Connect with us

ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ 

ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር  ምክር ቤት 

ነፃ ሃሳብ

ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ 

ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ 

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በኩል  ለገና በአል 1ሚሊየን ዳያስፖራ ወደ ወደ ተስፋይቱ ምድር 

 ኢትዮጵያ እንዲገባ የተላለፈውን  ብሔራዊ ግብዣ  በመደገፍ በታላቅ አክብሮትና ደስታ የተቀበልነው መሆኑን እናረጋግጣለን  : :

በተጨማሪም  የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የመንግስትን ወቅታዊ. ግብዣ   በመደገፍ. ለተግባራዊነቱም  አብሮ  ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን እያረጋገጥን ከዚህ በፊት  ጀምረነው የነበረውን : የዳያስፖራ ቱሪዝምን. በማጠናከር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወደ ሐገር ውስጥ በመግባት የቱሪዝም  ኢንዱስትሪ ውን ለማሳደግና ለማዘመን. የራሱን አሻራ እንዲያስቀምጥ አሁንም እናበረታታለን :: 

 በ2014 አዲስ አመት   ” አባይን እንጎብኜው. !! 

 እንቁጣጣሽ ኢትዮጵያ ” የፍቅር ጉዞ. ! በተሰኘ መርሀ ግብር 

ከመላው አለም የተሰባሰቡ 500 የሚሆኑ  ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጅ ዳያስፖራዎችን ከጳጉሜ አንድ ቀን  ጀምረው. እስከ ጥቅምት 15 ድረስ በሚቆየው  የጉብኝት  መርሀ ግብር ለማሳተፍ ፣ ያደርግናቸው ሙከራዎች  85% የሚሆነውን ተልእኳችንን አሳክተን  ወደየመጣንባቸው ሐገሮች በደህና ተመልሰናል: :

አሁንም ቢሆን ያለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ከውጭ ጠላቶች ጋር በመቀናጀት አሸባሪው የጁንታ  ቡድን የከፈተብንን  ሀገር የማፍረስ ጦርነት ለመቀልበስና ሀገርን ለማዳን እየተካሄደ ባለው የህልውና  ትግል ውስጥ  ለመሳተፍ ይቻል ዘንድ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅፈት ቤት ያስተላለፈውን. የገና በአልን ግብዣ  በደስታ በመቀበል  አጋር ሆነን ለማስተባበር ዝግጁ  መሆናችንን በድጋሚ እናረጋግጣለን  : :

 በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር መዝመት የኢትዮጵያውያንን ጀግንነት የሚያሳይ የአሸናፊነት ተምሳሌት በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊታችን ባስገኜው ድል የተደስትንና የኮራን መሆናችን. እየገለፅን በምንገኝባቸው  ሐገሮች ሁሉ  በሰላማዊ ሰልፍና በዲፕሎማሲው ዘመቻ  የዜግነት ድርሻችንን እየተወጣን

ከመንግስት ጎን  መሰለፋችንን  እናረጋግጣለን: :

 ስለዚህ ዲያስፖራው በሀገር ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሰላምን ለማረጋገጥ የሀይማኖት ልዩነታችን እንደተጠበቀ ሆኖ. እጅ ለእጅ በማያያዝ  በመንግስት የተደረገውን የገናን በአል ምክኒያት በማድረግ ወደ ቅድስት ሐገር ወደ ኢትዮጵያ የፍቅር ጉዞ ለማድረግ. አስፈላጊውን ዝግጅት እንድናደርግ. የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ጥሪ ያደርጋል: :

  የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር  ምክር ቤትም  የጉዞው  አካል ለመሆን በቁርጠኝነት መነሳታችንን እያረጋገጥን ለኢትዮጵያ. ክብር  ህይወታቸውን  እየከፈሉ ለሚገኙት  የመከላከያ ሰራዊት አባሎቻችን  ወሰን የለለው አክብሮታችንን እየገለፅን  ከጎናቸው መሰለፋችንን   በታላቅ  ደስታ  እንገልፃለን: :

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ. !! 

ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክ! !

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር  ምክር ቤት 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top