Connect with us

ለፋኖ ለመቆርቆር ፋኖን አታሳንሱት፤

ለፋኖ ለመቆርቆር ፋኖን አታሳንሱት፤
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ለፋኖ ለመቆርቆር ፋኖን አታሳንሱት፤

ለፋኖ ለመቆርቆር ፋኖን አታሳንሱት፤

እውነተኛው ፋኖ ከመከላከያና ከመንግሥት የጸጥታ ጎን ቆሞ ለእናትሀገር ጥሪው እየተፋለመ ያለ፤ የሚታወቅ ሀገር ወዳድ ኃይል ነው! 

(ስናፍቅሽ አዲስ -ድሬቲዩብ)

ፋኖ ድብቅ አላማ የለውም፤ እዚህ መንደር ለፋኖ ተቆርቋሪ በመምስል ፋኖን ከየመንደሩ አውደልዳይ ጋር አብሮ እኩል የሚመለከት ስራ ፈት በዝቷል፡፡ ፋኖ ህይወት አለው ኑሮ አለው አሁን የሀገሩን ጥሪ ሰምቶ ለእናት ሀገሩ ሆ ብሎ የወጣ ህዝባዊ ሠራዊት ነው፡፡

መንግስት የማያውቀው መንግስት የማያከብረው እውነተኛ ፋኖ የለም፡፡ የፋኖ ሃይል ከመንግስት የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት የሚሰራ ነው፡፡ ከመከላከያ ጋር ተናቦ ተቀናጅቶ እየተፋለ መሆኑን ግንባር ጠጋ ያለ የሚያውቀው እውነት ነው፡፡

በተቃራኒው በፋኖ ስም ከመንደሩ ሳይወጣ ኪሱን ማደለብ ስሙን ማግነን የሚፈልግ ሃይል አለ፡፡ ይሄ ሃይል መንግስት ከአሁን አሁን ደረሰብኝ በሚል የሰቀቀን ኑሮ የሚኖር ወሮ በላ ነው፡፡ በወገን ሞት የሚነግድ በሀገር መደፈር ሌላ ሴራ የሚጎነጉን ነው፡፡

ማኅበራዊ ሚዲያ የሚጠቀሙ አንዳንድ ፋኖዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን ክብር አድናቆትና ፍቅር ሲገልጹ አይተናል፡፡ በሌላ በኩል ፋኖ ነን በሚል ስም ራሳቸውን የሚጠሩ ግን ደግሞ በህዝብና በመከላከያ መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር ህዝባዊ ሰራዊቱ እንደተካደ በማቀንቀን መርዝ የሚረጩ አሉ፡፡

ምንም እንኳን የባለስልጣኑ የፌስ ቡክ ገጽ ባይሆንም አቶ ብናልፍ አንዷለም አሉት ተብሎ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ የታየው መልእክት በራሱ ችግር አልነበረበትም፡፡ ጸሐፊው ማንም ይሁን ማን ሀሳቡ ግን እውነተኛን ፋኖ ክብር የሚሰጥና በፋኖ ስም የሚነግደውን የሚያስጠነቅቅ ነው፡፡

በጎንደርም በወሎም በብዙ የጎጃም አካባቢዎችም ህዝቡ የዘመተው በጸጥታ መዋቅር እዝ ነው፡፡ እንዲህ ባለ ኮማንድና የተናበበ ህብረት በሚፈልግ ወቅት የፈለገ ቡድን እንደፈገለገ ይሁን የሚል መርህ ሀገር ለማዳን ከታሰበ መንፈስ የፈለቀ አይደለም፡፡

ፋኖ በትብብርና በአንድነት የሚያምን ሃይል ነው፡፡ መንግስትን ለመገዳደር ሳይሆን ቀድሞ ሞቶ የጸና ሀገራዊ ክብር እንዲኖር የመንግስትን ክተት ተቀብሎ የዘመተ ነው፡፡ ይሄንን ሃይል ለማንም ግለኛ በተላለፈ ስድብና መልእክት ልክ አስገብቶ መፈረጅ ልክ አይደለም፡፡

የማይታወቅ ፋኖ የለም በፋኖ ስም ለሚነግደው ደግሞ የፋኖን ጀብድ ወስዶ በመለጠፍ ለመሸፋፈን መሞከርም አይጠቅምም፡፡ ፋኖ ከተማ ከባለስልጣን ጋር እየተነታረከ ሳይሆን ግንባር ላይ ግንባሩን ሰጥቶ እየተዋደቀ ነው፡፡

አጀንዳ ለመፍጠርና ህዝባዊ አንድነቱን ለመሸርሸር እከሌ እንዲህ አለ ብሎ ዘመቻም አሁን ወቅቱ አይደለም፡፡ ቢያንስ እንደ ዲጂታል ወያኔው ባትጠነክሩ ዲጂታል ወያኔው የሚሰራውን ንቁ፡፡ ስንት ሀሰተኛ አካውንቶች ተከፍተዋል? ስንቱ በስንቱ ስም እየነገደ የቀረውን ሀገር የማፍረስ እቅድ በሶሻል ሚዲያው በኩል እየሞከረ ነው?

ይህ ከሀገሩ መከላከያ ጎን ቆሞ ቀድሞ እየሞተ ያለው ፋኖ የሚታወቅ መንግስት ክብር የሚሰጠው የመንግስትን ህግና ስርዓት የሚያከብር ቅድሚያ ሀገሬን ላድን ያለ ባለውለታ እንጂ ማንም የሚሸሸግበት ጥሻ አይደለምና ለፋኖ ለመቆርቆር ፋኖን አታሳንሱት፡፡

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top