ሀገር ወረራችሁ፣ ዩኤስ ኤይድን ዘረፋችሁ፣ ቤተስኪያንና መስጂድ አወደማችሁ፤ ግጭታችሁ ከምድሩም ከሰማዩም መንግሥት ሆነ!
(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)
መርከብ ሰርቀውናል፤ ከግድብ ላይ አርማታ ዘርፈውናል ስንል ውሸት የመሰላት አሜሪካ መጋዘኗ ሲገቡ እውነትም ብላለች፡፡
የጨጨሆ መድሃኒዓለም ጥቃትና ጉዳት ለእናንተ አፍቃሪዎች ዛሬም ውሸትና ፕሮፖጋንዳ ይምሰል እንጂ ትናንት ጀምሮ ታሪካችሁን ላጤነ ግብራችሁ ነው፡፡ በትግራይ ገዳማት ቅርስ ትጥቅና ስንቃችሁን አሟልታችሁ ከደርግ ታግላችኋል፡፡
ትህነግ ቤተ ክርስቲያን አታፈርስም ብሎ ከሚሟገት ጋር መሟገት ውሃ ማፍሰስ ነው፡፡ አክሱም ከተማን ለቆ የወጣው ጁንታ ያወደመውን ኤርፖርት ለተመለከተ ይሄ አያጠራጥረውም፡፡ አልነጃሺን አፍርሶ ጣት ቀስሮ ተአምር ለመፍጠር ያለመ ተራ ፖለቲከኛ ከዚህ በላይ እንደሚፈጽም እናውቃለን፡፡
ሀገር የወረረ፣ ከሀገር የተጣላና በመቶ ሚሊዮኖች ልብና መንፈስ ውስጥ የሴይጣንን ያህል ስፍራ የተሰጠው ቡድን አሁን ደግሞ እኩይ ዓላማውን በድብቅ ከሚደግፉት ጋር መጋጨት ጀምሯል፡፡ አሜሪካ ለአዲስ አበባ ቤተ መንግስት ያጨችውና ግፋ ያለችው ቡድን የህጻናት አልሚ ምግብ የሚሻማ ተምች በመሆን የሚያደርሰው ጥፋት እየከፋ መጣ፡፡
የዩኤስ አይ ዲ ሃላፊ ለሚዲያ እንደገለጹት ከሆነ በተጨባጭ ወራሪው ቡድን መጋዘኖች ሰብሮ የእርዳታ ድርጅቱን ንብረቶች ዘርፏል፡፡ የአሜሪካው የእርዳታ ድርጅት መጋዘኖች በአማራ ክልል የአርሶ አደሩ ጎጆ እጣ ደርሷቸዋል፡፡ ተመዝብረዋል ተዘርፈዋል፡፡
አሜሪካ ወንበዴውን ወንበዴ ለማለት ብታቅማም ወንበዴው ግን ወንበዴ ነኝ ብሎ በተግባር የአሜሪካንን የእርዳታ ድርጅት መጋዘኖች ለመመዝበር አላመነታም፡፡
እንዲህ ባለው ዓለም ጉድ እያለ በሚሰማው ነውር የተሞላው ወንበዴ ትግራይ አጥፍቼ፣ ኢትዮጵያን አክስሬ ብጠፋም አይቆጨኝም የሚል ቁማር ውስጥ ገብቷል፡፡ ሀገሩን በጣም በጎዳ ቁጥር ትግራይን በከፋ ደረጃ እያጠፋ እንደሆነና ያለ ዘር ወገኑን የማስቀረት ድራማውን እንደቀጠለ የሚነግረው አይፈልግም፡፡ አጥፍቶ መጥፋቱን ነጻ አወጣሃለሁ ካለው የራሱ ህዝብ ጀምሯል፡፡ ከእያንዳንዱ የአሸነፍኩና ተቆጣጠርኩ ሰበር ጀርባ ብዙ የትግራይ ወጣት ተማግዶ ወድቆ ቀርቷል፡፡ ደግሞ አጻፋው ከፍቶ ከምናደምጠው ሽሽትና የድል ዜና ጀርባ ምንም የማያውቁ የትግራይ ወጣቶች እልቂት አለ፡፡
እርግጥ ነው፤ ወንበዴው ያወደመው ያጠፋው የገደለውና መርዝ የወጋው የአማራ እና የአፋር ህዝብ ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ማህበራዊ ቀውሱም ቢሆን እጅግ የከፋ ደረጃ ደርሷል፡፡ ትናንት ትግራይ እስክትለማ ሌላው ሀገር ይድማ ብሎ ክፉ የዘር ፖለቲካን የዘራው ጁንታ ዛሬ እየፈጸመ ያለው በደል ከመከራው ለምትተርፈው ትግራይ ምን መአት እንደሚያመጣባት መገመት አያዳግትም፡፡
ትህነግ ሀገር ወራለች፤ ሀገር ወግታለች፡፡ የደገፏትን ሃያላን መንግስታት ንብረት ዘርፋለች፡፡ ቤተ እምነት አውድማለች፡፡ ከምድሩም ከሰማዪም መንግስት ግጥሚያ ውስጥ የገባው የሽፍታ ቡድን መቃብሩ አፋፍ ቆሞም ቢያንስ ወገኔ ያለውን ህዝብ ለመታደግ አልፈለገም፤ አልሞከርም፡፡ በጦርነት የሚያተርፈው ሁሉን ካጣሁ ሁሉም ይጥፋ ባይነት ውጤቱ በተለየ መልኩ በትግራዋይ ላይ መክፋት ጀምሯል፡፡ እዚያ ያለው ረሃብ፣ ችግር ስደትና መከራ ላይ ጦርነት ካልታከለ ባይነቱ ስቃዮን አብሶታል፡፡ ዓለም እውነተኛውን ጁንታ መተዋወቅ ጀምሯል፡፡ ቀጥሎ የሚሆነው ግልጽ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፡፡