Connect with us

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደር ሺመልስ አብዲሳ ያስተላለፉት መልዕክት፣

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደር ሺመልስ አብዲሳ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት፣
የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር

ነፃ ሃሳብ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደር ሺመልስ አብዲሳ ያስተላለፉት መልዕክት፣

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደር ሺመልስ አብዲሳ ያስተላለፉት መልዕክት፣

የተከበርከው የኦሮሞ ህዝብ፣ የተከበራችሁ ቄሮ እና ቀሬ፣ የተከበራችሁ ጀግኖችና የጀግኖች ቤተሰቦች ከሁሉ አስቀድሜ ከጥንት እስከ ዛሬ በደምና አጥንታቸው ነጻነቷ የተከበረ ሀገር ላቆዩልን ጀግኖች የምሰጠው ክብር ከፍተኛ መሆኑን መግለጽ እፈልጋለው፡፡

በተለይም 27 አመታት የኦሮሞን እና የኢትዮጵያን ህዝብ ሲጮቅን የነበረዉን አሸባሪዉን የህወኀት ቡድን ከነስሩ ለመንቀል ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን ቄሮና ቀሬዎች የከፈሉት መሰዋእትነት እንዳይረሳ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል፡፡

በዚህም በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው የለውጥ መንግስት የለቅሶን ጊዜ ታሪክ በማድረግ የህዝብን ድል አብስሯል፡፡ እብሪተኛው አሸባሪው ቡድንም ወደ መቀበሪያ ቦታው ሸሽቷል፡፡

ወጣቱን ሲገድል፣ ሲያስር ምሁራንን ሲስድድና ህዝብን ሲያሰቃይ የነበረው አረመኔው ስብስብ እንዳይመለስ ሆኖ ተሸኝቷል፡፡ የኦሮሞ ህዝብን ሀብት በመዝረፍ እንደ መዥገር ቆንዝሮ የነበረው ይህ ቡድን በህዝብ ትግል ከህዝብ ትከሻ ላይ ተሽቀንጥሮ እንዲወርድ ተደርጓል፡፡

በህዝብ እንደ ተተፋና እንደኮበለለ የተረዳው የቲፒ እል ኤፍ አሸባሪው ቡድን ህዝብን ወደ ማናከስና ማጋጨት አዲስ የብጥብጥ ፕሮጄክት ተሸገረ፡፡ የራሱን በግና ፊየል ትቶ ለኦሮሞ ሰንጋና ግመል የሚያዛጋው ይህ ቡድን ጥርሱን የነቀሰበትን የግጭት ሴራ ልምዱን በመጠቀም ሚሊዮኖች እንዲፈናቀሉ ሺዎች ደግሞ እንዲሞቱ አድርጓል፡፡

ለኢትዮጵያ ያለዉን ገደብ የለሽ ጥላቻዉን እና ኢትዮጵያን የማፍረስ ውጥኑን የሀገር አንድነት ምልክት የሆነውን መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር በገሃድ አሳየ፡፡

በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ ለአመታት የትግራይ ህዝብን ደንነት ሲጠብቁ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጭካኔ የተሞላበት ክህደትን ፈጸመ፡፡

በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ የተፈጸመዉን ክህደት አምርሮ የተቃወመው የኦሮሞ ወጣትም ከሌሎች ብሔረሰቦች ወንድሞቹ ጋር በመሆን እኛ እያለን ወያኔ ዳግም የክፋት ጓዙን እኛ ላይ አይጭንም በማለት ዘምተዋል፡፡

በሀገር አንድነትና ህልውና ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት በአንድነት ለመከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ አቅም ሆነዋል፡፡

የክልሉ ወጣቶች መሪያችሁ ዶክተር አብይ አህመድ ያስተላለፉላችሁን የሀገር ጥሪ ያለ አንዳች ማመንታት በመቀበል ታላቁን ህዝባችሁን በሚመጥን መልኩ ምላሽ እየሰጣችሁ ነው፡፡

ለዚህ ምላሻችሁ ታላቅ አክብሮት እንዳለኝ እና ገድላችሁ በታሪክ ሲወሳ እንደሚኖር ሳረጋግጥላችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

የኦሮሞ ህዝብና የኢትዮጵያ የአይን ብሌን የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሀገር የተጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ እና ዳግማዊ አደዋን በታሪክ ለመድገም ለአንድ ህይወቱ ሳይሳሳ ጦር ግንባር ወርዶ ከዚያ ይገኛል፡፡

በዚህ የጦር ውሎዉም ለአፍሪካ ትልቅ ተምሳሌት ሆኖ የሚወሳ ድል እነደሚመዘገብ አልጠራጠርም፡፡

ውዱ መሪያችን እኛ ኢትዮጵያውያን እያለን ሊያንበረክኩንና ነጻነታችንን ሊነጥቁን ከቅርብ ርቀት የሚያዘጉ ጠላቶቻችን በምድራችን ቁራሽ ቦታ አያገኙም ሲል ከሀገሩ ልጆች ጋር ዘምቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዘምቶ በማዘመትም ድል እየተቀጀ ነው፡፡ በተለያዩ ደረጃዎች ያለን እኛ አመራሮችና ህዝቡ በሞላ የጠቅላይ ምንስትራችንን ጥሪ ሰምተናል፡፡

የሀገር ህልውና እና አንድነትን ለማፍረስ የመጣን ጠላት መክቶ መመለስ የሚቻለው በተባበረ ክንድ እንደሆነ ነግረውናል፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ ቅሮዎችና ቀሬዎች ይህነ ታሪካዊ ጥሪ በመቀበል የዳግማዊ አደዋ ድል ታሪክ አካል እንድትሆኑ ጥሪዬን አስተላልፋለው፡፡

በተባበረ የህዝባችን ክንድ የጠላት አፍራሽ ተልእኮን ድባቅ እንመታለን!

ሺመልስ አብዲሳ

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top