Connect with us

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ
አዲስ ማለዳ እና ሌሎች

ዜና

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ

የኢፌድሪ  በክብር እንግድነት በተገኙበት 9 ነኛው የበጎ ሰው ሽልማት የመንግስት የሥራ ኃላፊነቶችን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተሸላሚ ሆነዋል።

በ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የመንግስት የስራ ሃላፊነቶችን በብቃት በመወጣት ዘርፍ መምህር ይኩኖአምላክ መዝገበ እንዲሁም ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ እጩ የነበሩ ሲሆን ላበረከቱት አስዋፅኦም የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

በተያያዘ ዜና በማህበራዊ ጥናት ዘርፍ የ2013 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ ሲሆኑ በሳይንስ ዘርፍ የ2013 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ኤምሬተስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ ሆነዋል።

በ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በማህበራዊ ጥናት ዘርፍ ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ እንዲሁም ዶክተር አሉላ ፓንክረስት እጩ የነበሩ ሲሆን ላበረከቱት አስዋፅኦም የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

ኤምሬተስ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ተፈራ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ኢንጅነሪንግ ዘርፍ በመምህርነት ያገለገሉትና በዘርፋም እጅግ በርካታና ውጤታማ ሥራዎችን ያከናወኑ ሲሆን የ2013 የበጎ ሰው ሽልማት የሳይንስ ዘርፍ ተሸላሚ ሆነዋል።

በ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በሳይንስ ዘርፍ ዶክተር አየለ ተሾመ እንዲሁም ፕሮፌሰር የወይንህረግ ፈለቀ ሌሎች እጩ የነበሩ ተወዳዳሪዎች ሲሆን ላበረከቱት አስዋፅኦም የእውቅና እና የምስጋና ሰርተክፌት ተበርክቶላቸዋል።

በ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ላይ በቅርስና ባህል ዘርፍ የ2013 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ቢላሉል ሀበሺ ሙዝየም ሆኗል።

ቢላሉል ሀበሺ ሙዝየም በ1992 የተመሠረተ የማኅበረሰብ ሙዝየም ሲሆን የተለያዩ በጎ አድራጎት ሥራዎችንም ይሠራል።

ለኢስላማዊ ቅርሶች ልዩ ትኩረት የሰጠ ሲሆን፣ የተቋቋመው በቅርስነት ሊያዙ የሚገቡ ቅርሶች እንዲጠበቁ፣ እንዲታወቁና በአንድ ቦታ ተሰብስበው ለጥናትና ምርምር ጭምር እንዲውሉ ለማስቻል ነው።

በ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በቅርስና ባህል ዘርፍ ሲሳይ ደምሴ እንዲሁም ዶክተር መንግስቱ ጎበዜ ሌሎች እጩዎች የነበሩ ሲሆን የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

በሚዲያና በጋዜጠኝነት ዘርፍ የ2013 የበጎ ሰው ሽልማትን ዶክተር ንጉሴ ተፈራ ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል።

በ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በሚዲያና በጋዜጠኝነት ዘርፍ ጋዜጠኛና ደራሲ ደጀኔ ጥላሁን እንዲሁም ጋዜጠኛ ስላባት ማናዬ እጩ የነበሩ ሲሆን ላበረከቱት አስዋፅኦም የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

በኪነ ጥበብ (ወግና አጫጭር ፅሑፎች) ዘርፍ የ2013 የበጎ ሰው ሽልማትን ደራሲ እና ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም ተሸላሚ ሆኗል።

በእውቀቱ <ኗሪ አልባ> ጎጆዎች የተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሐፉ በብዙዎች እንዲታወቅ ያስቻለው ሲሆን፤ መግባት እና መውጣት፣ ከአሜን ባሻገር፣ የማለዳ ድባብ፣ እንቅልፍና እድሜ የተሰኙ መፅሐፍትንም ለአንባብያን አድርሷል።

በእውቀቱ አገር ውስጥ ባለመገኘቱ ወላጅ አባቱ ስዩም መሰለ ሽልማቱን ተቀብለዋል።

በ9ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በኪነ ጥበብ (በአጫጭር ወጎች) ዘርፍ ደራሲ ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤሌ እንዲሁም ደራሲ ታደሰ ሊበን እጩ የነበሩ ሲሆን ላበረከቱት አስዋፅኦም የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

በየዓመቱ ለሀገርና ለሕዝብ አርያነት ያለው ታላቅ ተግባርን ያከናወኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመለየት ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት፤ ዘጠነኛ የሽልማት መርሀ ግብሩን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ለሽልማቱ ከ 500 በላይ ሰዎች ተመርጠው የነበረ ሲሆን 30 እጩዎች ታጭተው ከእነርሱ ውስጥም ዐስሩ በዛሬው ዕለት ለሽልማት በቅተዋል።

በበጎ ሰው ሽልማት እስከ አሁን ከ170 በላይ ሰዎችን ለሽልማት መብቃታቸው በመድረኩ ገልጿል።

የየዘርፉ ዕጩዎችና አሸናፊዎች

  1. በኪነጥበብ ዘርፍ እጬዎች የነበሩት

 _ በዕውቀቱ ስዩም

 _ ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤል

በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት

በዕውቀቱ ስዩም  ነው:: የበእውቀቱ ስዩምን ሽልማት የተቀበሉት አባቱ አቶ ስዩም መሰለ ናቸው::

2.በማህበራዊ ጥናት ዘርፍ እጬዎች የነበሩት

 _  ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ

 _ ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ

 _ ፕሮፌሰር አሉላ ፖንክረስት

በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት

ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ ናቸው::

3 . በቅርስና ባሕል ዘርፍ እጬዎች የነበሩት

   _  ዶ/ር መንግስቱ ጎበዜ

    _ አቶ ሲሳይ ደምሴ

    _ ቢላል ሐበሽ  ሙዚየም የልማትና የበጎ አድራጎት ማህበር ሲሆኑ

በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት

ቢላል ሐበሽ ሙዚየም ናቸው::

4.በመምህርነት ዘርፍ እጬዎች የነበሩት

– ዶ/ር ልዑል ሰገድ አለማየሁ

– ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

– ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ ሲሆኑ

በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት

ዶ/ር ልዑልሰገድ አለማየሁ ናቸው::

5.በሚዲያና በጋዜጠኝነት እጬዎች የነበሩት

  _  ጋዜጠኛ ደጀኔ ጥላሁን

  _ ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ

  _ ስለአባት ማናዬ

በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት

ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ ናቸው::

  1. በበጎ አድራጎት እጬዎች የነበሩት

⁃ ማርያም ሙኒር

⁃  እልልታ ውመን አት ሪስክ ግብረሰናይ ድርጅት

⁃ አቶ አማረ አስፋው ሲሆኑ

 በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት

አቶ አማረ አስፋው ናቸው::

  1. በሳይንስ ዘርፍ እጬዎች የነበሩት

 _ ዶ/ር አየለ ተሾመ

 _ ኤመሬትስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ

 _ ፕሮፌሰር የወይንሐረግ ፈለቀ ሲሆኑ

በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ  ኤመሬትስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ ናቸው::

  1. በንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ እጬዎች የነበሩት

 _ ወ/ሮ ብሩክታዊት ጥጋቡ

 _  አቶ በላይነህ ክንዴ

 _  ፓን አፍሪክ ግሎባል ኩባንያ

በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት

አቶ በላይነህ ክንዴ ናቸው::

  1. መንግስታዊ የስራ ኃላፊነት በብቃት በመወጣት ዘርፍ እጬዎች የነበሩት

   _ ኢንጂነር ሐብታሙ ተገኝ

   _ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ

   _ አቶ ይኩኑዓምላክ መዝገቡ

በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት

 ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ናቸው::

10.ኢትዬጵያ መልካም ስራ የሰሩ ዲያስፖራዎች  ዘርፍ እጬዎች የነበሩት

  _  ዶ/ር እንዳወቀች ዘርጋው

  _ አለምፀሐይ ወዳጆ

  _  ኤልያስ ወንድሙ

በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት

አቶ ኤልያስ ወንድሙ ናቸው::

የ2013 ዓ.ም  የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ  የሆኑት ጸሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ ናቸው::

(አዲስ ማለዳ እና ሌሎች)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top