Connect with us

የሠላም ኖቤል ተሸላሚው መሪያችን የሀገሩን ሠላም ሊያረጋግጥ እየመራው ያለ ዘመቻ በድል ይጠናቀቃል

Social media

ነፃ ሃሳብ

የሠላም ኖቤል ተሸላሚው መሪያችን የሀገሩን ሠላም ሊያረጋግጥ እየመራው ያለ ዘመቻ በድል ይጠናቀቃል

የሠላም ኖቤል ተሸላሚው መሪያችን የሀገሩን ሠላም ሊያረጋግጥ እየመራው ያለ ዘመቻ በድል ይጠናቀቃል

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)
የእኛ መሪ ሰላም ይወዳል፤ ሰላምን ፍለጋ ጦርነትን ተጸይፎ እንደ ፈሪ ተፎክሮበታል፤ እንደ ደካማ ተቆጥሯል፡፡ ከታጋሽ ህዝብ መሪ የሚጠበቀውን አድርጓል፡፡ እንደ ቀደሙት የኢትዮጵያ መሪዎች ዶክተር አብይ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን ፍለጋ ብዙ ተለማምጧል፡፡

ትህነጎች እንደ ቀደሙት አርአያዎቻቸው ደጋግመው በመካድ ደጋግመው ሀገራቸውን ቢወጉም ከቀደሙት ያልተማሩት አንድ ነገር ቢኖር በመጨረሻ ሰዓት እንኳን ድንጋይ ተሸክሞ ይቅርታ መጠየቅን ነው፡፡

የምዕራብ ሚዲያዎች ውጤት ላይ ያተኩራሉ፤ ሰላም ውጤት ነው፡፡ በትእግስትም ይመጣል በጦርነትም ይመጣል፡፡ የእኛ መሪ የሰላም ኖቤል ሽልማትን ወስዷል፡፡ ለሰላም እስከ መጨረሻ የሚቆም መሆኑን ሰላም ጠል ሃይሎችን በመደምሰስ ዳግም ያረጋግጣል፡፡

ትህነግን ከመደምሰስ በላይ ሰላምን ማረጋገጥ የለም፡፡ ትህነግን መደምሰስ የትግራይን ህዝብ አልፎም ኢትዮጵያን ብቻ መታደግ አይደለም፤ ከሃያል ሀገር ጋር ተሻርኮ የውክልና ጦርነት የሚዋጋ የቀጠና ሽፍታ ማስወገድ ነው፡፡ አፍሪካን ሰላም ማድረግ ነው፡፡

ትህነግን ለመደምሰስ ግንባር ዘምተው ድል እየተቀናጁ ያሉት ዶክተር አብይ ህጉ አይፈቅድም እንጂ ከዚህ ጦርነት በኋላ ጅቡቲን ትግራይን ሱዳንን ደቡብ ሱዳንን ጭምር ሰላም የሚያደርግ ድል ባለቤት በመሆናቸው ዳግም ኖቤል ይገባቸዋል፡፡

የአፍሪካን ታሪክ የሚቀይር ጦርነት ነው፡፡ በአማራ ህዝባዊ ሰራዊት፣ በአፋር ጀግኖች፣ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ድንቅ ተጋድሎ በኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ይህ ጦርነት ሲጠናቀቅ ዳግም አድዋ ይሆናል፡፡ የወገኑን ያፍራሉ፣ ያስወጉን መግቢያ ያጣሉ፡፡ ተልከው ሀገር ማፍረስ የፈለጉት ለዘለዓለም ይፈርሳሉ፡፡

አሁን ድሉ በየቀኑ ብዙ ጊዜ የሚመዘገብ ይሆናል፡፡ የሚገዙት ሳይሆን የሚጠሉት ግንባር ቆሟል፡፡ የትም መድረስ አይችሉም፣ የዝርፊያ መንፈስ የተጠናወታቸው ዘራፊዎች ነውራቸውን ዓለም የሚመለከትበት ቀን ነገ ነው፡፡

ጀግነው ድል አላደረጉም፣ ከሀገር በዘረፉት ገንዘብ ሀገር ሻጭ ገዝተው፣ ቆምንለት ላሉት ህዝብ ሳይጠነቀቁ ምንም የማያውቁ ዜጎችን የወንጀል ተሳታፊ አድርገው እዚህ የደረሱ ናቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ነገር ወደ ኋላ ነው፡፡ የዘረፉትን ሳይበሉ የሚከስሙበት ሌላ ምዕራፍ ይመዘገባል፡፡

ልጆቻቸው አባቴ ሀገር ሊያፈርስ ማድ ቤት ገብቶ ሊጥ እንደ ተሸከመ ድፍት ብሎ ቀረ የሚለው አሰቃቂ ታሪክ ለትውልድ ትተው ያልቃሉ፡፡ እውነቱን የሚሰማው ዓለም ዛሬ ለድራማ የጠላቴ ጠላት ብሎ አብሯቸው እንደቆመ አይቀጥልም ነገ በዚህ ነውራቸው ይሳለቃል፡፡

አፍሪካ እንደ አድዋ ሌላ የድል ታሪክ ከነጻነት ምድር ተጽፎ ይሰጣታል፡፡ አፍሪካውያን በቃ የሚሉበት አዲስ ምዕራፍ እውን ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top