Connect with us

ጦርነት ምርጫዬ ነው ያለው ትህነግ እዚህ ቦታ ገባን እያለ ዜና ያውጃል

ጦርነት ምርጫዬ ነው ያለው ትህነግ እዚህ ቦታ ገባን እያለ ዜና ያውጃል፡፡ አዎ ገባን ዜና ነው ገብቶ መቅረት ግን መርዶ።
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ጦርነት ምርጫዬ ነው ያለው ትህነግ እዚህ ቦታ ገባን እያለ ዜና ያውጃል

ጦርነት ምርጫዬ ነው ያለው ትህነግ እዚህ ቦታ ገባን እያለ ዜና ያውጃል፡፡ አዎ ገባን ዜና ነው ገብቶ መቅረት ግን መርዶ።

የገባው ካልወጣ የትግራይ ወጣቶች ዘመቻ ትርፉ ምንድን ነው?

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

ጌታቸው ረዳ እንኳን ለትግራይ ለአፍሪካ የሚተርፍ ቀልደኛ ነው፡፡ አሁን አድዋን ደበደቡብኝ፣ ትግራይ በቀን ይሄንን ያህል ጊዜ ተደበደበች እያለ ኡኡ የሚል ቡድን ኮምቦልቻ አይሮፕላን እንዳያርፍ አድርገናል የሚል ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ እንደመስማት የሚገርም ነገር የለም፡፡

ማፍቀርስ እንደ ትህነግ ደጋፊዎች መፈቀርም እንደ ህወሃት ትግራይ ላይ የጦርነት ተቋማቶቻቸው ሲደበደቡ ወፍ አያርፍም ብለው የፎከሩት ትህነጎች አፋቸው አርፎ ጨዋታውን ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ አድርገውት አረፉ፡፡

መቼም ጦርነት ለዓላማ ሲሆን ባይመረጥም ይሁን በተባለ፤ ጥቂት ሰዎች የውስኪ ጥም ሊገድላቸው ነው ብሎ እያንዳንዱን ቤት ልጅ መንጠቅ ምን የሚሉት ስካር ነው? በየጊዜው እዚህ ገባ እዚህ ደረሰ የሚባለውና ራሱን የትግራይ ሰራዊት ነኝ የሚለው ወራሪ ገብቶ በገባበት ከቀረስ ድልስ ትግልስ ለምን ዓላማ?

አስቀድሞ ጦርነቱ ልክ ያልነበረና ዓላማ ቢስ ነው፡፡ ጭቆናና በደልን እንቢ ብሎ መዋጋት የአባት ነው፡፡ ህዝብን ለይቶ ጠላቴ ነውና ላጥፋው ብሎ እንደመነሳት ቀድሞውኑ ዓላማቢስነት የለም፡፡

መቼም ምንም ቢሆን ትህነግ አዲስ አበባ ገብታ ስልጣን ይዛ ሀገር እንደማትመራ ሌላው ባይታመን እንኳን የራሷ ልብ እውነቱን ይነግራታል፡፡ ይሄንን ሁሉ ወጣት እንደ ቀጥል እንዲረግፍ ማድረጉ ፋይዳውን የሚጠየቅና ለምን የሚል ግን አንድም የለም፤

ትናንት ህግ ማስከበር ዘመቻ እንደሆነ እያወቀ አለም በገዛ ሀገሩና ግዛቱ የኢትዮጵያን መንግስት ትግራይ ገብቶ ሰው ጨረሰ በሚል ሲኮንን ነበር አስገራሚው ነገር ግን የትህነግ መሪዎች ለወዳጆቻቸው የማይመች ውሳኔ ወስነው አማራና አፋርን ወረሩ፣ በአማራና በአፋር በአየር ሳይቀር እምሽክ ሲሉ አለም ጦርነቱ ይቁም አለ እንጂ እያንዳንዷን የትግራይን እናት ቤት የሚያጎድል ዘመቻ አልፎ ለመኮንነን አልተመቸውም፡፡

ማሸነፍ ምንድን ነው? እየመጡ ማለቅ፤ የሆነውስ ሆነና ከዚያ በኋላ ድርድርም ይምጣ ሰላም ይሄንን ሁሉ ወጣት አስጨርሶ ድል አድራጊው ማን ሊባል ነው? ይሄ ሞት አዛኝ እንኳን የለውም አማራና አፋርን ለመዝረፍ ገብቶ አለቀ የሚል በታሪክ ፊት ጭምር ጸያፍ ስም አገኘ እንጂ፡፡

መሪዎቹ የቀረባቸውን ቁጭት አንድ የእኛ ያሉትን ህዝብ ማግደውና አስጨፍጭፈው እድላቸውን እየሞከሩ ነው ያ ባይሆን እንኳን ቁጭታቸውን ለመወጣት ይፍጨረጨራሉ፡፡ ህዝብ ግን ዛሬም ያልቃል፡፡

በሌላ በኩል አብሮ በኖረው ህዝብ መካከል ከዛሬ የሚሸጋር ቂምና ጥላቻ እንዲተርፍ እየተሰራ ያለው ስራም ከመካከላቸው ተው ባይ የለም እንዴ ያስብላል፡፡ ሌላው ቢቀር የሚደረገው ነገር ቢያንስ ከእምነት ከእውነትና ከመርህ አንጻር ባይፈተሽ እንኳን ከጥቅምና ከዘላቂ ፋይዳ አኳያ እንኳን ምን ረብ አለው አይባልም?

አሁን አለም የትህነግ ሴራ በቅጡ እየገባው ነው፡፡ አውሮፓ ህብረትም ደግሶት የነበረውን ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ የመጣል ሴራ ያለ ስምምነት ትቶት ወጥቷል፡፡ አሜሪካም አዳዲስ ሀሳቦች ይዛ ታይታለች፡፡ ይሄ ሁሉ እየሆነም ጦርነት ምርጫዬ ነው ያለው ትህነግ እዚህ ቦታ ገባን እያለ ዜና ያውጃል፡፡ አዎ ገባን ዜና ነው ገብቶ መቅረት ግን መርዶ መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top