Connect with us

በኮቪድ-19  የሶስተኛው ዙር ማዕበል እየጀመረ ነው

ጤና ሚኒስቴር በኮቪድ-19 የሶስተኛው ዙር ማዕበል እየጀመረ ነው አለ
ጤና ሚኒስቴር

ዜና

በኮቪድ-19  የሶስተኛው ዙር ማዕበል እየጀመረ ነው

ጤና ሚኒስቴር በኮቪድ-19  የሶስተኛው ዙር ማዕበል እየጀመረ ነው አለ

.~  ከጥቂት ወራት በፊት ሁለት እና ሶስት በመቶ የነበረው የስርጭት ምጣኔ በአሁኑ ሰዓት በአማካይ አስራ ሁለት (12 %) በመቶ ደርሷል፣

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና ክትባት ዙሪያ በትላንትናው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በባለፈው ሳምንት ብቻ 5547 ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት ሁለት እና ሶስት በመቶ የነበረው የስርጭት ምጣኔ በአሁኑ ሰዓት በአማካይ አስራ ሁለት (12 %) በመቶ ደርሷል፡፡ በየቀኑ ወደ ጽኑ ህሙማን ማዕከላትም የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ሲሆን እስከ ትላንትt ድረስ 510 ሰዎች በጽኑ ታመዋል፡፡ 

በባለፈው ሳምንት ብቻ 66 ሰዎች በወረርሽኙ የሞቱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም በቀን በአማካይ 9 (ዘጠይ) ሰዎች እየሞቱ እንደሚገኙ ዶ/ር ሊያ ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ ያለው ቁጥራዊ መረጃዎችና ሁኔታዎች የሚያሳዩት የሶስተኛው ዙር ማዕበል (3rd wave) በሀገራችን እየጀመረ ስለመሆኑ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ ማህበረሰቡ የሚጠበቅበትን መሰረታዊ የመከላከልያ መንገዶችን አጠናክሮ ከዚህ በበፊቱ ከነበርው በበለጠ የማይተገብር ከሆነ ነገሮች እየከፉ ሊመጡ እንደሚችሉ ሳይንሳዊ ትንበያዎች ያሳያሉ ብለዋል፡፡  በመሆኑም መሰረታዊ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በተጨማሪ ክትባቱን መከተብ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

እስከ አሁን እንደ ሀገር ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን ለማህበረሰቡ መሰጠት ተችሏል ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ አያይዘውም በአዲስ አበባ ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ፣ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ሆኖ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው እና በስራቸው ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም በክልሎች ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ፣ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ሆኖ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው እና በስራቸው ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተከተቡ እንደሚገኙና የሚመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍሎችም ወደ ጤና ተቋም እየሄዱ እንዲከተቡ ሚኒስትሯ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አሳስበዋል፡፡

ማህበረሰቡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር ከዚህ በፊት ያደርገው ከነበረው በበለጠና በተጠናከረ ሁኔታ አካላዊ ርቀትን በ 2 ሜትር መጠበቅ፣ ማስክን ሁልጊዜና በአግባቡ ከማድረግ ባለፈ የእጅ ንፅህናን በተገቢው መንገድ መጠበቅ የሚኖርበት ሲሆን አላስፈላጊ መሰባሰቦችን መቀነስ (በተለይ በዝግ ቦታዎች ላይ የሚደረጉትን)፤ እንዲሁም ምልክቶች ሲታዩም በአፋጣኝ እራስን በማግለል የባለሙያ ምክር መጠየቅ ይገባል ያሉት ሚኒስተሯ ከዚህ በተጨማሪ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንዲያግዝም በስራ ላይ የነበረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ቁጥር 30/2013 ማሻሻያ በማድረግ አዲስ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 803/2013) የወጣ ሲሆን በመመሪያው ዙሪያ ለህዝብ ተከታታይ ገለፃ ማድረግና የህግ ማስከበር ስራው  እንደሚጠናከር የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡(ጤና ሚኒስቴር)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top