Connect with us

ያላደረጉብን ምንም የለም…

Social media

ነፃ ሃሳብ

ያላደረጉብን ምንም የለም…

ያላደረጉብን ምንም የለም፤ ይሄ ቢያንስ የላኳቸው የውጪ ሰዎች አይናቸውን ቢጨፍኑ ለሌላው ዓለም ልናሳየው የሚገባ ነውር ነው!!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ ድሬቲዩብ)
ምንድን ነው ያላደረጉብን? ቡሃቃችንን ነው ቤተስኪያናችንን ያከበሩት? እናቶቻችን ወይስ መስጂዶቻችንን የተውልን? አንድ አባት በቴሌቨዥን መስኮት ነገሩ ግርም እያላቸው “ኪስ ፈትሸው መስታወት ወስደዋል” አሉ፡፡ ግን ያልወሰዱብን ምንድን ነው?

እኛ ሞኝ ስለነበርን መሬት ሰርቀዋል፣ መርከብ ሸጠዋል፣ ግድብ በልተዋል፣ ሀገር ዘርፈዋል ብለን ነበር፡፡ እነሱ ግን ያላደረጉት የማያደርጉት እንደሌለ አሳይተውናል፡፡ መስቀል አንጠልጥለው እሞሃይ ታግለዋል፡፡ እውነት የተፈጥሮ ባህሪያቸው ነው፤ ግን ይሄን ዓለም መስማት አለበት፡፡
ቢቢሲ ሲኤንኤን ወይም አልጀዚራ ዓይኑን ሊጨፍን ይችላል፡፡ የፈረንሳይ ጣቢያ ወይም ሮይተርስ ይሄ ነውር ባይወጣ ይመርጣል፤ ነውሩ ሊያፈርሷት ባሰቧት ሀገር ላይ ጉዳት ካደረሰ ለእነሱ ምናቸውም ነው፡፡ ግን ሌላው ዓለም እንዲያየው ማድረግ አለብን፡፡

ዛሬ በዓለም ብዙ ሚዲያ አለ፤ የፈጀውን ፈጅቶ ከወዳጅ ሀገራት ሚዲያ ባለሙያዎች መጥተው ከምንላቸው በላይ የሆነብንን ይዩት፤ ጫጩት ሰርቆ፣ ከተማ አጥፍቶ፣ ዱቄት ተሸክሞ አንዲት ፍሬ ልጅ በቡድን ደፍሮ ስለሄደ የዚህ ዘመን አውሬ ነውር ታሪኩ እንዲኖር ጥሪ ማቅረብ ይኖርብናል፡፡

የአፍሪካ ሚዲያዎች ገብተው ይመልከቱ፣ የቻይናው ዜና ተቋም መጥቶ ከእኛ ጎን እንኳንም ቆምኩ የሚልበትን ተግባር ይዘግብ፣ እነሱን የላኩት ሀገራት ሃያ አይሞሉም፤ ዓለም ሰፊና ብዙ ነው፡፡ ብዙ ሚዲያዎች ያደረጉትን ተመልክተው ዓለም እንደ ሰው ልጅ ነውር አስቀምጦ ይማርበት፡፡

ባለማተም ቤተስኪያ ደፋሪዎች፣ ሃይማኖተኛ አስገድዶ ተኚዎች፣ ከተማ አውዳሚዎች፣ ከብት ገዳይ ጀግኖች፣ ዝርፊያ ክብር እንደሆነ የሚሰማቸው አረመኔዎችን ገበና መሸፈን የለብንም፡፡ ይሄ በዓለም ዘንድ መታየት አለበት፡፡ የዓለምን ሚዲያ የኢትዮጵያ መንግስት ጠርቶ ያሳይ፣ በአዲስ አበባ የሚኖሩ አምባሰደሮች ችግሩ ወደ ተከሰተበት አካባቢ ይሂዱ ይመልከቱ፣ ፖለቲካ የመሰላቸውን ነውር መሬት ወርደው ይዩት፤

የሰው ልጅ አእምሮ በዚህ ዘመን በዚህ ደረጃ ወደ ኋላ ቀርቷል ብሎ ለማመን የሚከብድ ታሪክ ተሰርቷል፡፡ አንድ ሀገር አንድ ባህል አንድ ታሪክ ነበርን በሚሉ ህዝቦች መካከል እንዲህ ያለ ነገር ይፈጸማል ብሎ ለማመን ይከብዳል፡፡ ይሄ ህመም የሰው ልጅ ሁሉ ህመም መሆን አለበት፤

በብዙ መልኩ ነጻና ገለልተኛ የዓለም ሚዲያዎች አሉ፤ እነሱ ገብተው እነሱ አይተው እነሱ ቀርጸው ያስቀምጡት፡፡ ይሄ ተደብቆ መቅረት የሌለበት የሰው ልጅ የሚማርበት ጸያፍ ታሪክ ነው፡፡ ለዚህ አስፈላጊው ነገር ቢከፈልም ቢወጣም አይጎዳም፡፡ ይሄ ነውርና በደል የፈጸሙትና ዘራቸውን ሲከተል የሚኖር እንደ አቤል ደም የሚጣራ እንደ ቃየል እነሱ የሚያቅበዘብዝ እንዲሆን መሰራት አለበት፡፡

ፖለቲካ ድራማ ነው፤ ነገ የውሸት ስለመተቃቀፍ ማሰብ ሞኝነት ነው፤ ያልተደረግነው ምንድን ነው? በዓለም የተከሰተ ወረርሺኝ በዚህ ደረጃ በሰው ልጅ አይጨክንም፤ በዓለም የመጣ ጎርፍና እሳት እንዲህ አረመኔ አይሆንም ስጋና ደም ያለው የማይፈጽመውን ፈጽመውብናል፡፡ አቃጥለው አፍርሰው ገድለው ነገ እንዳይኖር አጨልመው ለማምለጥ የሞከሩ ናቸው፡፡ ይሄን ዓለም ማየትም ማወቅም አለበት፤

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top