Connect with us

ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል ትግራይ ወደ መገንጠል የተሻገረው የወራሪው ቅዠት

ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል ትግራይ ወደ መገንጠል የተሻገረው የወራሪው ቅዠት፤ ቤተ መንግሥት ሆናችሁ ያላሳካችሁት ትግራይን መገንጠል ኮንቲነር ቤት መታሰቡም ቅዠት ነው!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል ትግራይ ወደ መገንጠል የተሻገረው የወራሪው ቅዠት

ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል ትግራይ ወደ መገንጠል የተሻገረው የወራሪው ቅዠት፤ ቤተ መንግሥት ሆናችሁ ያላሳካችሁት ትግራይን መገንጠል ኮንቲነር ቤት መታሰቡም ቅዠት ነው!

(ስናፍቅሽ አዲስ – ድሬቲዩብ)

ወራሪው አዲስ የቅዠት ነጠላ ዜማ ሰርቷል፡፡ ኢትዮጵያን እበትናለሁ ብሎ አንዱን ካንዱ እሳትና ጭድ ለማድረግ ከበርሃ እስከ ከከተማ ደክሞ ነበር፡፡ በላቡ ሀገር ማፍረስ የፈለገው ብቸኛው የዓለም አማጺ አፈርሳለሁ ብሎ የሸረበው ሴራ ሁሉ ሀገር አንድ አድርጎ አረፈበትና ደግሞ ሌላ ቅዠት ውስጥ ገባ፡፡

ወያኔ እንደ ዘራችው የዘር ፖለቲካ፣ ጥላቻ፣ አለመተማመንና ሀገር መጥላት ቢሆን ኖሮ እንደ ቅዠቷ የልጅ ልጇ ድረስ ሀገር እያባለች ዘርፍ በበላች ነበር፤ አልተሳካም ሁሉም ከሸፈ እሳትና ጭድ ያሉት ህዝብ አብሮ ቆሞ ሀገር አዳነ፡፡

አጋር ብለው ያሳነሷቸው የወደብ ደጃፍ የገነት በር እስኪሆኑባቸው ድረስ ለበለቧቸው፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተመልካች የነበሩት ህዝቦች ሀገር መሪና ዘዋሪ ሆኑ፤ ከሱማሌ መሪ ጋር ሰርቆ የመካፈል ባህል ማሳደግ የሚፈልጉት ወያኔዎች ከእነሱ መርዝ ሀሳብ ኢትዮጵያን የሚታደግ የሱማሌ መሪ በቁማቸው አዩ፡፡ አፋርን ጨውን እየዛቁ፣ በጀቱን እያፈሱ ሞግዚት ሆነው እንዳልረገጡት ከቅዠታቸው ኢትዮጵያን የታደገ ሃያል ሃይል ሆኖ ተመለከቱት፡፡

ለዚህ ነው አሁን ባለው ሁኔታ የወያኔ ቅዠት ቦታ የሌለው፤ ወያኔ ተስፋ ቆርጣለች፡፡ አድናችኋለሁ ብላ የምታታልላቸው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ዛሬ እሷ የምታስባቸው ዓይነት ልፍስፍስ መሪዎች የላቸውም፡፡ ሀገር የሚታደጉ ጀግኖች ከዳር ዳር ወያኔን አጥፍቶ ኢትዮጵያን ለማቆም ሲጸኑ፤

ለጋምቤላ ላልቅስ፣ ለቤኒሻንጉል ልሙት ለአፋር ልሰቀል የሚለው ድራማውን አስቀምጣ በአደባባይ ስለ ሪፈረንደም ማውራት ጀምራለች፡፡ ቤተመንግስት ሆነው ያልቻሉት ትግራይን መገንጠል ኮንቲነር ቤት ሆነው ቢቃዡት ይሄም ቅዠት ሆኖ ይቀራል፡፡

የትግራይ ህዝብ በዲያስፖራው ጩኸትና በወያኔ እኔ ዞር ካልኩ ሌላው ይበልሃል ስሜት ሲፈተን ኖሯል፡፡ ታምሶ ተሰቃይቷል፡፡ ከምርኮኛ ልጆቹ የምንሰማው እውነት ሳይዘምቱ መኖር የማይቻልባትን ትግራይ እነ ጌታቸው ረዳ መፍጠራቸውን ነው፡፡

ይሄ ሁሉ ያከትማል፡፡ ከግብጽ ቢጋቡም፣ ከአሜሪካ ቢሻረኩም፣ ከሱዳን ሴራ ቢነድፉም ሁሉም ከሟች ጋር አይኖርም፤ አሁን ኢትዮጵያን ፈልገው ወደ ትህነግ ጎራ የመጡ ትህነግ ድርሻዬን ይዤ ዞር ልበል በሚለው የሪፈረንደም አቋሟ ብቻ ጀርባቸውን እንደሚሰጧት ጥርጥር የለኝም፡፡

የግብጽ ድጋፍና አይዞአችሁ ባይነት ግድቡን ለመያዝ እንጂ ከሽሬ ሜዳዎችም ሆነ ከአድዋ ተራሮች ወይም ከወርኢ በርሃ ጉዳይ ኖሯት አይደለም፡፡ እናም አዲሱ የሪፈረንደም ዜማ የህወሃት መንገድ የት መድረሱን እያሳየን ነው፡፡

ኢትዮጵያን ሲዖል ድረስ ወርጄ አጠፋታለሁ ያለ ቡድን ያ ቢያቅተው እሺ ከኢትዮጵያ ላይ ድርሻዬን ማለት ጀምሯል፡፡ አሁን ጥያቄው ድርሻ አለው ወይ? ወራሪው በኢትዮጵያ ድርሻ የለውም፤ ይልቁንም ኢትዮጵያ ያላወራረደችው የታረደችበት፣ የተካደችበት፣ የተዘረፈችበትና የተገደለችበት ብዙ ሀቅ ወራሪው ጋር አላት፡፡ ቀስ እያሉ ማመን አሁን ሪፈረንደም የምትል ቅዠት ጋር ደርሷል፤ ቀጥሎ የሚሆነውን የቅዠት ምዕራፍ አብረን እናያለን፡፡

ኢትዮጵያ ግን ትኖራለች፡፡

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top