሁን ደግሞ በጎቹ ለአራት ይከፈላሉ፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለ ለስድስት፣ ለስምንት፣ ለአሥር፣ ለአሥራ ሁለት፣ ይበታትናቸዋል፡፡ በዚህ መካከል ግርግር ይፈጠራል፡፡ አካባቢው ይሸበራል፤ የበረታ ይሮጣል፤ የደከመ ያዘግማል፤ የተደናገረ ባለበት ይቆማል፡፡ ተኩላውም ያለ ብዙ ድካም ከግርግሩ ያተርፋል፡፡

የወያኔ ስልት የተኩላ ስልት ነው፡፡ አንድም በሽብር ወሬ ይበታትናል፤ አንድም ራሱ ገብቶ ይከፋፍላል፡፡ በጎች ከተኩላ የሚተርፉት በሁለት መንገድ ብቻ ነው፡፡ አንደም የተኩላውን ጠረን ዐውቀው ነቅተው ከጠበቁት፤ አንድም ሁሉም በአንድነት ሰብሰብ ብለው፤ ቀንዳቸውን ወድረው ከጠበቁት፡፡

ያኔ ተራራው ላይ ሆኖ ነገሩን ይገመግምና፡-
በጎች፣ ካልተከፋፈሉ ወይ ካልተሸበሩ
ርሃብ ነው ጠኔ ነው የተኩላው አዳሩ፤
ብሎ እያንጎራጎረ ወደ ዱሩ ይመለሳል፡፡ በተኩላው ወያኔ ላይ እንወቅበት፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top