Connect with us

የገዛ መሪዎችን በመብላት ጥርሱን የሚጨርሰው የአማራ ፖለቲካ ቢያንስ ከዚህ በኋላ አብሮ በመቆም ይመን!

የገዛ መሪዎችን በመብላት ጥርሱን የሚጨርሰው የአማራ ፖለቲካ ቢያንስ ከዚህ በኋላ አብሮ በመቆም ይመን!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የገዛ መሪዎችን በመብላት ጥርሱን የሚጨርሰው የአማራ ፖለቲካ ቢያንስ ከዚህ በኋላ አብሮ በመቆም ይመን!

የገዛ መሪዎችን በመብላት ጥርሱን የሚጨርሰው የአማራ ፖለቲካ ቢያንስ ከዚህ በኋላ አብሮ በመቆም ይመን!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ድሬቲዩብ)

ዛሬ የአማራ ክልል ምክር ቤት አዲስ መንግሥት መስርቷል፡፡ እውነት ለመናገር አዲሱ መንግሥት ከነበረው ብዙም ርቀት ባለው መልኩ ልዩነት ያለው አልመሰለኝም፡፡ ይሁን እንጂ ክልሉን ሲመሩ የቆዩት አቶ አገኘሁ ተሻገር ስልጣናቸውን ለዶክተር ይልቃል አስረክበዋል፡፡ ምናልባትም በመንግስት ምስረታ ስልጣናቸውን ያስረከቡና ተኪ የቀየሩት አቶ አገኘሁ ተሻገር ይመስሉኛል፡፡

አቶ አገኘሁ ከባድ በሚባል ወቅት ወደ ስልጣን የመጡ መሪ ናቸው፡፡ የሚወቅሷቸውም የሚያመሰግኗቸውም የየራሳቸውን ጎጥ ተገን አድርገው ቁማር ቢጫወቱም ሰውዬው ግን በአመዛኙ በፈተና ወቅት የተገኙ መሪ በመሆን ለህዝቡ የቻሉትን እንደሰሩ አምናለሁ፡፡

ሰውዬው ያለፉትን አስራ አንድ ወራት ርዕሰ መስተዳድር ብቻ አልነበሩም፤ ጊዜያቸውን ከልማት ይልቅ የገጠማቸውን ፈተና ለማለፍ ወታደራዊ ጉዳይና ጸጥታ ላይ አውለው ባትለዋል፡፡ የተወሰኑ የክልሉ የፖለቲካ ልሂቃን ውጤት አላመጡም በሚል ይኮንኗቸዋል፡፡ ዞናቸውን ጥለው ለፈረጠጡ አመራሮች ጥፋት ሳይቀር ሲወነጀሉበት ቆይተዋል፡፡

ዛሬ ስልጣናቸውን ለአዲሱ መሪ አስረክበዋል፡፡ አዲሱን መሪም ማገዝ ካልተቻለ እና ተቀናጅቶ ለመስራት ካልተወሰነ አሁንም ወቅሶ ከመሸኘት የተለየ እድል አይፈጠርም፡፡ ዶክተር ይልቃል ከፍያለ ብዙ የሰሩ ምሁር ናቸው፡፡ የመጓተቱ ፖለቲካ ምናልባትም ምሁር ማሃይም የሚያድርግ ስለሆነ ችግሩን ለማቅለል መስራት ያስፈልጋል፡፡

የአማራ ፖለቲካ ጥርሱን የጨረሰው የገዛ መሪዎቹን በመብላት ነው፡፡ መሪዎቹ የሀገር አቀፍ ፖለቲካ ሽኩቻ ሲቀጠቅጣቸው ተደርቦ በወደቁበት የሚደበድብ የራሳቸው ምሁር ፍዳቸውን ያበላቸዋል፡፡ መሪ አልባ መሆን ውጤቱ ምን እንደሆነ የጠፋው ሳይሆን አንዳንዴም ከማዶ የተገዛ የሌላ መሪ እያወደሰ የራሱን መሪ ሲያንጓጥጥ ይውላል፡፡

ዶክተሩ ስኬታማና ለህዝቡ የሚጠቅም የሥራ ዘመን እንዲኖራቸው ከተፈለገ ማገዝ ነው፡፡ ማገዝ በእውቀት፣ በገንዘብና በጉልበት እንጂ የክልል መሪ በላይክና በሼር አልያም ሰፈሩን አስልቶ ጎንህ ነኝ በማለት አይደለም፡፡

ከጎጥ ዕይታ ማለፍ ያልቻሉ የአማራ አንቂ ነን ባይ ፖለቲከኞች ዛሬ ብዙ ጎጣቸውን በጁንታ አስበልተው ዳግም ቀበሌና ወረዳ እየለዩ ከመቧደን ያለፈ መፍትሔ አላመጡም፡፡ ያገዙትን መሪ ሲያቅተው ቢወቅሱት ያባት ነው፡፡ 

ብዙ ፈተናዎች የተጋረጡበት ህዝብ በሾመውም በአስማረውም ሳይጠቀም የመከራ ኑሮ የሚገፋበት እድሜ እንዲያበቃ እጅ ለእጅ መያያዝ ያስፈልጋል፡፡ የተያያዙት ያመጡትን ውጤት መመልከት ካቃተው ምሁር ትንታኔ ርቆ ጠንክሮ መስራትም ግድ ይላል፡፡

አሁን አማራ በርካታ ችግሮች አሉበት፣ ለዘመናት ሲወርድ የመጣው ድህነትና የልማት ችግር ዋናው ነው፤ የገጠመው የህልውና ዘመቻ ደግሞ ጊዜ አይሰጥም በዚህ ውስጥ የሚቀድመውን አስቀድሞ በህብረት መቆም ያስፈልጋል፡፡

ሹማምንቱን ማገዝ እምነት መቀየር እስከመሆን የሚሰማቸው ጥቂቶች በሰፈር እቃ እቃ ሊያጫውቱት ሲሞክሩ በቃ የሚል አንድነት ያስፈልጋል፡፡ የሰራውም ያጠፋውም አሁን አልፏል፡፡ የሚመጣው ለህዝቡ የሚጠቅም ስራ እንዲሰራ ግን የሚጠቅም ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡ ዘለፋም፣ ሀሜትም፣ ቡድንተኝነትም እንኳን በዚህ ከባድ ወቅት በሰላምም ጊዜ ለዚህ ህዝብ አይጠቅምም፡፡ 

ለአዳዲሶቹ መሪዎች የስኬት የስራ ዘመን ተመኝተናል፡፡   

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top