Connect with us

ሴራችሁ ለUN ባይበቃም፤ ይሄ እንባ ግን ራማ ደርሷል፡፡ የዘራችሁትን ታጭዳላችሁ!!

ሴራችሁ ለUN ባይበቃም፤ ይሄ እንባ ግን ራማ ደርሷል፡፡ የዘራችሁትን ታጭዳላችሁ!!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ሴራችሁ ለUN ባይበቃም፤ ይሄ እንባ ግን ራማ ደርሷል፡፡ የዘራችሁትን ታጭዳላችሁ!!

ሴራችሁ ለUN ባይበቃም፤ ይሄ እንባ ግን ራማ ደርሷል፡፡ የዘራችሁትን ታጭዳላችሁ!!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

ንጹህ የት እና እንዴት እንደሚገደል አለም አይቶ እንዳላየ ሆኗል፡፡ ከጦርነት ውጪ ከተማ ላይ ሲቪል ዜጋ በሚኖርበት ቀዬና ቤት የተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ቤተሰብ ጨርሷል፡፡ ቤታቸው የተቀመጡ ህጻናት ሞተዋል፤ አካላቸው ተቆርጧል፡፡ የሚያሳዝነው የዘመቻው ስም ግን ጦርነት ነው፡፡

የትህነግን ወረራ ጦርነት በሚል ክብር መጥራት ጸያፍ ነው፡፡ ቡሃቃ ለመሸከም ነፍስን አጥፍቶ ቤት አቃጥሎ ከተማ አውድሞ መፈርጠጥ ነው፡፡ በንጹሃንና ጦርነቱ ላይ በሌሉበት ሰዎች ነፍስ መፍረድ ነው፡፡

የትህነግ ተደጋጋሚ ሴራ አጀንዳዋ የጸጥታው ምክር ቤት አጀንዳ ለመሆን እንኳን እንዲበቃ አላገዛትም፤ ከእናት ሀገራቸው በዘረፉት ገንዘብ ነጭና ቅጥረኛ ገዝተው መረጃ በማዛባት የሚከፍሉትን መስዋዕትነት እሚበላው ላጣው ወገናቸው ቢቸሩት መልካም ነበር ያም አልሆነም፡፡

ይሄ ሁሉ ሴራና ሸፍጥ ሩቅ ላይጓዝ ለዘለዓለም ይቀበራል፡፡ የተባበሩት መንግስታት በተባበረው ክንዳችን እና በሀቀኛ እውነታችን ነገሩን ሲረዳ እንደ ቻይና አብሮን ይቆማል፤ እንደሩሲያ መገፋታችንን ያምናል፡፡ ያኔ ሴራና ድራማው ሁሉ አንገት በመድፋት ይጠናቀቃል፤

ግን ይሄ የንጹሃን እንባ ዝም አይልም፡፡ እንደ አቤል ደም ይጣራል፡፡ ቤታቸው ተቀምጠው በከባድ መሳሪያ የተደበደቡና ህይወታቸውን ያጡ፤ ከብቶቻቸው በጥይት ያለቁባቸው፡፡ የቀዬያቸው የልማት ተቋም ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ዓይናችን እያየ አንተወውም በሚል የወደሙትን ግፍ ፈጣሪ ይቆጥራል፡፡

የዘራችሁትን ታጭዳላችሁ፡፡ ይህ ግፍ ሌላ ሳይሆን ፈጣሪ ይበቀለዋል፡፡ ቤቱ ቁጭ ባለበት እናቱን ስላጣው ህጻን እንባና ጩኸት ፈጣሪ ዝም እንደማይል እናምናለን፤ እኛ በሰማይ ያለን መንግሥት በተዘረፈ ዶላር የማይሸነገል ወይም ኢትዮጵያ እንድትፈርስ የማይመኝ እውነተኛ ነው፡፡

የነጻነት ትግላችሁ ግብ እህቶቻችን ጭን ውስጥ መግባት መሆኑን አሳይታችሁናል፡፡ መንደሮችን ማራቆት፣ ጎተራ መመዝበር፣ የቤት እንስሳትን መጨረስ፣ ከ1983 በኋላ የተረፈን ጀነሬተር እንደ ታማሚ በአልጋ ይዞ መስገር እንደሆነ አይተናል፡፡ እኛ ካየነው በላይ የሆነውን ደግሞ ፈጣሪ አይቷል፡፡

በቴሌቨዥናችሁ መስኮት ወጥታችሁ በደስታ ተቀብሎናል የምትሉትን አርሶ አደር ለስንት አመት የሚሆነው የጥላቻ ስንቅን እንደሰጣችሁት ሳታውቁ ቀርታችሁ አይደለም፡፡ እዳውን እናንተ ወይም ልጆቻችሁ አይከፍሉም፤ ደጋፊዎቻችሁም ዶላር ይወረውራሉ እንጂ ሌላ መከራ የለባችሁም፡፡ ነጻ እናውጣህ እያላችሁ በየቀኑ ወደ ከፋ ባርነት የከተታችሁት፤ የሌላን ካልበላን በሚል ጥላቻና ቁጭት የራሱን እንዳይበላ ያደረጋችሁት ትግራዋይ መከራውን ይሸከመው በሚል ገፍታችሁበታል፡፡

ዛሬም ውሸት፤ ዛሬም ሀሰት እየተረካችሁ በጥላቻ የሰከረ ትውልድ ከፊት በማስቀደም ጉሮሯችሁ ለተነጠቀው ውስኪ ቁጭት አንድ ትውልድ እሳት ስትማግሩ እውነት ይሰነብታል እንጂ ይወጣል፡፡ ያኔ የስንቱን ደጋፊያችሁ ልብ ሰብራችሁት እንደምትቀሩ አንጠራጠርም፡፡ ዛሬ ታውሮ ሆ ያለው ነገ ህይወቱ ሰቀቀንና ለቅሶ ይሆናል፡፡ በነውር የከበረም የተከበረም የለም፡፡

አሁን የውሸታችሁ ጸሐይ ደርቃለች፡፡ በድርቅናችሁ ጨለማ እድላችሁን ለመሞከር እንደ አውሬ ያገኛችሁትን ማጥፋታችሁን ቀጥላችኋል፡፡ ሩቅ መንገድ የማይሄደው ጭካኔ ወደ አፎቱ እየገባ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ከምንም በላይ በፈጣሪ እናምናለንና፤

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top