Connect with us

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዛሬም መቀለዱን ቀጥሏል

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዛሬም መቀለዱን ቀጥሏል
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዛሬም መቀለዱን ቀጥሏል

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዛሬም መቀለዱን ቀጥሏል

(በፍቃዱ አባይ)

የቶኪዮ ኦሎምፒክን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በሸራተን አዲስ ሆቴል ድግስ ደግሷል። ኦሎምፒክ ኮሚቴው በላከው መጥሪያ መሰረት ከየፌዴሬሽኑ አምስት 5 ተወካዮች እንዲገኙ ጋብዟል። ነገር ግን አሁን ባገኘሁት መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮሮችን ጨምሮ የበርካታ ፌዴሬሽኖች ተወካዮች  በዝግጅቱ እስካሁን አልተገኙም።

ሱፍ ለብሶ መገኘትን ግዴታ ባደረገው ጥሪ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ጥሪ ለዝግጅት ድምቀት የሚሆኑ እንግዶችን በብዛት ጠርቷል። ነገሩ ታስቦበት የተደረገ ሲሆን አሁንም ድጋፍ አለኝ የሚል መልእክት ለማስተላለፍ የፈለገ ይመስላል ።ቀሪው ለሚዲያ ፍጆታ እንዲሆን ታስቦበት ነው።

ለስልጠናና እና ሌሎች የስፖርት ልማቶች መዋል የነበረበት የመንግሥት እና የህዝብ ገንዘብ አሁንም ውጤት ለሌለው ኦሎምፒክ አሼሼ ገዳሜ እየዋለ ነው። ለነገሩ የማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ባልተለመደ መንገድ ሸራተን አዲስ የተደረገውም በምክንያት ነው። ለብሽሽሽቅ!!!!!ብሽሽቁ ከማን ጋር እንደሆነም የሚያውቅ ያውቀዋል።

ሙሉ መረጃውን ከአዳራሽ መልስ ነገ እናየዋለን። ነገር ግን አሁንም እየታዘብን ነው።

ኦሎምፒክ ኮሚቴው ኢትዮጵያ ውስጥ ባይሆን ኖሮ ምን ይጠብቀው እንደነበር መቼም ግልጽ ነው።

ለቀጣይ ኦሎምፒክ ሌላ ዙር ንትርክ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የቀለዱ ሁሉ ባሉበት እንዳወዛገቡን ይቀጥላሉ ማለት ነው።

ስልጣናቸውን ለግል ስብዕናቸው ግንባታ እያዋሉ ያሉ የስፖርት ኃላፊዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ዛሬም በግሌ እጠይቃለሁ ።

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ስንል በሁሉም መስክ መሆን አለበት።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top