Connect with us

ጂጂ ባትወለድ ኖሮ፤

ጂጂ ባትወለድ ኖሮ፤
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ጂጂ ባትወለድ ኖሮ፤

ጂጂ ባትወለድ ኖሮ፤

(ሄኖክ ስዩም ድሬ ቲዩብ)

እንኳን ተወለደች፤

ጂጂ ባትወለድ ኖሮ ማን የአባቶቻችን አጥንት ተነስቶ አለማለቁን ስሙት ይለን ነበር፡፡ መቼ ተነሱና የወዳደቁት ያለችው እኮ እሷ ነች፡፡ መለወዷማ ደግ ነው፡፡ መወለዷማ ጥቅም ነው፡፡ አዊን አፍሪካ ሙዚቃ ማዕድ አኑራ ስሜት እናጣጥም ዘንድ ያደረገች እኮ ናት፡፡

ጂጂማ እንኳን ተወለደች፡፡ አንዳንዴ የምትናፍቀን ስለሌለች የሚመስለው አለ፤ ግን ስላለች ነው የምትናፍቀን ስለማትለየን፤ አብራን እንድትሆን ባሰገደደን ጥበቧ ምርኮኞች ነንና አብረን አለን፡፡ አቦ ሸማኔ እያልን ዜማ በአቦ ሸማኔ ፍጥነት እያለቀብን አብረን አለን፡፡

ጂጂ ባትወለድ ኖሮ

ፍቅር መራብ ዜማ ሆኖ አብረን ተርበን አብረን ባልዘመርን፡፡ እስከ መቼ እህህ ብለን የጠየቅነው ተወልዳ ጠይቃ አጠያይቃን መስሎኝ፡፡ ጂጂን እወዳታለሁ፡፡ እሷ የእነሱን ቤት ጨዋታ እንደናፈቀችው ሁሉ እኔም የሷን ውብ ጨዋታ የትም እሰማሁ ዘንድ እናፍቃለሁ፡፡

ጂጂ ሀገር ዘፍናለች፡፡ ጂጂ ለሀገር ዘፍናለች፡፡ ሀገር የሰሩ ከያኒያን ስማቸው ሲጠራ ከጥቂቶቹ አንዷ ሆናለች፡፡ ዛሬም በየዓመቱ ሀገር አድዋ ሲል በድምጽዋ ነው፡፡ አበው ሲዘከሩ በእሷ እንጉርጉሮ ነው፡፡ እንዲህ ያለች ጥበበኛ ልደቷ ሲሆን እንኳን ተወለደች እንላለን፡፡

ጎጃም ያረሰውን ለጎንደር ካልሸጠ…..

አብሮ መኖር ሰብካለች፡፡ ገጠር ናፍቃ ወገን በትዝታ ራሱን ተመልሶ ይመለከት ዘንድ ውበትና ህይወትን ናኝታለች፡፡ ዘፋኝ የሚለው ቃል ለክብሯ ቁምጣ ነው፡፡ እሷ ጥበበኛ ናት፡፡ እሷ ዜማና ቃል ናት፡፡

እንኳን ተወለደች፡፡

ሰው መሆን ክብርነትን በአድዋ ማፈር በቃጣው ዘመን ላይ ሆና ሰው ለሰው መሞቱን አውጃለች፡፡ ጂጂ እንደ መንግስትም ናት፤ የቀደሙት መንግስታት ያስከበሯት ሀገር መከበሯ አይነገር ሲባል ከቀደሙት መንግስታት ሀገር ተረክባ በዜማዋ ትውልድን ወደ ክብሩ የመራች፡፡

ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ በክብር መሄድን ያወጀችው፤ ሰው ሊኖር ሰው በሞተበት የተፈጠረ ትውልድ አድዋ ምኔ ነው ሲል ነበር፡፡ የተሰጣት ህይወት እንኳን ተወለድሽ ለማለት የሚያበቃ ሰው ህይወት የከፈለበት ነውና፤ በአባቶቻችን ገድል ትውልድ በማረከችበት ዜማ ሀገር በቀረጸችበት ቃል፡፡ የኮራሁ እኔ ጂጂማ እንኳን ተወለደች ብያለሁ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top