Connect with us

ለክቡራን የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች

ለክቡራን የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች
ታዬ ደንደአ

ነፃ ሃሳብ

ለክቡራን የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች

ለክቡራን የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች

ምንም ሸቀጥ አታምጡ!

(ታዬ ደንደአ)

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ለሚቀጥለዉ ገና ቢያንስ አንድ ሚሊዬን ኢትዮጵያውያን ወደ ኢትዮጵያ ይመጡ ዘንድ ጥሪ አቅርቧል:: እጅግ ብዙ ዜጎችና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ጥሪዉን በደስታ ትቀብሏል! አብዘኛዉ ደግሞ በባንዳና በባዳ ሴራ ተፈናቅለዉ ለሚቸገሩት ወገኖቹ ምን ይዞ እንደሚመጣ ይጠይቃል! በዚህ ልክ ወገን ለወገን ሲያስብ ደስ ይላል! እንደ ህዝብ ያለንን የብልፅግና ራዕይ ለማሳካት መደመራችን ግድ ይላል! ይህ ከመተሳሰብ ይጀምራል!

ነገር ግን የውጭ ቅኝታችን ሊስተካከ ይገባል! ምን ለምን ይመጣል? በዚህ ጉዳይ ሀሳቤ የሚከተለዉን ይመስላል! ምንም ዓይነት ዕቃ ወያም ሸቀጥ አታምጡ:: ዕቃ ሊትገዙበት ያሰባችሁትን ዶላር / ፓዎንድ/ ፍራንክ ብቻ ይዛችሁ ኑ! ይህ በእንድ ድንጋይ ሦስት ወፎችን መምታት ያስችላል! አንደኛ ኢትዮጵያ የማይናቅ የውጭ ምንዛሪ ታገኛለች:: አንድ ሚሊዬን ሰዉ $500 ዶላር ብቻ እንኳን ቢያመጣ ሀገሬ $500,000,000 ታገኛለች! እያንዳንዱ $5000 ማምጣት ቢችል ደግሞ ኢትዮጵያ $5 ቢሊዬን የውጭ ምንዛሪ ታፍሳለች!

ሁለተኛ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች እጅግ ይበረታታሉ! ሸቀጦቻችን ቢያንስ $500,000,000 – ከፍ ሲል ደግሞ የ$5 ቢሊዬን ገበያ ያገኛሉ:: ይህ ኢትዮጵያ ከAGOA መገፋቷን ትርጉም ያሳጧል!

ሦስተኛ የትራንስፖርት ወጪ ስለማይኖር በገንዘቡ ብዙ ሸቀጥ መሸመት ይቻላል! ይህ ደግሞ ለተፈናቃዮች ትልቅ እፎይታ ያስገኛል! ስለዚህ ገንዘብ እንጂ ሸቀጥ አታምጡ! ለጉዟችሁ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ተጠቀሙ!ከቻላችሁ ደግሞ በሚትኖሩበት ሀገርም የኢትዮጵያን ምርት ተጠቀሙ! ያን ቢታደርጉ ያለምንም ተጨማሪ ወጪ ሀገራችሁን ትረዳላችሁ! የሰዉ ወርቅ አያደምቅ! በኢትዮጵያ ምርት እንኩራ! በሠላም ኑ!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top