Connect with us

የሆዳቸውን ለነገረን ጌታቸው ረዳ ምሥጋናችን ወደር የለውም፤ ዕዙ ፈርሷል ብሎን ነበር….

የሆዳቸውን ለነገረን ጌታቸው ረዳ ምሥጋናችን ወደር የለውም፤ ዕዙ ፈርሷል ብሎን ነበር ፤ ዕዙን አክመን ትህነግን ቀብረናታል!!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የሆዳቸውን ለነገረን ጌታቸው ረዳ ምሥጋናችን ወደር የለውም፤ ዕዙ ፈርሷል ብሎን ነበር….

የሆዳቸውን ለነገረን ጌታቸው ረዳ ምሥጋናችን ወደር የለውም፤ ዕዙ ፈርሷል ብሎን ነበር ፤ ዕዙን አክመን ትህነግን ቀብረናታል!!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ ድሬቲዩብ)

ጌታቸው ረዳን ያህል ባለውለታ የለንም፡፡ ጌታቸው የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ባይሆን ኖሮ ሲዖል ድረስ ወርዶ ኢትዮጵያ ለማጥፋት የታሰበውን ማን ይነግረን ነበር?

ጌታቸው ረዳ ቀን የመከሩበትን ማታ እየዛተ ባይጠቁመን ኖሮ ከተኛንበት ማን ያነቃናል፡፡ እሱ ባለውለታችን ነው፤ የሆነውን ብቻ ሳይሆን የሚሆነውን ነግሮናል፡፡ ለምሳሌ ደሴ ሊያዝ ሲል ዕዝ ፈርሷል፡፡ መከላከያው ተበትኗል ያለን ጥሩ ጥቁምት ሆነና ወራሪው ሰሜን ሸዋን እንዳያልፍ መንቂያችንን አቀበለን፡፡

ጌታቸው ረዳ እንደ ፋኖው እንደ ልዩ ሃይሉ እንደ ሚሊሻው እንደ መከላከያ ሠራዊት ሆድ ያባውን ሚዲያ ያወጣል እስክንል በቴሌቨዥን መስኮት ብቅ እያለ በሚያወራው ነገር ለድሉ ስኬታማነት የድርሻውን ተወጥቷል፡፡

ጌታቸው የወያኔ ህገ መንግሥት፣ መርዛማ ጥላቻ፣ በየቦታው የተቀበረ የቂም ፈንጂ ብዙ ቦታ የከፋፈለውን ዜጋ አንድ ለማድረግ ያበረከተልን አስተዋጽኦ ምትክ የለሽ ነው፡፡ እኛ ጋር ሆኖ ከከፋፈሉን እዚያ ሆኖ በንግግሩ ቁጭት ተሰምቶን እንድንዋሃድ አንድ ያደረገን ጌታቸው ባለውለታችን ነው፡፡

ጌታቸው ኦሮሞና አማራ እሳትና ጭድ መደረጋቸውን ሳያውቁ በወያኔ ድራማ ጥላቻ ሲዘራባቸው መኖራቸውን ያጋለጠልን ባለውለታ ነው፡፡

ጌች ነበር እኮ የአማራ ኤሊት ላይ የምናወራርደው ሂሳብ አለ ብሎ ዳር የያዘውን ኤሊት ውጊያ እንዲገባልን ያገዘን፡፡ ጌችማ ውለታው ብዙ ነው፡፡ ብዙ ምስጢር ብዙ ሴራ ብዙ ድራማ ታፍኖ ይቀር የነበረው እድሜ ለጌች ቤታችን ድረስ ቁጭ ብለን አደመጥነው፤ ነቃን፣ ተደራጀን፣ ድል አደረግን፡፡

ጌች ከዚያች መሰሪዋ ትህነግ መሃጸን የወጣ አይመስልም፡፡ ትህነግ ራሷ ገድላ የቀብር ስርዓት የምታደምቅ መሰሪ ስትሆን ጌች ግን ገና ያልሞተውን ልንገድለው አቅደናል ብሎ መረጃ በአደባባይ የሚያደርሰን የእኛ ሰው በትህነግ ቤት ነው፡፡

ብዙዎቹ የጌታቸው ረዳ ንግግሮች መልካም እድሎች ይዘው የመጡ የትግሉ ስኬት ምክንያቶች ናቸው፡፡ ስውሩ ሸኔ አደባባይ ከእኛ ጋር ጋብቻ ፈጽሟል ብሎ ባይነግረንና ጃልመሮን ጭምር ባያስለፈልፈው ኖሮ ይሄኔ ተወናብደንና በስውር ሴራው ተጎድተን ነበር፡፡

ጌች ቅማንትና ጉሙዝ እያለ ያቀዱትን ባይተነትንልን ኖሮ የአንድ አባት ልጆች አማራ ቅማንት በማያውቁት አልቀው ነበር፡፡ ያነቃንን ጌታቸው ረዳን ሳናመሰገን ማለፍ ንፉግነት ነው፡፡ እሱ ከእኛ ድንዙዝ ባለስልጣናት ሁሉ በበለጠ ባለውለታችን ነው፤ እንድንደራጅ ምክንያት ሆኗል፡፡ አብንን ዱርዬ ብሎ ጦርነቱ የብልጽግና እንዳልሆነ ለአማራ ልጆች በደንብ ያስረዳልን የጠላት ወዳጅ ነው፡፡

ሰሞኑንም እየጠበቅን ነው፡፡ ገና እንቀጥላለን ሃይል አለን እያለ ብዙ ነገር ነግሮናል፡፡ አመስግነን መረጃውን ተጠቅመን፣ ሸሽተን ነው አልሞትንም ስላለን ገዳይ አይደላችሁም ያለንን ተቀብለን ትህነግን ወደ መቃብሯ እንሸኛታለን፡፡

ከሁሉ በላይ ግን የሁልጊዜው ወዳጃችን አጋራችንና የመረጃ ስፖንሰራችን ጌታቸው ረዳ ይኑርልንና የማንሰማው የተሰወረ ትህነግ አቅዳው የተደበቀ ነገር የለም፡፡ ማታ ሲሆን ብቅ ብሎ ጌች እንካችሁ ይለናል፡፡ የድላችን መንገድ ለሆነው ሰው ምስጋናችን ወደር የለውም፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top