Connect with us

ህወሓትን እንደናዚ

ህወሓትን እንደናዚ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ህወሓትን እንደናዚ

ህወሓትን እንደናዚ

ኢትዮጵያውያን ህወሀት ከሚለው ስም ጋር ያለንን ደመኝነት አይሁዳውያኑ ናዚን ለመጥላት የሄዱትን እርቀት ያክል መጓዝ ይገባናል!

(ያሬድ ነጋሽ)

ህወሀት ጠላቴ ነው ለሚለው ህዝብ በበጎ ጎኑ ምስክርነት የሠጠበት አንድ አጋጣሚ አለ። ባሳለፍነው ወራት የህወሀትን ተልእኮ ተሸክመው ከኢትዮጵያውያን ሀይሎች ጋር ፊት ለፊት ገጥመው የነበሩ ሴቶች የሀሰት አሻንጉሊት ህፃን አስመስለው በማዘል ፤ ሆዳቸው ውስጥ ጋቢ በመክተት የሀሰት እርጉዝ በመምሠል ተሠልፈው እንደነበር ሰምተናል። 

ይህ ድርጊት የህወሀት ሀይሎች ከፊታቸው የቆመው የኢትዮጵያ ሰራዊት ስላለው የሞራል ልእልና ምስክርነት የሰጡበት አጋጣሚ ነበር። በሌላ አነጋገር ህፃን ያዘለችን ሴት ተኩሶ ለመምታት የሚከለክል እርህራሄ ያለው፤ እርጉዝ ሴትን በጥይት ተኩሶ እንዳይጥል ያደገበት ባህልና ስነ ልቦና እንደማይፈቅድለት ተማምነዋል። የህወሀት ሀይል ለኢትዮጵያ ጦር ይህንን በገሀድ ከመሠከረ በሗላ እርጉዝ ሴት እስከመድፈር ድረስ በመጓዝ እራሱን በምን አይነት የስነ ልቦና ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አሳይቷል።

ህወሀት ከፅንሰቱ አንስቶ በስልጣን በቆየባቸው አመታት የኦሮሞ ህዝብ በአማራ ህዝብ ይሄን ተደረገ ፤ ይሄ ደረሰበት በማለት የጥል ሀውልት እስከማቆም እንዳደረሰው ትርክት አይነት ዛሬም በተመሣሣይ መልኩ በሰሜን ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በፈፀመው ወንጀል ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር የትግራይ ህዝብ በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ግፍ በሚል በሁለቱ ብሄሮች መካከል ታሪካዊ ጠላትነትን ማወጅ ቀላል ነው።

ነገሩን በዚህ መንገድ ከመመልከት ይልቅ ጉዳዩ በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣና የልብ ስብራትን ያደረሰ ክስተት ነውና  አንድም በአማራው ላይ የደረሰ በደል ከሚል ስያሜ ተሻግሮ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመ ዘግናኝ ግፍ በሚል ጉዳዩ ሲሰነድም ሆነ ሲዘከር አጀንዳው ሀገራዊ ሊሆን ይገባዋል። በሁለተኝነት ነገ ላይ ኢትዮጵያ ላይ ህወሀት ያደረሰውን ዘግናኝ ግፍ የሚኮንን ፣ የሚፀየፍ ፣ በነገሩ የሚያፍርና በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር አዲስ ትውልድ በትግራዊያን ዘንድ ሊፈጠር ይችላል የሚል ተስፋ በማድረግ የድርጊቱ ፈፃሚ አካልን የትግራይ ህዝብ ነው ከሚል አገላለፅ ይልቅ የትግራይ ህዝብ ወኪል ነኝ በሚለው ህወሀት ስም ዘግናኙ ድርጊት ተፈፅሟል ብሎ ማሠብ የተቀረው ኢትዮጵያዊና የትግራይ ህዝብ በቀጣይ የሚኖረውን የአብሮነት ጉዞ ጡዘት በጥቂቱም ቢሆን ያረግባል ብዬ አስባለሁ።

የህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን የቆይታ ታሪክ መቋጫ ሊሆን ይገባል የምላቸውን ሁለት አንኳር ነጥቦች ላንሳና ጉዳዬን ላጠቃልል፦

1.በየአመቱ የካቲት 12  ቀን ፋሽስት ኢጣልያ ጦር በንፁሀን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመው ጭፍጨፋ ለመዘከር በዓል ሆኖ ተከብሮ ይውላል።በተጨማሪም በትምህርት ስርአት ውስጥ በታሪክ መልክ ተካቶ ለተማሪዎች እንደሚሰጥ እናውቃለን። የህወሀት ታሪክ አገሪቷ ገጥሟት ካሣለፈቻቸው ፈተናዎች መሀል አቻ ከሌለው ፀያፍ ግብሩ ጋር ለዘመናት ታትሞ ይኖር ዘንድ አንድም ህወሀት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ላይ  ፀያፍ ግብሩን የፈፀመባቸው አራቱ ወራት በተለየ ሁኔታ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ታስቦ ሊውል ይገባዋል። በሁለተኝነት በትምህርት ስርአት ውስጥ በታሪክ መልክ በማካተት ለተማሪዎች መማሪያ በሚሆን መልኩ በመስጠት ትውልድ ሁሉ እየተፀየፈው የሚኖር ገጠመኛችን ተደርጎ መወሰድ ይገባዋል።

2.ጀርመናውያንና አይሁዳውያን የናዚን ስም በበጎ መልኩ እንዲወሣና እንዲዘከር ይቅርና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይሄ ስም ተነስቶ ለሀያና ለሰላሳ ደቂቃ ያህል ቢቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ተቋሙን ካሣ ሊያስከፍሉ እንደሚችሉ እናውቃለን። ኢትዮጵያውያን ህወሀት ከሚለው ስም ጋር ያለንን ደመኝነት ጀርመናውያኑና አይሁዳውያኑ ናዚን ለመጥላት የሄዱትን እርቀት ያክል መጓዝ ይገባናል። 

ህወሀት የሚል ስም በበጎ አንስቶ  ከበሮ እስከመደለቅ የሚያደርስ እንቅስቃሴ ህወሀት በስልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ካደረሠው ግፍና መከራ በተጨማሪ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በፈፀመውና ወደፊትም በትውልድ ደረጃ እየታሰበ በሚኖረው  ዘግናኝ ግፍ ላይ እንደመሣለቅ የሚቆጠርና ከግፉ ፀበል ፃዲቁ እንደመቋደስ ተደርጎ ይወሰዳልና ማንኛውም ሠው በውጪም ይሁን ከውስጥ በቀጣይ እስከአለም ፍፃሜ ኢትዮጵያ በሚኖራት ቆይታ ውስጥ አብሮ በስምምነት ለመጓዝ ይህንን እውነት አፅንኦት ሠጥቶ ሊቀበለው ይገባል።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top