Connect with us

አባ መስጠት ወሎን እንታደግ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረግ እንደ ህዝብ አብረን እንቁም፡፡

Social media

ነፃ ሃሳብ

አባ መስጠት ወሎን እንታደግ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረግ እንደ ህዝብ አብረን እንቁም፡፡

አባ መስጠት ወሎን እንታደግ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረግ እንደ ህዝብ አብረን እንቁም፡፡

(ስናፍቅሽ አዲስ -ድሬቲዩብ)
የትህነግ ወራሪ በወሎ ህዝብ ላይ ያደረሰው በደል የጥላቻ ጥጉን ያየንበት ሆኗል፡፡ ወራሪው ሃይል በጭና፣ በዳባትና አካባቢው፣ በደባርቅ ገጠር ቀበሌዎችና በጋይንት እንዳደረሰው በደል ሁሉ በወሎም ብዙ ቀውስ አምጥቷል፡፡

ሙታንታ ሳይቀር ሰርቆ የፈረጠጠው ሃይል እንደ አንበጣ በየገበሬው ቤት የሚላስ የሚቀመስ እንዳይኖር አድርጎ ቤት አራቁቷል፡፡ መንደር አቃጥሏል፡፡ በጦር አውደ ውጊያዎች የደረሰበትን ሽንፈት ዘለዓለማዊ የነውር ታሪክና ነገ ዓለም የሚደርስበትን አጸያፊ ስራ ለማጥፋት ንጹህ የወሎን ህዝብ መከራ አድርሶበታል፡፡

እኛ ግን ብዙ ነን፤ የወራሪውን ያህል በጣት የምንቆጠር፣ ጥሪት አልባና እና ወገን የምንጠላ ስላልሆንን ወሎን ለመታደግ ከዳር ዳር መነቃነቅ አለብን፡፡ ዲያስፖራው የሆነውን የማጋለጥም ችግሩን ለመታደግ የመርዳትም ሃላፊነት አለበት፡፡

አንዳንድ ሌት ተቀን የምሬትን ዜማ የሚያሰሙና አንዳች ለማድረግ ሀሞት የሌላቸውን አንስማቸው እንደ ሀገር የመጣን ጠላት እንደ ሀገር በመቆም እንመክተዋለን፤ እንረዳዳለን እንደጋገፋለን፤ እንዲህ ከሆነ መከራው ከእኛ ይልቅ ባደረሰው ወራሪ ሃይል ላይ ወድቆ ይቀራል፡፡

አሁን ደርሶ ሴራ ነው ደባ ነው እያሉ አንድ ጉርሻ ዳቦ የማይሆን ትንታኔ ከመንዛት የሚበልጠው ተጠራርቶ መረዳዳት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የነፍስም የስጋም ጠላት የሆነውን ወራሪው ሃይል ድምጥማጡን አጥፍተን እንዋቀሳለን፤ ከወቀሳው በፊት አብሮ መቆም ይቅደም፡፡

በወረራቸው አካባቢዎች የወራሪው ሃይል ክፉ ክንድ ያላረፈበት የአማራ ቀዬ የለም፤ ያልበላውን ደፍቶ የሄደ በሺህ አመታት ታሪካችን ገጥሞን የማያውቅ እጅግ የከፋ ጠላት ነው፡፡ ለዚህ ጠላት ሌላ የዳቦ ስምም የመጣበትን እና ያደረሰውን ጫና ትንታኔም አይፈልግም፡፡ ክተት ተብሏል፡፡ ክተት፤ በቀረው ለወገን አለሁ ማለት ነው፡፡

ከተለያዩ የወሎ አካባቢዎች ቤት ንብረታቸው ጥለው ህይወታቸውን ለማትረፍ ከሞቀ ህይወታቸው የተፈናቀሉትን አለሁላችሁ ለማለት እንደ ሀገር ከቆምን ችግሩ እጅግ ተራ ትንሽና ዝንብ ያረፈብን ሳይመስለን የምናልፈው ይሆናል፡፡
የሚያስፈልገንን በአስፈላጊው ሰዓት ካላደረግን ጠላት ካደረገብን በደል በላይ ራሳችን በራሳችን ላይ እናደርጋለን፡፡ ስለዚህ ሆ ብለን መነሳት ያለብን ወገንን ለመታደግ ነው፡፡

ወገን ደራሽ ሲፈልግ እኛ ፖለቲካ ተንታኝ ከሆንን ተያይዞ ማለቅ እንጂ አንዳችም የምናተርፍው ነገር የለም፡፡ መጽሐፉ ለመወቃቀስም ጊዜ አለው እንዲል ለመወቃቀስ ጊዜው እስኪመጣ አሁን ለመደጋገፍ የመጣውን ጊዜ በህብረት ቆመን እውን እናድርገው፡፡

በኦሮሚያ ሲዳማ ደቡብና ሌሎችም ክልሎች ለአፋርና ለአማራ እየተደረገ ያለው ድጋፍ አለኝታነትና ህይወትን ከመስጠት ባሻገር ያለን ተካፍሎ ለመብላት የታየው አንድነት በአማራ ውስጥም ጠንክሮ መቀጠል አለበት፤ ለአማራው አማራው አለሁ ብሎ በመተጋገዝ ይሄንን ችግር መወጣት ይቻላል፡፡

ለረሃብ ስቃይና መከራ ትንታኔ ወቅታዊ መፍትሔ አይደለም፤ ወቅታዊ መፍትሔውን ትተን ጭራሽ ወደሚብስ እንካ ሰላንቲያ የሚከቱንን ተላላኪዎች ጆሮ አንስጣቸው ይልቁንም ለወገኖቻችን ችግር ልባችንን ሰጥተን መቀነታችንን እንፍታ፤
እናልፈዋለን፡፡ በማይጨበጥ ሀሳብ ሳይሆን በተግባር ተጋግዘን እናልፈዋለን፡፡

ይህ ሁሉ ነገ አይኖርም፤ መከራውን ለማሳጠር በህብረት እንቁም፤ ከወሎ ህዝብ ጎን እንሁን፡፡ አስቸኳይ ህዝባዊ የድጋፍ ንቅናቄ እንዲፈጠር ስልት እንንደፍ፤

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top