Connect with us

አምባሳደር ጄፍሪ ፊልትማን እየዋሸን ነው!

Social media

ነፃ ሃሳብ

አምባሳደር ጄፍሪ ፊልትማን እየዋሸን ነው!

አምባሳደር ጄፍሪ ፊልትማን እየዋሸን ነው!
(ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ)

በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆነው አምባሳደር ጄፊሪ ፊልትማን ኖቬምበር 1, 2021፣ የአሜሪካ የሰላም ተቋም ባዘጋጀው መድረክ ላይ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ግንኙነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል። ገለልተኛና ነፃ ተቋም ስለመሆኑ የሚምለው ይህ ተቋም በአሜሪካ ኮንግሬስ አማካይነት የተመሠረተው እ. ኤ. አ. በ1984 ዓ.ም. ነበር።

ታዲያ በዚህ ማብራሪያው ላይ ፊልትማን በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት “Civil War” ስለመሆኑ አስረግጦ ከመግለፁም በላይ ጦርነቱ እልባት ካልተገኘለት ለ20 ዓመታት ያህል ሊዘልቅ እንደሚችል ጥናቶች ያረጋግጣሉ በማለት ለማስረዳት መሞከሩ ይታወሳል።

“Studies show the average modern civil war now lasts 20 years. I repeat: 20 years. A multi-decade civil war in Ethiopia would be disastrous for its future and its people.”

ጥያቄው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት “Civil War” ነው ወይ? የሚል ነው። በአጭር ቃል ጦርነቱ “Civil War” አይደለም።

የ20ኛውን ክ/ዘመን መገባደጃንና የቀዝቃዛውን ጦርነት ማክተም ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተካሄዱ ያሉ አብዛኞቹ ጦርነቶች ሲቪል ጦርነቶች ሊባሉ እንደማይችሉ ብዙ ጥናቶች ያረጋግጣሉ። ለዚህም በ980ዎቹና በ1990ዎቹ ለየት ባለ መልኩ ያቆጠቆጠው ግሎባላይዜሽን እንደ አንድ ምክንያት ይቆጠራል። በዘመነ ግሎባላይዜሽን ውጭ/ውስጥ የሚለው ነባር ግድግዳ በእጅጉ ሳስቷል፤ በሀገራት መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ ወታደራዊና ባሕላዊ ትስስር በእጅጉ ናኝቷል። በአንድ ሀገር የሚከሰት የትኛውም ሁነት ሌላውን የመንካት ዕድሉ ከፍተኛ ሆኗል፤ ደሴታዊነት ታሪክ ሆኗል። ስለዚህም ይህን ተከትሎ ጦርነቶችም ቅርፃቸውና ይዘታቸው ተቀይሯል። ቀድሞ “Civil Wars” ይበሉ የነበሩ ጦርነቶች ወደ ታሪክነት ተቀይረው “Old Wars” የሚለውን ስያሜ ተጎናፅፈዋል።

እናም አምባሳደር ጄፍሪ ፊልትማን የኢትዮጵያን ጦርነት “Civil” ብሎ ሲጠቅሰው ይህን ሳያውቀው ቀርቶ አይመስለኝም። በእንደዚህ ዓይነት ጦርነቶች ዕድሜ መራዘም የአሜሪካ እጅ እንዳለበትም ተሰውሮበት አይደለም። ይልቁን ዓላማው ጦርነቱን የውስጥ ጦርነት ብቻ እንደሆነ በመጠቆም ላይ ያነጣጠረ ነው። ዓላማው…ጦርነቱ ውስጥ የኛ እጅ የለበትም፤ የናንተው ጣጣ ነው… የሚለውን መልዕክት ማስተላለፍ ነው።

እንግሊዛዊቷ ሜሪ ካልዶር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካና በማዕከላዊ እስያ የሚደረጉትን ጦርነቶችን ቅርፅና ይዘት በተመለከተ በምታደርጋቸው ጥናቶቿ ትታወቃለች። ጄፊሪ ፊልትማን “Civil War” የሚለውን ስያሜ ለሰጠው ለኢትዮጵያ ጦርነት ሜሪ ካልዶር “New War” የሚለውን ነው የምትመርጠው።

የብሪስቶል ዩኒቨርስቲው ፕሮፈሰር ማርክ ደውፊልድ ደግሞ “Postmodern Wars” የሚለውን ስያሜ ይጠቀማል። እንግሊዛዊው ዴቪድ ክን ደግሞ Informal War” ይለዋል። አሜሪካዊው ፕሮፈሰር ክሪስ ሄብል ግሬይ ” Virtual Wars and Wars in cyberspace” የሚለውን ስያሜ ሲመርጥ፣ ፍራንክ ሆፍማን ደግሞ “Hybrid Wars” በማለት ይጠራል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ራሺያና አሜሪካ ሶሪያ ውስጥ እያደረጉ ያለው ጦርነት የውክልና ጦርነት (Proxy War) ተብሎ እንደሚጠራ ብዙዎቻችን የምናውቀው እውነት ነው።

ከላይ የጠቀስኳቸው የዘመኑ የጦርነት ዓይነቶች ፊልትማን “Civil War” ብሎ ከጠራው ከበፊቶቹ ጦርነቶች የሚለዩበት አንዱና ዋናው ነጥብ ጣልቃ የሚገቡ የዓለም አቀፍ ተዋንያን መብዛታቸው ነው። እንደ አሜሪካ ካሉ ከምዕራባውያን ሀገራት በተጨማሪ በሌላ ሀገር ጦርነት ውስጥ በልዩ ልዩ ምክንያት (ለምሣሌ በሰብዓዊ ጣልቃ ገብነት) ጣልቃ የሚገቡ ዓለም አቀፍ ተዋንያን ዝርዝር ይህን ይመስላል፦

▶️ ዓለም አቀፍ ዘጋቢዎች

▶️ ቅጥር አልሞ ተኳሾች

▶️ ሚሊተሪ አማካሪዎች

▶️ ወዶ-ገብ ዲያስፖራዎች

▶️ እንደ “USAID, OXFAM, SAVE THE CHILDERRN, HUMAN RIGHTS WATCH, UNHCR, EU, UNICEF, AU, UN” ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት (NGO)

በእርግጥ ጦርነቱ ጅምር ላይ “Civil War” ሊመስል ይችላል። በቆይታ ግን የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት እየጨመረ ሲሄድ ጦርነቱ ወደ “New War, Hybrid War, Proxy War” ይቀየራል። ለምሣሌ ሊቢያ ውስጥ ጦርነቱ የተቀጣጣለው መነሻ ላይ የአረብ አብዮትን ተከትሎ ቤንጋዚ ውስጥ ወህኒ ውስጥ የነበረ እስረኛ ጠበቃ እንዲፈታ በሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች በተነሳ ተቃውሞ ነበር።

ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል እንዲሉ በዚህ ክፍተት አያሌ “ጅቦች” ሀገሪቷን ሊቀራመቷት ወደ ሊቢያ ተመሙ። አሁን ባለንበት ወቅት በሊቢያ ሰማይ ሥር ፍላጎታቸውን በየፊናቸው የሚያንፀባርቁ ወደ 11 ሀገራት አሉ፤ እነሱም አሜሪካ፣ ፈረንሳይ ፣ እንግሊዝ ፣ግብፅ ፣ ሳውድ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣የአረብ ኢሚሬትስ ፣ ራሺያ፣ ኳታር ፣ ቱርክና ሱዳን ናቸው። ታዲያ እነዚህ ሀገራት በሙሉ እጃቸውን ያስገቡበት ጦርነት በምን ስሌት ነው “Civil War” ተብሎ የሚጠራው?

በእኛስ ሀገር ቢሆን ምዕራባውያን ለሕወሓት የሳተላይት መረጃን ድጋፍ እየሰጡ ባሉበት ሁኔታ፣ እንደ CNN, BBC, AP, Al Jazeera ወዘተ ያሉ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት ለ24 ሰዓታት በተቀናጀ ሁኔታ በፕሮፓጋንዳና በሐሰት ወሬ ሀገሪቷን እያመሱ ባለበት ሁኔታ፣ ግብፅና ሱዳን ወታደራዊ ሥልጠና እየሰጡ ታጣቂዎችን በድንበር በኩል እያሰረጉ በሚያስገቡበት ሁኔታ፣ USAID, UN እና EU ውግንናቸውን በግልፅ ለሕወሓት በገለፁበት ሁኔታ፣ ጄፍሪ ፊልትማን “ጦርነቱ ‘Civil War’ ነው” በማለት የተሳሳተ ማብራሪያ መስጠቱ ገራሚ ነው።

እሱ የጠቀሳቸው አጥኚዎች ሲቪል ጦርነት እስከ 20 ዓመታት ሊራዘም ይችላል ሲሉ ለመራዘሙ አንዱም ሰበብ እንደ አሜሪካ የራሳቸውን ጥቅም አስልተው ጣልቃ የሚገቡ ሀገራት ስለመሆናቸው ሳይጠቅሱ ይቀራሉ? አሁንስ ቢሆን አሜሪካ ለሕወሓት የሞራልና የሳይበርስፔስ ድጋፍ ከበስተጀርባ እየሰጠች ጦርነቱን ባታቀጣጥለው ኖሮ የጦርነቱ መልክ ዛሬ ምን ይመስል ነበር? አምባሳደር ጄፍሪ ፊልትማን ለ”ሲቪል ጦርነት” መራዘም የጠቀሰው የስታንፈርድ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፈሰር የ”JAMES D. FEARON” ጥናትን ይመስለኛል።

የጥናቱ ርዕስ “Why Do Some Civil Wars Last So Much Longer Than Others? ይሰኛል። ታዲያ በዚህ ጥናት ውስጥ ለጦርነቶች ዕድሜ መረዘም ከተጠቀሱት አምስት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ “Support from foreign States” የሚል ነው። ፊልትማን አማፂያንን ደግፎ ጣልቃ በመግባት የጦርነትን ዕድሜ እስከ 20 ዓመታት በማራዘሙ ሂደት የራሱና የሀገሩ የአሜሪካ እጅ እንዳለበት ያልተገነዘብን መስሎት ይሆን?

አምባሳደሩ እየዋሸን ነው!

ምንጭ፦
1. New and Old Wars, Third Edition MARY KALDOR, 2012

2. David Keen, ‘When war itself is privatized’, Times Literary Supplement (December 1995).

3. Mark Duffi eld, ‘Post-modern confl ict: warlords, postadjustment states and private protection’, Journal of Civil Wars (April 1998);

4. Chris Hables Gray, Post-Modern War: The New Politics of Conf l icts, London and New York: Routledge, 1997.

5. Frank Hoffman, Confl ict in the 21st Century: The Rise of Hybrid Wars, Potomac Institute for Policy Studies, 2011. John Mueller, The Remnants of W

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top