Connect with us

ጸረ-ሰላምና ጸረ-ህዝብ ቡድን!!

ጸረ-ሰላምና ጸረ-ህዝብ ቡድን!!
ነቢዩ ስሑልሚካኤል

ነፃ ሃሳብ

ጸረ-ሰላምና ጸረ-ህዝብ ቡድን!!

ጸረ-ሰላምና ጸረ-ህዝብ ቡድን!!

(ነቢዩ ስሑልሚካኤል)

ለአገርና ለህዝብ ያለን ተቆርቋሪነት እኛ እንደ ግለሰብ ወይም እንደ ቡድን ሲበርደንና ሲሞቀን የሚቀያየር ነገር አይደለም፤

ይህ ሃሳብ ማንሳት የፈለኩት በቅርቡ የህወሓት የሽብር ቡዱን በሰሙኑ ያሰራጨው የአልደራደርም ቀረርቶ ነው፤ ይህ ማንም በወግ ሳይጠይቀው ያሰማው ቀረርቶ የቡዱኑ አላማ መጀምርያዉኑም አገር የመውረርና የህዝብ ሰላም የማደፍረስ እንደነበረ ላንድ ተጨማሪ ግዜ ግልጽ አድርጎልናል፡፡

በተለይ ጉዳዩ ከትግራይ ህዝብ አንጻር ሲታይ በዚህ ቡዱን የብቃትና የኃላፊነት መጓደል ምክንያት ህዝባችን በአስከፊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ በገባበት በዚህ አስቸጋሪ ግዜ አላስፈላጊውና አሰቃቂው የርስ-በርስ ጦርነቱ መቋጫ እንዳያገኝና ህዝብ ወደ መደበኛው ህይወቱ በፍጥነት እንዳይመለስ መፈለጉ ምን ያክል ብስለት፣ አቅምና ኃላፊነት የጎደለው እንዲሁም ለትግራይ ህዝብ ደህንነትና መጻኢ-ተስፋ ደንታ-ቢስ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡

ይህ ጽንፈኛ ቡድን ጦርነቱ እያስፋፋ ያለበት ምክንያት ሲገልጽ ‘ትግራይን ከከበባ ለማላቀቅ ነው’ ቢልም ቅሉ ቡድኑ ከበባ ብሎ በገለጸዉን ችግር ሳይሆን ከዛ በላይ በተለጠጠ የወራሪነት ጀብድ ውስጥ ለመዋኘት እየሞከረ ይገኛል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ወደ ባህሩ ማእከላይ ክፍል ሲገፋ ምን ያክል ትልቅ አደጋ እየጠበቀው እንደሆነ አሁንም የገባው አይመስልም፡፡ በተለይ ከዚህ በኋላ እንኳንስ ኢትዮጵያ ትግራይም በቅጡ ማስተዳደር የማይችል መሆኑ በገሃድ እየታወቀ በዚህ ደረጃ መፍጨርጨሩ ለመላላጥና ሞቱን ለማፋጠን ካልሆነ በስተቀር ሌላ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡

ከዚህም በላይ የሰላምና የድርድር አማራጭ እሱ ሲበርደው የሚናፍቀው ሲሞቀው ደግሞ የሚያጥላላው ሆኖ መገኘቱ የቡድኑ የሞራል ሚዛንና የቅንነት/integrity መጠን እጅግ የላሸቀ መሆኑ በግልጽ ያመላክታል፡፡ አንዳንድ ጽንፈኛና ቁንጽል ደጋፊዎቹም ቢሆኑ ሲመቻቸው ግፋ-በልውን ሲከፋቸው ደግሞ እሪታን ከማሰማት መቆጠብ ይገባቸዋል፡፡ ካልሆነ ነገርየው ለሰዋዊም ለህዝባዊም ለአገራዊም ግብርና ፍላጎት የማይመጥን ተራ የጅሎች ጨዋታ ይሆናል፡፡

በዚህ መሰረት ቡዱኑ የብልሃት፣ የኃላፊነትና የሞራል መሰረት የሌለው ለማንኛውም ህዝባዊ ኃላፊነትና ተልእኮ የማይመጥን ጸረ-ሰላምና ጸረ-ህዝብ ቡዱን መሆኑ ማረጋገጫ እየሰጠ በመሆኑ ለተፈጥሮውና ለከፋው ወቅታዊ ቁመናው የሚመጥን እርምጃ ተወስዶበት ሊማርና ሊቀጣ ይገባል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top