Connect with us

ሲዳማ አለሁ ብሎ ባህር ዳር ከተተ፤ የአማራ ባለሀብትም ሠመራ ገባ። ሀገር ተጋምዶ አብሮ ቆመ!

ሲዳማ አለሁ ብሎ ባህር ዳር ከተተ፤ የአማራ ባለሀብትም ሠመራ ገባ። ሀገር ተጋምዶ አብሮ ቆመ!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ሲዳማ አለሁ ብሎ ባህር ዳር ከተተ፤ የአማራ ባለሀብትም ሠመራ ገባ። ሀገር ተጋምዶ አብሮ ቆመ!

ሲዳማ አለሁ ብሎ ባህር ዳር ከተተ፤ የአማራ ባለሀብትም ሠመራ ገባ። ሀገር ተጋምዶ አብሮ ቆመ!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ድሬቲዩብ)

አብረን ቆመን ሀገር ለማፍረስ የቆሙትን እያንበረከክን እንደሆነ ከዳር ዳር ያለው እንቅስቃሴ ማሳያ ነው። እርግጥ ነው ሀገራችን ቢሆንም ትግራይን ከመልቀቅ ሰው ይለቅ አላልንም። ትግራይን ለመሥራት ብንፈልግም ማፍረስ የፈለገው ሲፈለግ አላኮረፍንም። የጥሞና ጊዜው ዓላማ ይኼ ነበር ወያኔ ግን እድሉን ኢትዮጵያን ለማፍረስ አጨው። ገዳም ለማቃጠል መነኩሴ ለመግደል ኢማም ለመረሸን ተጠቀመበት። ብዙ ጅል እንደሚለው ጦርነቱ እርስ በእርስ አይደለም። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከተነሱ ተላላኪዎች ጋር ነው። እናም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ቆሟል።

ወያኔ በየቀኑ ብትዋሽም በትግራይ ክልል የሚኖር ቢያምናትም እውነታው የተለየ ነው። ከዳር ዳር ወያኔን ዳግም ከሚመለከት ሞቱን የመረጠ መቶ ሚሊዮን ህዝብ ሆ ብሏል። ይሄ ህዝብ ትግራይ ልግባ ከእኔ ደብረ ፅዮንን ለምን መረጣችሁ ያለ አይደለም የፈለጋችሁትን ምረጡ ሀገሬን ግን አታፈርሱም ባይ ነው። ጥጋብ ከሞቀ ስልጣን ዋሻ የኸተተው ሌባ ዘርፎ መብላት አሳር ሲሆንበት የትግራዋይ ነፍስ አሲይዞ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በታሪካዊ ጠላቶቿ ተቀጥሯል። ድንጋይ ተሸክመው ማሩን እንዳሉት ታሪክ አንበርክኮ ነውሩን ሲነግረው ይኖራል።

የሲዳማ ክልል አዲስ ጎጆ ወጪ ብዙ ገንዘብ ለመዋቅሩ የሚያስፈልገው ክልል ነው። ግን ያፈነውንና ክልል ለመጠየቅ እርጥብ ሳር ይዞ ቢወጣ የረሸነውን የሀገር ጠላት ዛሬም ሀገር ላፍርስ ሲል እንቢ አለ። ሰንጋውን ይዞ ገንዘቡን ቋጥሮ ባህር ዳር ገባ። ህዝባዊ ነው በሚል ሽፋን የሌባ አጀንዳ ለማራመድ ጦርነት ያወጀው የጌታቸው ረዳ ቡድን ኢትዮጵያን አጋመድ ሀገር ከዳር ዳር አስተሳሰረ። ሀዋሳን ባህር ዳር አመጣ። ምክንያቱም ሀገር ናታ።

ወያኔ ያልበደለው እና ያልዘረፈው ህዝብ የለም። ለዚህም ነው ጥሪው ከዳር ዳር አስተጋብቶ ርቀትም ቋንቋም ሳይገድበው አብሮ የቆመው። ይህ የዘመን ነቀርሳ ከእናት ሀገር ጫንቃ ይነቀል ዘንድ ሁሉም በጋራ ቆሟል።

የኦሮሞ ህዝብ መቀነቱን ፈትቷል ሰንጋ ልኮ ደጀን ሆኗል። ለዚህ ጦርነት ኪስ በመፍታት ጅማ ከጎንደር እኩል አለሁ ብላለች በሌላ በኩል የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በደባርቅ ግንባር ከኢትዮጵያ ህዝባዊ ሠራዊት ጋር አብሮ እየተዋደቀ ነው። ሱማሌ ሞቴን ለሀገሬ ያድርገው ብሏል። ደቡብ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ሆ ብለው ተመዋል። ሀገር አፍራሽ እየፈረሰ ነው።

አፋር እንኳን እሱ ግመሉ ባንዲራውን የምትለይ የእናት ሀገር ታፍራ መኖር ምልክት ነው። ትህነግን ደቁሶ ዓላማዋን አክሽፎ ዶግ አመድ አድርጓታል። እርግጥ ነው ንፁሃን ሞተዋል ማይካድራን በአፋር ደግመዋል ግን የአፋርን ፅናት አልገቱትም።

ዛሬ የአማራ ባለሀብቶች አፋር ሰመራ ገብተዋል። እናት ሀገሩን ለሚወደው ወገን እነ ወርቁ አይተነው ወርቅ ልብ ይዘው ሰመራ ገብተዋል። አለን ደጀን ነን ሲሉ አንድነትን አውጀዋል። አብረን ስለቆመን ሌባና ተላላኪ አይጥለንም ሲሉ ዳግም ሀገር አጋምደዋል። ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top