Connect with us

ዶክትሬታቸውን መግፈፍ ይቻል ይሆን?

ዶክትሬታቸውን መግፈፍ ይቻል ይሆን?
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ዶክትሬታቸውን መግፈፍ ይቻል ይሆን?

ዶክትሬታቸውን መግፈፍ ይቻል ይሆን?

(ኦሃድ ቤንአሚ)

~ ከplagiarism የከፋ አሳፋሪ እና ሙያዊ ስነምግባሩን ለፖለቲካዊ ትርፍ የሸጠ ሽቀላ!

ቴድሮስ አድሓኖምን ከአምስት አመታት በፊት ለአለም የጤና ድርጅት ሲወዳደሩ ደግፌያቸው ነበር፤ በዚህ የጦርነት ወቅት ግን የያዙት አቋም ግን በመደገፌ ባልጸጸትም እንደገና እንዳያቸው አድርጎኛል፤ እሳቸው እዛ ጄኒቫ ተቀምጠው በኢትዮጵያ ላይ እቀባ ሲዶለት አንዲት ነገር ተናግረው ቢሆን ኖሮ ስንት ነገር በተለወጠ ነበር፤ ነገር ግን ኃያላኑ መንግሰታት በድሃይቱ አገር ላይ እቀባ እያሉ ሲያሟርቱ አንዲት ነገር መተንፈስ አልቻሉም፤ ያችን እንኳን ማድረግ አልቻሉም፤ ይህ ደግሞ ጦርነት እና ድህነት ፈተና በሆኑባት አገር ውስጥ ባሉ ዜጎቿ ላይ እሳቸውም አብረው ሲፈርዱ እና ለጎሰኛ አሸባሪ ድጋፋቸውን ሲያስተጋቡ ስሰማ በጣም አዝኛለሁ፤

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ሙያ ምን ማድረግ እንደነበረባቸው በግልጽ ያስቀመጠው ሙያዊ ግዴታ ነበር፤ ግን ቴድሮስ አድሃም ምንም ማድረግ አልቻሉም፤ አገሬ የወገን ያለህ እያለች ትጮህ ነበር፤ ዲፕሎማሲያዊ ክንዶቿ በዛሉበት ወቀት ቴድሮስ ከጠላቶቿ ጎን ቀመው ወግተዋታል፤ ያማል፤

ከተሾሙ በኋላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቀት “አድበሰበሱት” የተባለውን ለአልሸባብ መሳሪያ መሸጥን አስመልክቶ በሳቸው ዙሪያ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ያወጡት ዘገባ እንደገና እንዳስብ አድርጎኛል፤

አሁን ግን ቴድሮስ አድሃኖም እያደረጉ ባለው እንቅስቃሴ ዶክትሬታቸውን መግፈፍ ቢቻል ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ምክንያቱም ህይወት ለማትረፍ የተሰጣቸው ካባ የማይካድራን፣ የመከላከያን እና የአፋር ንጹሃን ዜጎቻችን ላይ እልቂት ያወጁትን አሸባሪዎች እና ነፍሰገዳዮቹን ለማገልገል ተጠቅመውበታልና፤

ዶክትሬት ዲግሪዎች የሚሻሩባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ፤ አንዱ ከplagiarism ወይም ቅጂ ጽሁፎችን ገልብጦ የራስ አስመስሎ በመጻፍ ነው፤ ቴድሮስ አድሓኖም ያደረጉት ከplagiarism የከፋ አሳፋሪ እና ሙያዊ ስነምግባሩን ለፖለቲካዊ ትርፍ የሸጠ ሽቀላ ስለሆነ ነው፡፡

ለእውነት እና ለሃገራቸው መቆም ያቃታቸውን “ምሁር” እንዴት መደገፍ ይቻላል?

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top