Connect with us

ሁሉን ትተው ሀገር ሊያፈርሱ ነው፤ ሁሉን ትተን ሀገር እናድናለን!!

ሁሉን ትተው ሀገር ሊያፈርሱ ነው፤ ሁሉን ትተን ሀገር እናድናለን!!

ነፃ ሃሳብ

ሁሉን ትተው ሀገር ሊያፈርሱ ነው፤ ሁሉን ትተን ሀገር እናድናለን!!

ሁሉን ትተው ሀገር ሊያፈርሱ ነው፤ ሁሉን ትተን ሀገር እናድናለን!!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

ሁሉን የተውት ኢትዮጵያ ከፈረሰች በኋላ ሁሉም ይደርሳል ብለው ነው፡፡ እኛ ደግሞ ሁሉን እያደረግን በትርፍ ሰዓት የምናደርገው ተግባር ይመስል ችላ ብለነዋል፡፡ ዛሬም የሙዚቃ ድግሶች፣ ዛሬም ዳንኪራዎች ዛሬም እግር ኳስና ጭፈራ አለ፡፡

አሁን የፌዴራሉ መንግስት ያቀረበው ጥሪና የአማራ ክልል ያወጀው አዋጅ እንደ እንደ እነሱ የኢትዮጵያም ሁሉ ነገር ኢትዮጵያን ካዳንን በኋላ የሚል ሆኗል፡፡ እነሱ ሁሉን ነገር አያስፈልገንም ብለው የህጻናት የእርዳታ ምግብ ሳይቀር ነጥቀው እየበሉ ኢትዮጵያ ስትጠፋ ይደርሳል ብለው ሀገር ለማጥፋት ዘምተዋል፤ እኛም ኢትዮጵያ ስትድን በሚል ሀገር ለማዳን ሆ ብለን መነሳት አለብን፡፡

ነገሮች ጥሩ ይሆናሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዶክተር አብይን ከፊት ያቆመው ትህነግን ጠልቶ ከገባችበት አብርሮ ነው፤ ዶክተር አብይ አይደለም ኢትዮጵያን ህዝብ ከትህነግ ያለያየው አስቀድሞም የነበረ ግፍ በደል መራር ጭንቅና መከራ ነው፡፡

አሁንም ትህነግ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ያላትን ቦታ ራሷም ታውቀዋለች፡፡ በየቀኑ የሚረግፈው የትግራይ ወጣት አያሳስብም እኔና ጻድቃን ብቻ ራሱ አዲስ አበባ ከገባን የሚል መንፈስ ያለው የጌታቸው ረዳና ጀሌዎቹ ግፋ በለው ሁሉን አጥተን ኢትዮጵያን እናፍርስ ከሚል የመጣ መሆኑን አይተናል፡፡

ትልልቆቹን የዓለም ሚዲያዎች ሳይቀር እነሱን ሊዋጋ የወጣ የኢትዮጵያን ልጅ ፎቶ የትህነግ ሃይል ነው ብለው ሲያሳስቷቸው በቀላሉ የማናውቀውን እንዴት እንደሚዋሹ መገመት ነው፡፡ ፎቶዋ የተሰረቀባት ልጅ ምርር ብላ ታሪክ ተሰረቀ፣ ተራራ ተሰረቀ፣ መርከብ ተሰረቀ፣ ሀገር ተሰረቀ እንዴት የኔ ፎቶም ይሰረቃል ብላ ጠይቃለች፡፡

አሁን የአማራ ክልል በአስቸኳይ ኮማንድ ስር እንዲውል ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ ሀብትም ንብረትም ህይወትም ለዚህ ቅዱስ ዓላማ እንዲውል ጥሪ ቀርቧል፡፡ ይሄ ፍጻሜው ነው፡፡ እስከአሁን ትውልድ ጨረስው ከተማ ያዝን ይላሉ፡፡ 

ሰሞኑን ደጋፊዎቻቸውን ደሴን ያዝን ብለው አስጨፍረው እንደውም ደሴን ትተናት ኮምቦልቻ ገብተናል አይነት ድራማ ቀጥለዋል፡፡ የትም ይዋጋሉ እንጂ የትም አልያዙም፡፡ በተቃራኒው ጠንካራው የኢትዮጵያ ሃይል ጎዳናቸውን ዘግቶታል፤ ወሳኝ የሎጀስቲክስ አንገታቸው ታንቋል፡፡

ሁሉን ትተን ሲዖል ወርደን ኢትዮጵያን እናጠፋለን ለሚሉት አሁን መንግስት የሰጠው ምላሽ ጥሩ ነው፡፡ ሁሉን ትተን ከሞት ጋር ተጋፍጠን ኢትዮጵያን እናድናታለን፡፡ የቱ ግቡን እንደሚመታ ይታያል፡፡ ያኔ ምናልባትም የኢትዮጵያ ጠላቶች ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን አንነካም የሚሉበት ዘመን ምክንያት የሚሆን የመጨረሻ ፍልሚያ ይሆናል፡፡

የፎቶ መነሳት ጦርነቱ እድሜው አጭር ነው፡፡ ግርግር ይፈጥራል በውስጥ አርበኛ ወገን እንዲታመስ ያደርጋል ከዚያ ይከስማል፡፡ ደብረ ታቦርና ደባርቅ የሆነው ይህ ነው ውጤቱን ግን እነሱም እኛም ዓለምም ያውቀዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ሰው ባለው ነገር ሁሉ ሀገሩን ያድናል፡፡ ሀገር ትድን ዘንድ ሁሉም ሁሉን ነገር ይሰጣል፡፡ ህዝባዊ ማዕበሉን በጥሪው ዋዜማ አይተነዋል፡፡ ነገ ከነገ ወዲያ የሚሆነውን እናያለን፡፡ አንድ ነገር ግን እርግጠኞች ነን፡፡ ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ናት፡፡ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top