Connect with us

ዛሬ ዓለም የስደተኛ ወፍ ቀንን ያከብራል፤

ሄኖክ ስዩም

ነፃ ሃሳብ

ዛሬ ዓለም የስደተኛ ወፍ ቀንን ያከብራል፤

ዛሬ ዓለም የስደተኛ ወፍ ቀንን ያከብራል፤
ስለ ስደተኛ ሰው ክብር እያሰብን እናከብረዋለን

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)
ዓለም የፈረንጆቹ ኦክቶበር ወር በገባ ሁለተኛው ቅዳሜ የዓለም ስደተኛ ወፍ ቀንን ያከብራል፡፡ ዘንድሮም ቀኑን ዛሬ በዓለም ሀገራት ሁሉ “ዘምሩ ፣ ይብረሩ ፣ ከፍ ይበሉ – እንደ ወፍ!” በሚል መሪ ቃል ያከብረዋል፡፡
እርግጥ ነው ለወፍ የሚራራ ደጉ የሀገሬ ሰው ከቀዬው ተሰዶ ሜዳ በወደቀበት በዚህ ወቅት በእኔም ሀገር ቀኑ ታስቦ ይውላል፡፡

የፕላኔታችን ወፎች ከአንዱ ሥፍራ ወደ ሌላው በሚጓዙበት ጊዜ የመድረሻ ወቅታዊ የመኖሪያ ሥፍራቸው መጥፋት እና ሕገወጥ አደን እንዲሁም መርዝን ጨምሮ በኬሚካሎች ሳቢያ እየገጠማቸው ያለ የሞት ስጋት የከተሞች ዝማኔ የፈጠረው በመስታወት የተሸፈነ ሕንፃ ጦስ ግዙፍ ሃገር አቋራጭ የኤሌክትሪክ መስመሮች የሚተፉት እሳት ፈተናቸው ብዙ ነው፡፡

ዓለም ይሄንን ቀን ማክበር ሲፈልግም ይሄንን አበሳ ቆጥሮ የፕላኔታችን ወፎች በፕላኔታችን ያለ ስጋት እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል ነው፡፡ ነገሩ ከሰው ልጅ ጉዳይ ውጪ ይመስል እንጂ ከሰው የተቆራኘ ምስጢር ነው፡፡

ወፎች ሲፈልሱ ዓለምን ዳር ከዳር የሚያገናኝ ተግባር ይዘው ነው፡፡ ሰዎች ስለ ሌላው የዓለም ክፍል እንዲያውቁ ረድተዋል፡፡ አገሮችን እና ሥነ ምህዳሮችን አገናኝተዋል፡፡
ቀላሉ ማሳያ በአለማችን እና በኒው ዚላንድ መካከል እስከ 11,680 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ የሚበርሩትን እንደ Artic Tern እና Bar-tailed Godwit ያሉ እጅግ በጣም ብዙ ርቀቶችን የሚሸፍኑ ከዓለማችን 11,000 የአእዋፍ ዝርያዎች መካከል 2000 ያህል ይሰደዳሉ።

ሃሚንግበርድስ ትንሹ ተሰዳጅ ወፍ ናቸው። የስደታቸው መንገድ በሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይወስዳቸዋል። 600 ማይሎች ሊደርስ የሚችለውን ይህንን የአየር ጎዳና ያለማቋረጥ ይበርራሉ።

መጠናቸውን ለተመለከተ ደግሞ እንዴት ያለ ረጅም ጉዞ እንደ ተጓዙ ይረዳል፡፡
ስለ ስደተኛ ወፎች ሲነገር ብዙ ቀላል የሚመስሉ ጉዳዮች አሉ፤ እስከ 16,000 ማይል ድረስ እንደሚጓዙ ለሚያስብ ግን የመጨረሻ መድረሻቸው ጋር ለመድረስ እስከ 533 ሰዓታት ድረስ የሚበሩ ወፎች አሉ የሚለውን ለሚሰማ ግን ጉዳዩ ይከብድበታል፡፡

የአንዳንዶቹን ጉዞ ከባድ የሚያደርገው ደግሞ መንገዳቸው በከፍታ የሚፈጸም መሆኑ ነው፡፡ አንዳንድ ወፎች ከፍ ወዳለ ከፍታ ይሰደዳሉ ከ500 እስከ 2,000 ጫማ ከፍታ ላይ የሚጓዙ አሉ፡፡ ለምሳሌ እንደ Kaytee መረጃ ዝይዎች እና አሞራዎች ከ29,000-37,000 በሚደርስ ጫማ ከፍታ ላይ እንደሚጓዙ ይጠቁማል። አንዳንድ የሳይንስ ሊቃውንት ወፎች ከፍ ባለ ከፍታ ላይ የሚጓዙት ክንፎቻቸውን በማጠፍ እና በበለጠ መንሸራተት ኃይልን ለመቆጠብ እንደሆነ ያምናሉ።

ከዓለም አንድ ክፍል ወደሌላው የሚጓዙት ስደተኛ ወፎች በአስገራሚ ሁኔታ ደግሞ የት እንደሚሄዱ ጠንቅቀው የሚያውቁና መድረሻቸውን ተረድተው መንገድ የሚጀምሩ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች እነኚህን የስደተኛ ወፎች ተቀብለው አኑረው መልሰው የሚሸኙ እንደ ሀገር የመስህብ ጸጋዎቻችን ለመሆን የበቁ ናቸው፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top