Connect with us

“ልባችንን ሰፋ እናድርግ?!”

Social media

ነፃ ሃሳብ

“ልባችንን ሰፋ እናድርግ?!”

“ልባችንን ሰፋ እናድርግ?!”

(ዶ/ር አበበ ሀረገወይን)

የህይወትን ጣእምና ያምላክ ቸርነትን በደምብ የሚያውቅ እንደኔ ከሞት አፋፍ ይተርፋል ሳይባል የተረፈ ነው።

ተርፌያለሁ ግን የዱሮ ጉልበቴ የለም። ትንሽ ጥረት ያደክመኛል። የጀርባና የጡንቻ ህመም አድብቶ ያጠቃኛል። ነገር ግን አእምሮዬ በብርሀን ፣ ልቤ በፍቅርና በሰላም የተሞሉ በመሆናቸው ለተሰጠኝ እያንዳንዷ እስትንፋስ ተመስገን አምላኬ እላለሁ። ተመስገን አጭሬ የዘላለም ጸሎቴ ናት። በፊት በልማድ ነበር የምላት። አሁን ግን የምትወጣው ከልቤ ከመሀሏ ነው። በሽታ አንዳንዱን ይሰብረዋል። እኔን ግን አበርትቶኛል።

በሙሉ ጤና ያለ ሰው መብቱ ይመስለዋል። አውቀዋለሁ። ለኔም እንደሱ ነበር። ነገር ግን ባልታሰበ ጊዜና ሰአት እልም ብሎ ሊጠፋ ይችላል። ዋናው ነገር ግን ለማንኛውም ክፉ ለሚደርስብን ነገር ተጠንቅቀንና ደግሰን መቆየት አለብን። ምንም ብሆን ምንም እቋቋመዋለሁ ብለን በጤና ሳለን ራሳችንን ለክፉ ቀን ማዘጋጀት አለብን። ክፉ ቀን ብዙ ጊዜ ድንገተኛ ነው። ድንገት ከተፍ ይላል።

የምንመክተው ግን በጥንካሬ መሆን አለበት። በመልካምነትና በትህትና መሆን አለበት። እነዚህ ደሞ ለራሳችን መጀመሪያውኑ ፍቅርና ክብር ካለን አይቸግሩንም። ሌላ ማወቅ ያለብን ነገር ደሞ ባካባቢያችንም በሩቅም ያሉ ወዳጅ ዘመዶች የራሳቸው ትግል አላቸው። በምንም ምክንያት አንኮንናቸው። ለነሱ ብቻ ብለን ሳይሆን እንዲህ አይነቱ አመለካከት ከጥላቻ ነጻ ያደርገናል።

ልባችንንም ሰፋ አድርገን ለማንኛውም የሰው ልጅ ፍቅር ይኑረን። በማንኛውም የጥላቻ ትርክት አንሸነፍ። ስለፍቅር ከሚያስተምረው ይልቅ አሳማኝ የጥላቻው እባብ መርዙን በማር ሸፍኖ አሳማኝ ይመስለናል። እናዳምጥ ነገር ግን ውሳኔያችን ሳንቸኩል የራሳችን ይሁን።

ይህችን አለምኮ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ጥለናት እንሄዳለን። ሀላፊነታችን ግን በተቻለን መጠን ፍቅርና ሰላም ያላን አለም ትተን ለመሄድ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ አለብን። አምላክም ይረዳናል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top