Connect with us

ለእናት ሀገራችሁ ቀኑን በግንባር እያሳለፋችሁ ላላችሁ የኦሮሚያ ልጆች እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ!!

Ethiopian news agency

ነፃ ሃሳብ

ለእናት ሀገራችሁ ቀኑን በግንባር እያሳለፋችሁ ላላችሁ የኦሮሚያ ልጆች እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ!!

ለእናት ሀገራችሁ ቀኑን በግንባር እያሳለፋችሁ ላላችሁ የኦሮሚያ ልጆች እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ!!

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)
እናንተ ለሀገር ፍቅር ግንባር ናችሁ፡፡ ግንባራችሁን ለጥይት አልሰሰታችሁም፡፡ አውቃለሁ የልጅነት ትዝታችሁ የወጣትነት ናፍቆታችሁ፣ የቀዬ መንደር ትዝታችሁ እንዲህ ባለ ቀን ውል ይላል፡፡ ዛሬ ሆራ ሀርሰዴ አይደላችሁም፡፡ ይልቁንም ለሀገር ዘብ ቁማችሁ ነፍስን እስከመስጠት ዋጋ በሚጠይቅ ሙያ ተሰልፋችኋል፡፡

እናንተ የኦሮሚያ ምድር ልጆች፣ በወሎ ግንባር ያላችሁ፣ በጎንደር ግንባር ያላችሁ፣ የግብጽን ቅዠት የምዕራባውያኑን ከንቱ ምኞት፣ የሱዳንን የተልእኮ ጥፋት ከምንጩ ለማድረቅ ለሀገሬ አለሁላት ብላችሁ ዘብ የቆማችሁ ጀግኖች እንኳን አደረሳችሁ፤

ከድል መልስ የምስጋናችሁ ቀን እውን ይሆናል፡፡ ጨለማው ይገፈፋል፤ የክፋት ወንዝ ከሞላበት ይጎድላል፡፡ በሀገር የመጨከን ጉም ለሀገር በመቆም ጸሐይ ፍንትው ይላል፡፡ ሁለት ጎራ የሆነው ጎራውን በፈጠረው ኢትዮጵያ ጠል ኪሳራ ዳግም አንድ ጎራ ይሆናል፡፡ ያኔ የምስጋና ቀኑን ተመስግናችሁ ጭምር እናከብረዋለን፡፡

ዛሬ በመልካችሁ የላችሁም፤ ነገ ምናልባትም ቀጣዩን አፍራሳ በቀዬያችሁ ኢሬቻን ታከብራላችሁ፤ ተከብራችሁ የምታከብሩት ቀን ቅርብ እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ ባለውለታ ናቸሁ፤ ሀገር ብላችሁ ሀገር ታላቁን በዓል ሲያከብር እናንተ ለእውነትና ለሀገር ፍቅር በመቆም የኢትዮጵያ ዘብ ሆናችኋል፡፡
እናንተን እንኳን አደረሳችሁ ማለት ትርጉሙ ልዩ ነው፡፡ እናንተ በዛሬማ፣ እናንተ በሁመራ፣ እናንተ በወሎ እናንተ በበጌምድር እናንተ በህዳሴው ግድብ ጉያ ያላችሁ የኦሮሚያ ምድር ያፈራችሁ የሀገሬ ጀግኖች እንኳን አደረሳችሁ፤

ዛሬም አብዲሳ አጋን ባየንበት፣ ደጃች ገረሱን እጅ በነሳንበት፣ ደጃች ባልቻን ባከበርንበት፣ አባ መላን ባወደስንበት፣ የበርሃውን መብረቅ ከፍ ባደረግንበት መንፈስ ስማችሁን ከፍ አድርገን፣ ግብራችሁን አወደስን ለሀገር በሆናችሁት መንፈሳዊ ቅናት ቀንተን እንዲህ ባለው ቀን እንኳን አደረሳችሁ እንላለን፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top