Connect with us

ጠቅላይ ሚኒስትራችን፤ እኛ የመረጥነው እርስዎን እንጂ ባይደንን አይደለም፤

Social media

ነፃ ሃሳብ

ጠቅላይ ሚኒስትራችን፤ እኛ የመረጥነው እርስዎን እንጂ ባይደንን አይደለም፤

ጠቅላይ ሚኒስትራችን፤ እኛ የመረጥነው እርስዎን እንጂ ባይደንን አይደለም፤ የምንፈልገውም ትህነግን ማጥፋት ነው!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ ድሬቲዩብ)
ጆ ባይደን እንዲህ አለ ይሉኛል፤ እርግጥ ነው የሃያላኑ ሀገር መሪ ልባቸው ላይ የፈጣሪን ያህል የታተመበት ሰው ብዙ ቢርበተበት አይገርመኝም፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡

የመረጥኩት የበሻሻውን ዶክተር አብይን ነው፡፡ እንዲህ አለ ብዬ ያለው የሚገዛኝ የኔው ጠቅላይ ሚኒስትር እንጂ ጆ ባይደን አይደለም፡፡

ጆ ባይደን የሚሸልልባት ሀገር ሰው እንደ ዝንጀሮ ከዛፍ ዛፍ ሲዘልባት የእኔ ሀገር በጥበብ ረቃ የቅዱሱ ዮሐንስ ምድር ተብላ ስውር የምስጢር ጦሯን ለአውሮፓ ትልክ ዘንድ የተፈለገች ናት፡፡

ዛሬም ጥቁርን አጋድሞ በማነቅ የሚገድል ፖሊስ ባለባት የጆ ባይደን ሀገር የምኖር አይደለሁም፡፡ ሀገሬ በታላቁ ነብይ የፍትሕ ሀገር የተባለች ልዩ ምድር ናት፡፡ እናም ጆ ባይደን የጻፉትን ደብዳቤ ለራሳቸው ያንብቡትና ያለ አግባብ አፍጋንን ያተራመሱበትን ነውር ያጢኑ።

የአሜሪካ እና የወያኔ ግንኙነት የታወቀ ነው፡፡ ዛሬ በገዛ ሀገራችን ምን አገባችሁ ባይዋ ሀገር ትናንት እኮ ወያኔን አስታጥቃ ሱማሊያ ያስገባች ነውር የማትፈራ ጉድ ናት፡፡ ዓለም የአሜሪካንን የመነሳትና የመውደቅ ታሪክ ሲያነብ ደጋግሞ ሊል የሚችለው እንዴት ግን በየጊዜው ከስህተታቸው አይማሩም ይመስለኛል፡፡

ለማንኛውም የራሳችን መሪ አለን፤ የራሳችን ፍላጎት ደግሞ ዘለዓለማዊ ጠላታችን ከእኛ አልፎ ለጎረቤትና ለምስራቅ አፍሪካ መከራ የሆነውን ትህነግ መደምሰስ ነው፡፡

ይህንን ፍላጎት እውን ለማድረግ የአሜሪካ አልሚ ምግብ አያስፈልገንም፤ ያ አልሚ ምግብ ለሚያስፈልጋቸው ተዋጊዎች እየረዳች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ችግር ላይ ሲወድቁ አንዳች ነገር ያላለችን ሀገር ሀገር ብሎ እንዲህ አለች ማለት አያስፈልግም፡፡

አሜሪካኖቹ ገና አባይን ብርሃን እናደርጋለን ካልን ቀን ጀምሮ ግብጽን ሆነው ያረፉ፤ መፈራረሳችንን ተመኝተው ሁሉንም አማራጭ እና እድሎች ሲጠቀሙ ያየናቸው ናቸው፡፡
ቀና ልብ ኖሯቸው ቢሆን ኖሮ ገና ያኔ ህጻናትን ለጦርነት ማሰለፋቸውን ስንነግራቸው ባላየ ባልሰማ ባላለፉን ነበር፡፡

ከቀና ልብ ቢነሱ የገባ መኪና መውጣት እያቃተው ለጦርነት ሲውል፣ የእርዳታ መጋዘኖቻቸው ሲዘረፉ፣ በድራግ የታወረ ወጣት ሲማገድ፣ አማራና አፋር ሲወረር ተው ማለት በተገባቸው ነበር፡፡

ትህነግ የነቀነቃትን ኢትዮጵያ ነቅለን እንጥላታለን በሚል ምኞት ስውር ደባ ይዘው እየታገሉ መሆኑን ደርሰንበታል፡፡ አሁን የምንፈራው ምንም ነገር የለም፡፡ የማዕቀብ ዛቻው ገና ባልተጨበጠ ስጦታቸው ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ጠንካራ ዝምድናና አሜሪካን ባህሪዋን እስክትገራ ፊትን የሚያዞር የዲፕሎማሲ መርህ ያሻናል፡፡ ብትተወን እንኳን አልሳካ ብሏት እንደሆነ አምነን መጨከን አለብን፡፡

ከዚህ ውጪ ሴቶች ተደፍረዋል፡፡ ትምህርት ቤቶች ወድመዋል ዜጎች ሙታንታቸው ሳይቀር ተዘርፏል፡፡ ሚሊዮኖች ከቤታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ይህም ሆኖ ሲዖል ድረስ ወርዶ ኢትዮጵያን ማጥፋት የሚፈልገው ቡድን አሁንም ከክፋትና ቅዠቱ ጋር አለ፡፡

ይሄ ቡድን ከምድር ካልጠፋ ጠላቴ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ በምድር መኖር አይችልም፡፡ ስለዚህ የህልውናውን ዘመቻ ለመኖር ነው እስካልነው ድረስ የባይደን ቡራኬ አያስፈልገውም፤ የባይደን እርዳታም እኮ ስንኖር የሚደርሰን ነው፡፡ አሁን ጥያቄው ስለመኖር ነው፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top