Connect with us

የዳያስፖራው የልዑካን ቡድን ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ 

የዳያስፖራው የልዑካን ቡድን ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ
ኢዜአ

ዜና

የዳያስፖራው የልዑካን ቡድን ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ 

የዳያስፖራው የልዑካን ቡድን ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ 

~ በስካላይት ሆቴል መግለጫ ይሰጣል፣

ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ የሚያካሂዱት ጉብኝት የሚያስተባብር የልዑካን ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተግባር ምክር ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ያዘጋጀው መርሃ ግብር “እንቁጣጣሽ ኢትዮጵያ የፍቅር ጉዞ” በሚል መሪ ሀሳብ ከጳጉሜን ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄድ ነው።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተግባር ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አለባቸው ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ መርሃ ግብሩን የሚያስተባብሩት ስድስት የምክር ቤቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ።

በመርሃ ግብሩ 500 ዳያስፖራዎች የሚሳተፉ ሲሆን፤ ከሰሜን አሜሪካ፣ እስያ፣ አፍሪካ፣ አውሮፓና መካከለኛው ምስራቅ እንደሚመጡም አመልክተዋል።

በመርሃ ግብሩ ዳያስፖራው “አባይን እንጎብኘው” በሚል መሪ ሀሳብ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ እንደሚጎበኝና የግድቡን ሰራተኞች እንደሚያበረታቱም ተናግረዋል። 

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሃሳብ አመንጪነት ግንባታቸው የተከናወነው የሸገር ማስዋብና በገበታ ለአገር ፕሮጀክት የተካተተው ጎርጎራ የጉብኝቱ አካል ናቸው ብለዋል።

በኢትዮጵያ “የዳያስፖራ ሙዚየም ለመመስረት የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ የሚቀመጥበት መርሃ ግብር ይከናወናል ነው” ያሉት አቶ አለባቸው።

ለጉብኝት የሚመጡት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደሚሳተፉ ጠቁመው፤ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ደም እንደሚለግሱም አመልክተዋል።

ዳያስፖራው በኢትዮጵያ ሕዝብ በተመረጠውና ለአምስት ዓመት ለመምራት ሃላፊነት ለተቀበለው መንግስት አደራ እንደሚሰጡ አመልክተው፤ ከኢትዮጵያ ጎን መቆሙን የሚያረጋግጥበት የቃል ኪዳን እራት መርሃ ግብር እንደሚዘጋጅም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ “በችግርና ፈተና ውስጥ ባለችበት ወቅት ዳያስፖራው ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ደስታን የሚፈጥር ነው” ያሉት አቶ አለባቸው፤ በዚህም ረገድ መርሃ ግብሩ አገር ያለችበትን መከራ እንድታልፍ ከጎኗ በመቆም አጋርነቱን የሚያሳይበት መሆኑን አብራርተዋል።

ዳያስፖረው ለኢትዮጵያ እድገትና ልማት የሚያደርገውን ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥልም አክለዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት በመስከረም 2013 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን፤ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎችን የያዘ ነው።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ በመገንባት፣ በልማትና በትውልድ ቀረጻ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራም ነው።

አስተባባሪ ቡድኑ ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በስካይላይት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ታውቋል።

ኢዜአ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top