Connect with us

መረጃው ይፈተሽ?

Social media

ነፃ ሃሳብ

መረጃው ይፈተሽ?

መረጃው ይፈተሽ?
(ሙሼ ሰሙ)

በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል እየቀረበ ያለው መረጃ የጠራና በቅጡ የተደራጀ ባይሆንም ከሰሜን ወሎ አካባቢ የሚሰማው ነገር የሚረብሽ ነው።

ነዋሪዎቹ የረሃብ አደጋ አንዣቦባቸዋል። እንኳን ነዋሪውን ሊታደግ ይቅርና የራሱን ሰራዊት በዘረፋ የሚቀልብ ሃይል መሬታቸውን ወሮ በመያዙ የሚላስ የሚቀመስ ያጡበት አሳሳቢ ሁኔታ ተፈጥሯል። በረሀብ ምክንያት ሞት ሊከሰት እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ ነው።

ጉዳዮ የደቀነው አደጋ አስጊ ቢሆንም የችግሩን መጠንና ስፋት፣ የደቀነውን አደጋና የመፍትሔ አቅጣጫ ከፌስ ቡክና ከመፈክር ውጭ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ፣ አግባብነት ባለው አካሄድ ለሚመለከተው አካል ሲቀርብ አይታይም። ይህ ደግሞ ይበልጥ የሚያሳስብ ነው።

ዛቻውን፣ ማስፈራሪያውንና ጣት መቀሳሰሩን ጋብ አድርጎ አደጋው የተጋረጠበት ሕዝብን እንዴት መድረስና ሕይወቱን መታደግ እንደሚቻል ተቀራርቦ በመነጋገሩና በጋራ መፍትሔ መሻቱ ፍሬ ሊያፈራ ይችላል።

አሁንም ኋላፊነት የሚሰማችሁ ጉምቱ የሰሜን ወሎ ተወላጆች፣ ተቆርቋሪዎችን አካታችሁ፣ ግንባር ቀደም ኋላፊነቱን በመውሰድ ሌሎችን በሚያሳትፍ መልክ ተደራጅታችሁ መፍትሔ በጋራ የምንፈልግበትን ፕላት ፎርም ፍጠሩ። እውነትም ሴራ፣ አቅም ማነስና ኋላፊነትን ለመወጣት አለመቻል ካለ ወይም ሕዝባዊ ድጋፍ የሚያስፈልግበት አግባብ ካለ ለቀጣይ እርምጃ፣ በተደራጀ መልክና በሀቅ መረጃውን እንፈትሽ፣ እናግኝ።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top