Connect with us
#አትርሳ!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

#አትርሳ!

#አትርሳ!

(እሱባለው ካሳ)

ቢመችኸም ባይመችኸም እውነታው ይኸ ነው፡፡ ሰውየው ለዚህች ሀገር ፖለቲካ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ዋጋ ከከፈሉ ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው፡፡ እንደምታውቀው የሀብታም ልጅ ነው፡፡

 የሚበላው፣ የሚጠጣው…አስፈላጊ ከኾነም የሚቀብጥበት ዕድሉንም፣ ሳንቲሙንም አላጣም፡፡ እንደአንዳንዶች ፖለቲካውን  ተንጠላጥሎ ሥልጣን ለመያዝ፣ ቤትና መኪና ለመቀየር፣ ለታይታ ብሎ አልገባበትም፡፡ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አራት አስርት ዓመታትን ሲዳክር በውስጡ ትልቅ ተስፋን አርግዞ ነበር፡፡ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ማየት ይናፍቅ ነበር፡፡  

በውስጡ” ይኸቺ ሀገር በእኔና በጓዶቼ ትግል አንድ ቀን መከራዋ ያበቃል!” የሚል ጽኑ እምነት ነበረው፡፡ ይኸ እምነቱ በተሸረሸረበት ወቅት ደግሞ የሞቀ ኑሮውን፣ ሕይወቱን እና የሚሳሳለት ቤተሰቡን ትቶ ብረት ለማንሳት ያላመነታ ጀግናም ነበር፡፡ ለውጥን በመሻቱ፣ ስለኢትዮጵያ በመድከሙ ብቻ ከባድ ዋጋ ሲከፍል ኖሯል፡፡ ተገፍቷል፣ ታስሯል፣ በጠላትነት ተፈርጇል፣ ሀብት፣ ንብረቱን አጥቷል፣ የሚወደውን ሀገር ጥሎ ተሰዷል፣ በረሃ ለበረሃ ተንከራቷል፡፡

ይኸ ሰው ዛሬ የሚኒስትርነት ሹመት ቢያገኝ አይግረምህ?! ዓላማው ሀገሩን ወገኑን ማገልገል ስለሆነ እንጂ ከዚህም በላይ የሚገባው ሰው ነበር፡፡ ደግሞ ወያኔን ፊት ለፊት ገጥሞ፣ አሁን ለተገኘው ለውጥ ዋጋ ከከፈሉ ኢትዮጵያውያን ግንባር ቀደሙ እንደነበረም አትርሳ፡፡ ዛሬ ትልቁ ቁምነገር የእሱ የሚኒስትርነት ቦታ ማግኘቱ አይደለም፡፡ 

ይኸንማ ቀድሞም ወያኔ ጉያ ስር ተወሽቆ ቢሆን ኖሮ ባላጣው ነበር፡፡ ቁምነገሩ የአሳታፊ፣ የአርቆ አሳቢ፣ በልዩነት ውስጥ አንድነትን ፈላጊ…ሥርዓት አካል መሆኑ ነው፡፡ ይኸን ሥርዓትን አዋልዶ በማሳደግ ረገድ ያለበትን የዜግነት ኃላፊነት እነሆ አምኖበት ተረክቧል፡፡ መቼስ ምን ይባላል?!

ይቅናሃ!.. የእኔ ጀግና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ቦንገር!!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top