Connect with us

[ ፓርላማው ሕዝብን በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ!]

ዛሬና ትናንት የብዙ ሰዎችና የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበ ጉዳይ በመሆኑ የግል ምልከታዩ እነሆ:-
Social media

ነፃ ሃሳብ

[ ፓርላማው ሕዝብን በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ!]

[ ፓርላማው ሕዝብን በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ!]

(ሙሼ ሰሙ)

ኢትዮጵያ ስድስተኛውን ፓርላማ ልታስተናግድ ሽር ጉድ እያለች ነው፡፡ ፓርላማው ምን ይዞልን ይመጣል? ወይም ምን ይዞብን ይመጣል? ይህንን ወደ ፊት የምናየው ይሁናል፡፡ አዲሱ ፓርላማ ግን በስራ ያልተፈተሸ፣ ለወቀሳም ሆነ ድጋፍ ያልደረሰ ስለሆነ መልካም የስራ ዘመን እመኝለታለሁ፡፡

ከሶስተኛው ፓርላማ (1997) በስተቀር ያለፉት አራቱ ፓርላማዎች “በከባድ የእንቅልፍ ድባቴ የተመቱ” በጭብጨባ ድምቀት በርግገው በመንቃት እውቀትና ክህሎት በሌላቸው ጉዳዮች ላይ በአጽዳቂነት ብቻ ንቁ ተሳተፎ የሚያደርጉ ፤ የፓርቲያቸውና የስራ አስፈጻሚው ማህተም (Rubber Stamp) በመሆን በትጋት እያገለገሉ የዘመናችንን ሩብ ምዕተ ዓመት ገደማ በከንቱ የፈጁ ናቸው።

ይህም ሆኖ አምስተኛው ፓርላማ በከባድ የነውጥ ጊዜ ውስጥ ያለፈ በመሆኑ ለየት የሚያደርገው ነገር አለው፡፡ ሕዝባዊ አመጽ፣ ግድያ፣ ስደት፣ መፈናቀል የመብት ጥሰት፣ ኮሮና፣ አንበጣ፣ ድርቅ፣ ጦርነትና የመሪ፣ የአመራረርና የፓርቲ መተካካትን አስተናግዷል፡፡ በርካታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆችን አውጇል፡፡ በሕዳሴ ግድብ ዙርያ መሰረታዊ መውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ መነቃቃት ቢሳነውም፣ በርካታ አነቃቂ ንግግሮችንም አድምጧል፡፡

ፓርላማው በተለይ የሃገራችንን ሕልውና ተፈታትኖት የነበረውን የሽግግርና የጥምር መንግስት ምስረታ ውዝግብ በማስወገድ የስራ ዘመኑን ማራዘሙ በመቻሉ ሀገራችን ላይ ተደቅኖ የነበረውን የውድቀት ደመና እንዲገፍ አድርጓል፡፡ በሕዝባዊ አመጹ ወቅት በርካታ እንደራሴዎች በመረጣቸው ሕዝብ ላይ እየደረሰ የነበረውን ግድያ፣ አፈና፣ እስርና ስደት እንዲቆምና ሕዝባዊ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ታግለዋል፡፡ ባልተለመደ ሁኔታ የመረጣቸው ሕዝብን ጥቅም አያስጠብቀም ባሏቸው ፓሊሲዎችና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ተቃውሞ በማሰማት፣ በሃሳብ በመሞገትና በድምጽ ብልጫ እንዲወሰን በማድረግ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ሚናቸውን ተወጥተዋል፡፡

አምስተኛው ፓርላማ ከሌሎቹ የተሻላ ተግባር የፈጸመው በተዓምር ሳይሆን፣ የተፈጠረለትን ወቅታዊ ሁኔታ (Window Period) ወደ ትግል ምእራፍነት መለወጥ በመቻሉ ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ግን የመጀመሪያን ሁለት አመት ተኩል እንቅልፉን እየለጠጠ ለመረጠው ሕዝብ ሳይሆን ለፓርቲና ለስራ አስፈጻሚው መሳርያ ሆኖ አገልግሏል፡፡ በተለይ የመጨረሻውን አንድ አመት ተኩል ግን ፓርላማው ለለውጡ ምክንያት የነበሩ ጥያቄዎች ዛሬም በፓርቲና በስራ አስፈጻሚው ሲተገበሩ እያያ እንዳላየ አልፏል፡፡ የመወሰን አይደለም የመማከር እድል እንኳን ሳያገኘ የስልጣን ጠገጉ እየተጣሰ የተለያዩ ውሳኔዎች በአናቱ ላይ ሲወሱኑ እንዴትና ለምን ብሎ አልጠየቀም፡፡ በጥቅሉ የመረጠውን ሕዝብ በፓርቲና በስራ አስፈጻሚው ተክቷል፡፡

ፓርላማው በጎ ጎኖቹ እንደተጠበቁ ሆነው በሕዝብ ትግል የተፈጠረለትን እድል በአግባቡ ተጠቅሞ ራሱን ከስህተት በማጽዳት ትግሉን በፅናት ማስቀጠል አለመቻሉ፣ ለመረጠው ሕዝብ ያልታመነና የድሮ በደሉ ሊሰረዝለት የሚገባው ፓርላማ አልነበረም፡፡ ለዚህ ደግሞ ሕዝብን በይፋ ይቅርታ ይጠይቃል ብዬ እጠብቃለሁ፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top