Connect with us

ኢትዮጵያውያን አስመጪዎች 637 ተሽከርካሪዎች ወደአገር ውስጥ ማስገባት ባለመቻላችን ለኪሳራ ተዳረግን አሉ

ኢትዮጵያውያን አስመጪዎች 637 ተሽከርካሪዎች ወደአገር ውስጥ ማስገባት ባለመቻላችን ለኪሳራ ተዳረግን አሉ
ድሬቲዩብ ሪፖርተር

ኢኮኖሚ

ኢትዮጵያውያን አስመጪዎች 637 ተሽከርካሪዎች ወደአገር ውስጥ ማስገባት ባለመቻላችን ለኪሳራ ተዳረግን አሉ

ኢትዮጵያውያን አስመጪዎች 637 ተሽከርካሪዎች ወደአገር ውስጥ ማስገባት ባለመቻላችን ለኪሳራ ተዳረግን አሉ

(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

አስመጪዎች ያስገቧቸው በድምሩ 637 ተሽከርካሪዎች ባገለገሉ ተሸከርካሪዎችላይ ከተጣለው  የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ በጉምሩክ ቅጥር ግቢ እና በወደብ ላይ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቆሙ መደረጉ ለከፍተኛ ኪሳራ እና ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ተዳረገን አሉ።

ኢትዮ ተሽከርካሪዎች አስመጪ ባለቤቶች ማህበር በዛሬው ዕለት በጊዜ ባርና ሬስቶራንት አዳራሽ በሰጠው መግለጫ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ወደአገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ሆነ የገቡት ባለመለቀቃቸው አስመጪዎች ለከፍተኛ ወጪ ከመዳረጋቸውም በላይ መንግስትም ከታክስና ቀረጥ ማግኘት የሚገባው ከፍተኛ ገቢ ማጣቱን የማህበሩ አመራሮች በመግለጫቸው ጠቅሰዋል፡፡

የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ መሐመድ አመዴ፣ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አሥራት ደምለው ዝርዝር ሁኔታውን ለጋዜጠኞች አስረድተዋል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1186/2012 ባወጣው አዋጅ መሰረት ከውጭ አገራት በሚገቡ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲጣል መወሰኑ እና አስመጪዎች የገዟቸው ተሽከርካሪዎች በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ማለትም አስከ ነሐሴ 6 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እንዲያስገቡ የጊዜ ገደብ መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡

የማህበሩ አባላት የሆኑ አስመጪዎች መንግስት ያወጣውን አዋጅ በማክበር የተሰጠው የጊዜ ገደብ ከማብቃቱ በፊት ተሽከርካሪዎቻቸውን ለማስገበት ጥረት ማድረግ በጀመሩበት ወቅት ከተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ባጋጠሟቸው የተለያዩ እንቅፋቶች ሳቢያ በተሰጠው ጊዜ ተሽከርካሪዎቹን ለማስገባት አልቻሉም ብለዋል፡፡ 

ይህንንም ሲያብራሩም በኮቪድ ምክንያት በአንዳንድ ሀገራት መግባትና መውጣት በማገዳቸው፣ የአየርና የመርከብ እንዲሁም የወደብ አገልገሎቶች በመቋረጣቸው እንዲሁም አባላቱ በአካል ሄደው  የሻጭ ድርጅቶችን ወይንም አቅራቢ ድርጅቶች በፍጥነት እንዲጭኑ በማድረግ ተሽከርካሪዎቻቸውን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ማስገባት እንዳይችሉ እንቅፋት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ 

ይህም በመሆኑ ማህበሩ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የባንክ ፈቃድ (ባንክ ፐርሚት) ያገኙ አስመጪዎች ተጨማሪ የመሸጋገሪያ ጊዜ እንዲሰጣቸውና ተሽከርካሪዎቻቸውን ማስገባት እንዲችሉ ለገንዘብ ሚኒስቴር፣ ለጉምሩክ ኮሚሽን ተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያስገቡም መፍትሄ ለመስጠት አዋጁ መሻሻል እንዳለበት በተነገራቸው መሰረት ተደጋጋሚ አቤቱታ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የገቢ፣ የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮምቴ ቢያቀርቡም ተገቢው ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ አስረድተዋለ። በዚህም ምክያት አስመጪዎቹም በቢሊዮኖች ለሚቆጠር ገንዘብ ኪሳራ፣ አላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየተዳረጉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

አስመጪዎቹ ከአቅም በላይ በገጠማቸው ችግር ምክንያት  ወደሀገር ውስጥ ያስገቧቸው በጉምሩክ ባለስልጣን ቅጥር ግቢ ውስጥ ከዘጠኝ ወራት እስከ አንድ ዓመት የቆዩ 328 ያህል መኪኖች እንዲሁም አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው ወደአገር ውስጥ ሊገቡ ዝግጁ የነበሩና በጅቡቲ ወደብ ላይ የሚገኙ 309  መኪኖች ወደአገር ውስጥ ማስገባት አልተቻለም፡፡ 

እነዚህ መኪኖች ወደአገር ውስጥ መግባት ባመቻላቸው ሆነ የገቡት ባለመለቀቃቸው አስመጪዎች ለከፍተኛ ወጪ ከመዳረጋቸውም በላይ መንግስትም ከታክስና ቀረጥ ማግኘት የሚገባው ከፍተኛ ገቢ አጥቷል፡፡

አቶ መሐመድ አመዴ አያይዘውም በችግሩ ምክንያት አስመጪዎችና ቤተሰቦቻቸው ሕልውና ከመጥፋቱ በፊት መንግሥት መፍትሔ ሊሰጠን ይገባል በማለት ተማፅነዋል።

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top