Connect with us

ከሶማሊ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን የተሰጠ የአቋም መግለጫ!!

ሶማሊ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን

ዜና

ከሶማሊ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን የተሰጠ የአቋም መግለጫ!!

ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከሶማሊ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን የተሰጠ ሳምንታዊ የአቋም መግለጫ!!

ባለፉት ሶስተ አስርተ አመታት አሸባሪው ህወሀት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ባደረሰው ዘርፈ ብዙ ችግሮች እና በደሎች መካከል በሶማሊ ክልል ህዝብ ላይ ያደረሰው ግፍና መከራ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ አዕምሮ የሚጠፋ አይደለም።

አሸባሪው የወያኔ ቡድን በሶማሊ ክልል ከፈፀማቸው ወንጀሎች መካከል ንፁሀን ዜጎች ከነህይወታቸው ተቀብረዋል፣ ህፃናት እና ሴቶች ተደፍረዋል፣ ክቡሩ የሰው ልጅ ከአውሬ ጋር ታስሯል ፣ወጣቶች ተገድለው በገመድ ተጎትተዋል፣ ይህ ሁሉ ግፍ በአሸባሪው ህወሃት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በጀነራሎቹ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተፈፀሙ እንደነበር ይታወቃል።

የሽብር ቡድኑ በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የኢትዮጵያን ህዝብ ለማለያየት ይከተል የነበረው የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ በሶማሊ ክልልም በመተግበር የክልሉን ህዝብ በጎሳ በመከፋፋል በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ግንብ በመገንባት እርሰ በእርሳቸው በጥርጣሬ እንዲተያዩ በማድረግ ስልጣኑን ለማራዘም ተጠቅሞበት የኖረ አረመኔ ቡድን ሆኖ ቆይቷል።

አሸባሪው ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ የተባበረ ክንድ ከተወገደ በኋላ እኔ ስልጣን ካጣው ሀገር አፈርሳለሁ በሚል በእብሪት ጥቅምት 24/2013 ቀይ መስመር በሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀሙ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት የሆነው የወያኔ እኩይ ተግባር ለመመከት የሀገራች ህዝቦች በሠሩት ተጋድሎ የሶማሊ ክልል ህዝብ በግንባር ቀደምትነት ተሳትፏል፣ የአሸባሪው ቡድን ግብዓተ መሬት እስኪፈፀምም ህዝባችን ትግሉን ይቀጥል።

ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት በሶማሊ ክልል 10 ዞኖች በተከሰተው ድርቅ የክልሉ መንግሥት ህዝብና እንስሳትን ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ቢሆንም፣ ህዝቡ ከተፈጠረው ድርቅ ጎን ለጎን የሀገር ህልውናና ሉአላዊነትን በማስቀደም አካባቢውን ከአሸባሪዎች በመጠበቅ ትልቅ ተጋድሎን በማድረግ ላይ በመሆኑ ላቅ ያለ ምስጋና የክልሉ መንግስት ያቀርባል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሊ ክልል ህዝብ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን የገባችበት የህልውና ጦርነት የሶማሊ ክልል ተወላጅ ዲያስፖራ ማህበረሰብ በተለያዩ በውጭ ሀገራት ኮንፈረንሶችን አዘጋጅተው ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከመንግስት ጎን በመሆን ድጋፋቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው።

በሌላ በኩል በሚኒሶታ የሚኖሩ የክልሉ ዲያስፖራ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ግንኙነትን ፈጥረው በማህበራዊ ሚዲያዎች የሀሰት መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦችን እኩይ ሴራ ከማክሸፍ ባለፈ፣ በክልሉ ድርቅ የተከሰተባቸው አከባቢዎች እርዳታ በማድረግ ከሀገራቸው እና ከህዝባቸው ጎን መቆማቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚኖረው የክልሉ ህዝብ በሀገሩ ኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንደማይደራደር የሚያሳይ ነው።

የህልውና ጦርነቱን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በሀገር ህልውናና ሉአላዊነት የማይደራደረው ጀግናው የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሽብርተኛው ህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው አሸባሪዎችና የክልሉን ሰላም ለማናጋት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ፣ አጋጣሚውን ተጠቅመው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በጀግንነት ረዥሙን ድንበር በመጠበቅ አለኝታነቱን በድጋሚ በማሳየት ላይ ይገኛል።

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ መሀል ሀገር ሰላም ሆኖ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ የሶማሊ ክልል ህዝብና የፀጥታ ሀይሎች የሀገራችን ዳር ድንበር በመጠበቅ ላይ በመሆኑ የሀገራችን ህዝብ ምንም አይነት ስጋት እንዳይሰማውና ትኩረቱን ሀገር ማዳኑ ላይ እንዲያደርግ የሶማሊ ክልል መንግሥት ይገልጻል።

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መሪነት በተለያዩ ግንባሮች በአሸባሪው ቡድን ላይ የተገኘው ድል የሶማሊ ክልል ህዝብ የኮራበት ሲሆን፣ ቡድኑ እስኪደመሰስ የሶማሊ ህዝብ ከጠቅላይ ሚኒስትርና ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አብይ አህመድ ጎን መሆኑን ይገልጻል።

በመጨረሻም ባለሀብቶች፣ ነጋዴዎች፣ ድርጅቶች ለዘመናት የቆየው የሀገራችን ህዝቦች የመረዳዳት ባህል የሆነውን በማስቀጠል የተጎዱ ወገኖቻችንን በመርዳት እንዲሁም በሶማሊ ክልል የተፈጠረው ድርቅ ለህዝባችን የምናደርገውን እርዳታ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

√ ሰላም ለሀገራችን
√ ድል ለሀገር መከላከያ ሠራዊት

የሶማሊ ክልላዊ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ
ህዳር 23/ 2014 ዓ.ም
ጅግጅጋ

Continue Reading
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top