Connect with us

 እልህና እብሪት የወጠራቸው ወያኔና ሸኔ የእጃቸውን እያገኙ ነው !! 

እልህና እብሪት የወጠራቸው ወያኔና ሸኔ የእጃቸውን እያገኙ ነው !!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

 እልህና እብሪት የወጠራቸው ወያኔና ሸኔ የእጃቸውን እያገኙ ነው !! 

 እልህና እብሪት የወጠራቸው ወያኔና ሸኔ የእጃቸውን እያገኙ ነው !! 

 (ገለታ ገ/ወልድ-  ድሬቲዩብ ) 

 በአገራችን ከብዙ ውጣ ውረድና መስዋዕትነት በኃላ ለውጥ መምጣት ቢጀምርም ፅንፈኞች እንቅፋት ለመፍጠር የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ነው ፡፡ በተለይ የትግራይና የኦሮሞን ህዝብ ነፃ በማውጣት ስም እያወናበዱ ያሉት አሸባሪዎቹ ህወሀትና ሸኔ የአገር ነቀርሳ የህዝብም እዳ መሆናቸው በተግባራቸው ይበልጠ ተጋልጧል ፡፡በብዙሃኑ ህዝብና በመንግስት በሽብርተኝት ተፈርጀው እየተቀጠቀጡ የሚገኙትም ለዚሁ ነው ፡፡ 

 ያለፈው ዘመን በደላቸው አንሷቸው ፣ ካለፉት ሶስት የለውጥ አመታት ወዲህ አገራችን  የጀመረችውን  ተስፋ እያጠወለጉ ካሉት ቀዳሚ እንቅፋቶች ዋነኞቹ የህወሀት ጁንታና የኦነግ ሸኔ ሃይሎች ናቸው ፡፡ በተለይ ወያኔ ግልፅ በሆነ የአገር ክህደት የመንግስትን ህጋዊ ተቋማት ቅቡልነት ክዶ፣ ጀግናው የመከላከያ ሃይላችንን በይፋ ወግቶና አፈራርሶ አገረ መንግስቱን ለመናድ የደፈረ ፣ በቂም በቀል ዘረፋና ህዝብ መበደል ፖለቲካዊ ትርፍ አገኛለሁ ብሎ የተነሳ ከንቱ ሃይል ነው ፡፡ 

ሸኔ ደግሞ የዚሁ እኩይ ሀሳብ ተጋሪና አገር አፍራሽ ወንበዴ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት ሲያሳድደው ከነበረውና ወገኖቹን ሲባለ ከከረመው ፅንፈኛ ሃይል  ጋር ሽርክና ፈጥሮ የስልጣን ፍርፋሬ ለማግኘት የሚቋምጥ አሸባሪ ነው ፡፡ ካለምንም ጥርጥር ግን እነኝህ አውዳሚና ከንቱ ሃይሎች አገሩን በሚውደው መላው ህዝብና ጀግናው ሰራዊታችን ይደመሰሳሉ ፡፡ ደግሞም የእጃቸውን እያገኙ ነው!!

ህወሀትና ሸኔ ያልተነቃባች መስሏቸው  ህዝብን ከህዝብ እያጋጩ ፣  በደቦና በመንጋ ፍርድ እየተመሩ ፣ በሴራና በተንኮል እየተነዱ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ጥፋት አድርሰዋል ፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃንን ገድለዋል ፣የተፈናቀሉና ሀብት ንብትረታቸውን ያጡ ወገኖችም ትንሽ አይደሉም ፡፡ ይህን ሁሉ ነውርና ግፍ ሲፈፅሙ አይቶ እንዳላያ ሲያልፍ የነበረው መንግስት በትእግስት የሚለወጥ ነገር ይኖራል ብሎ ነበር፡፡ ሁሉም ሳይሆን ቀረና ሙሉ ጦርነት ተለኩሷል ፣ መፍትሄው ሳይዘናጉ መለብለብና አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ጠላትን ማጠናቀቅ ብቻ ነው ፡፡ ወንበዴውን ከነጭፍራው!!

  እነዚህ ሁለት ሃይሎችና መሰሎቻቸው አገሪቱ  አሳድራ የነበረውን ተስፋ እየጠወለጉ ፣ በየአካባቢው ሞት ፣ መፈናቀልና እንግልት  እንዲባባስ አድርገዋል ፡፡ የእምነት ተቋማት፣ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ መዋቅሮች ውድመት ፣ የባንኮች ዘረፋ ፣” እምቢ አልጠየቅም! ” ባይነት እየተዘወተሩ የመጡትም በነዚህ ነውረኛ ሃይሎች ከንቱ መንገድ ነው ፡፡ እንዲህ ያፈነገጠ አጉራዘለልን ደግሞ፣ ለሌላውም በሚስተምር ደረጃ በመረጠው መንገድ ማንበረከክ ካልተቻለ መፍትሄ መመኘት ሞኝነት ነው!!

 በተለይ ጁንታው በትግራይ ህዝብ ላይ እሳት ጭሮ የፈፀመው ግፍና በደል አንሶት ፣ ከወራት ወዲህ ወደአማራና አፋር ክልሎች ለዘረፋና ውድመት ከዘመተ በኃላ በመቶ የሚቆጠሩ ንፁሃን አልቀዋል ፡፡ ሴቶች ተደፍረዋል ፡፡ እጅግ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው የአገር ሀብት ተዘርፏል ፣ ወድሟል ፡፡ ይህን ሌባና ከንቱ ሃይል አሸንፎና አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ከመፋረድ ባነሰ በምን ለማስተማር ይቻላል !!

 መግደርደር አያስፈልግም፡፡ አሁን አገር ምንም ያህል በለውጥ ውስጥ ብትሆንም የህግ የበላይነት የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ላይ ነች ፡፡ 

በተለይ ከህወሀት አሸባሪ ቡድን ውስጥ የወጣው ጁንታና ኦነግ ሸኔ የተባሉ የታጠቁ ሃይሎች በለኮሱት ጦርነት አገር እያናጉ ነው፡፡ እነዚህ ከእንስሳ የማይሻሉ ከንቱዎች የለኮሱት በህዝብ ላይ ያነጣጣረ ግፍና መከራ ካልተቀለበሰ ፣ አንደአገርም መቀጠል የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረስ ይመጣል ፡፡ ስለዚህ ትግሉ ጠላትን እስከማንኮታኮት መግፋት ያለበት ነው!!

 ጁንታውና የኦነግ ፅንፈኞች ከተፈጠሩበት ጊዜ ጀምረው እስከአሁን እስከሚያጣጥሩበት ዘመን ድረስ ትውልዱን የሰበከውት ልዩነትና መነጣጠልን ብቻ ነበር ፡፡ ቂምና ቁርሾን ፣ፀብና ጥላቻንም ሲጭኑ በመኖራቸው ፣እንሆ ቀኑ ሲደርስ ህዝቡን እርስበርስ ወደማባለት ዳርገውታል ፡፡ ይህም ህዝቡ በብሄር ፣በሃይማኖትና መሰል ልነቶች እየተፋጠጠ ፣የእነርሱን የስልጣንና የአገዛዝ ዘመን ለማራዘም ቀደም ሲል የታለመው ሴራ አካል ነበር ፡፡ ይህን ነውረኝነት ተፋልሞ አለማሸነፍ ነው ትልቁ ውርደት !! 

 በአጠቃላይ  የፅንፈኛ ፖለቲከኞቹ ህወሀት/ሸኔና አጋሮቻቸው  ግብና  አላማ በቀዳሚነት አገሪቱን ሰላምና አንድነት የለሽ ፣እርስበርስ የምትባላና የተዳከመች ማድረግ ነው ፡፡ ከዚያም በደቀቁ ጎረቤት አገሮች እንደምንመለከተዉ በጥቂት አጉራ ዘለሎች ፍጭት፣አገር አተረማምሶ  ፍርፋሪ ለሚያገኙበት የውጭ ጠላት የደቀቀች ምድር ማስረከብ ፡፡ ይህ ደግሞ መላው አገር ወዳድ ዜጎች እያሉ ተግባራዊ ሊሆን ከቶ አይችልም ፡፡ እንዳውምእልህና እብሪት የወጠራቸው  አሸባሪዎች ፈጥነው የእጃቸውን የሚገኙ ወሳኝ ምእራፍ እውን ይሆናል፡፡  ኦሮማይ !! 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top