Connect with us

ኦሮሞ አማራ ሌላም ብሔር አትበል የጠረጠርከውን ተከታተል፣

ኦሮሞ አማራ ሌላም ብሔር አትበል የጠረጠርከውን ተከታተል፣ ጠቁም ትህነግ ዘርና ቋንቋ ሳይገድበው ለሆዱ የሚኖርን ይገዛልና!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ኦሮሞ አማራ ሌላም ብሔር አትበል የጠረጠርከውን ተከታተል፣

ኦሮሞ አማራ ሌላም ብሔር አትበል የጠረጠርከውን ተከታተል፣ ጠቁም ትህነግ ዘርና ቋንቋ ሳይገድበው ለሆዱ የሚኖርን ይገዛልና!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

ሀገር የሚድነው በዜጋው ነው፡፡ ዜጋ መኖር የሚችለው ሀገር ስትኖር ነው፤ እንዲህ ኢትዮጵያን መቀመቅ ዜጎቿን ለመከራ የሚዳርግ ችግር ተጋፍጠናል፡፡ ይሉኝታና ችላ ባይነት የእያንዳንዳችንን ቤት ያፈርሰዋል፡፡ የእያንዳንዳችንን ህይወት ይጠይቀናል፡፡

አሁን እንደ 1983 መንግስት መሆን የፈለገ አማጺ አይደለም እየመጣ ያለው፤ አሁን ወጣት እየጨፈጨፈ፣ መጋዘን እየሰበረ፣ ሱቅ እያወደመ፣ ጤና ተቋም እያፈረሰ፣ ትምህርት ቤት እየገነጠለ ሀገር የሚበትን መንጋ ነው፡፡

መንግስት አካባቢያችሁን በንቃት ጠብቁ ብሏል፡፡ አካባቢን በንቃት መጠበቅ ከቤተሰብ ይጀምራል፤ ወዳጅ ዘመድ አይልም፤ ጓደኛ ከሀገር አይበልጥም፡፡ እነሱ ጋር እኩይ አላማ ከትዳርም ከማኅበራዊ ህይወትም የበለየ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ሀገር ማዳንና ለሀገርና ለህዝብ ዘብ መቆም ከዚህ የሚበልጥ ቅዱስ ተግባር ነው፡፡

ዓይኖቻችንን ከምንጠረጥራቸው ላይ ሁሉ አንንቀል፤ አማራ ነው ኦሮሞ ነው ወይም ሌላ ብሔር ነው ብለን መዘናጋት የለብንም፡፡ እንዲህ ያሉ የማንገምታቸው ሰዎች ሀገር አስበልተዋል፡፡ የምንጠረጥረውን ሁሉ እንከታተለው፤ የተለየ ነገር ካየን ከጸጥታ አካላት እንጠቁም፡፡

ትህነግ ዘርና ቋንቋ ምኗም አይደለም፤ እሷ ዓላማዋን ከተቀበለ ለሆዱ ያደረውን ሁሉ ለጥፋት ትገዛለች፡፡ ትናንትም ዛሬም ነገም ከምትንቀው ኦነግ ሸኔ ጋር እንኳን ጋብቻ ለመፈጸም አልቀፈፋትም፤

ሰሞኑን አንድ የጁንታው ኮለኔል ተማርኮ የሰጠውን ቃል ሰማሁ ሰውዬው መንጋው ምን ያህል አደጋ እያደረሰ መምጣቱን በደንብ በሚያሳይ መልኩ ገልጾታል፡፡ ይሄንን ሃይል ጥይት ታጥቆ ከሚያግዘው በላይ መንደር ለመንደር ጀግንነቱን እየሰመከረ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ህዝብ የሚያሸብረው ሰራዊቱ ይበልጣል፡፡

ይሄንን ሃይል ጥይት በግንባሬ ብሎ አብሮት ከዘመተው በላይ በገንዘብ የሚደግፈው የከተማ ጀሌ ይበልጣል፡፡ ይሄን ሀገር አጠፋለሁ ብሎ አሰፍስፎ የኢትዮጵያን ከተሞች ዶግ አመድ ለማድረግ የቋመጠ ቡድን ከነቅዠቱ እንዲመክን ሁላችንም መንግስት፣ ሁላችንም የፀጥታ አካል ሁላችንም ተቆርቋሪ መሆን አለብን፡፡

አጠገባችን ቢኖር፣ አበልጃችን ቢሆን፣ ስጋ ዝምድናው ቢልቅ ከሀገር የሚበልጥ ስለሌለ በጥንቃቄ ተመልክተን፣ ተከታትለን የተለየ ነገር ካለ ለጸጥታ አካላት በመጠቆም ሀገር ማዳን ድርሻችን ነው፡፡

አሁን በሀገር ደህንነት ጉዳይ ንቁ መሆንና መሳተፍ ፖለቲካ አይደለም፡፡ ህልውና የሚለው ቃል የሚያንሰው የመኖር ያለመኖር አጀንዳ ነው፡፡ ጉዳይ ለእነ እከሌ የሚተው አይደለም፡፡ ለፖለቲከኞችና ለሹመኞች የሚጣል ነው ብሎ ማመን መውደቅ ነው፡፡ የገጠመንን ፈተና ማለፍ የምንችለው ሁላችንም አብረን ቆመን፣ አብረን ነቅተን አብረን ሀገር ስንታደግ ነው፡፡

ሌላው ቀላል ነው፡፡ ይሄ ቡድን መንግስት ነበር፤ ደህንነቱ በእጁ ሆኖ ባንኩን እያዘዘበት፣ ቀይ ለባሽ ገዳይ ወታደር ከተማ እየበተነ ታንክ በአደባባይ እየተኮሰ እውነት አላሸነፈም፡፡ ውሸቱና ሀገር ጠልነቱ ከቤተ መንግስትና ከቅንጡ ህይወት ወደ ዋሻ፣ ከአንገት ሀብል ወደ አንገት ላይ ሽርጥ ጠምጣሚነት የተቀየረ ነው፡፡

አሁንም ኢትዮጵያን ለሚያክል ሀገር የሚከብድ ነገር ምንም የለም ይሄ ሁሉ እንደ ጉም ብን ብሎ ይጠፋል፤ ግን የኢትዮጵያውያንን አንድነት አብሮነትና እኩል ንቃት ይፈልጋል፡፡ አካባቢን መጠበቅ፣ መዝመት፣ መከላከያን መደገፍ፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top