Connect with us

የብሔራዊ ፓርኮችና ዱር እንስሳት መጠለያዎች በ2014 በጀት ዓመት ጠንካራ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚሰሩ ተገለጸ  

የብሔራዊ ፓርኮችና ዱር እንስሳት መጠለያዎች ልማትን ዘላቂ ለማድረግ በ2014 በጀት ዓመት ጠንካራ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚሰሩ ተገለጸ
በድሬቲዩብ ሪፖርተር

ዜና

የብሔራዊ ፓርኮችና ዱር እንስሳት መጠለያዎች በ2014 በጀት ዓመት ጠንካራ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚሰሩ ተገለጸ  

የብሔራዊ ፓርኮችና ዱር እንስሳት መጠለያዎች ልማትን ዘላቂ ለማድረግ በ2014 በጀት ዓመት ጠንካራ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚሰሩ ተገለጸ  

(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮችንና የዱር እንስሳት መጠለያዎችን ለማልማት በ2014 በጀት አመት ጠንካራ ቅንጅታዊ ስራዎች እንደሚሰሩ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላቱ ጋር በመሆን የ2013 ዓ.ም. በጀት አመት አፈጻጸምን የሚገመግምና የ2014 ዕቅድ ላይ የሚመክር ጉባኤ በአዳማ ከተማ ማካሄዱን ቀጥሏል፡፡

ትናንት ነሐሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀመረው ጉባኤ ላይ የአካባቢ ደን እና አየር ንብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፣ የባህል ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ዘርፍ ዴኤታ ክብርት ወይዘሮ ቡዜና አልቀድር፣ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የሥራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የየክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሥራ ሃላፊዎች፣ የፌዴራልና ክልል ብሔራዊ ፓርክ ዋርደኖችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡   

ጉባኤው በትናንትና ውሎው የ2013 ዓ.ም. የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አድምጦ የተወያየ ሲሆን የ2014 የሥራ ዘመን ላይም መክሯል፡፡ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ከባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ጋር በጋራ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትም በጉባኤው በአመቱ የሰሩትን ተግባር በሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በተለይም gef 6 በኦሞ፣ ጨበራ ጩርጩራ፣ ማጎ፣ ባቢሌና ቃፍታ በዝኆን ጥበቃ ላይ የሰራቸውን ስራዎች፣ በተመሳሳይ አፍሪካ ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን በስሜን ተራሮች፣ ፍራንክፈርት ዙኦሎጂካል ሶሳይቲ ደግሞ በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሰሯቸውን ሥራዎች በተመለከተ ለጉባኤው አቅርበዋል፡፡

PHE በሰንቀሌ ቆርኪዎች መጠለያ ያከናወናቸውን የመዳረሻ ልማት ስራዎችና በKWF,JIZ ድጋፍም እየተሰሩ ያሉ የአጋርነት ሥራዎች የቀረቡበት ነው፡፡

የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ 2014 በጀት አመት በተመሳሳይ መልኩ በከፍተኛ ቅንጅት የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን በተሻለ ለማልማት እንደሚሰራና ገልጸው በእቅድ ትስስርም በኩል ተናቦ ለመስራት የሚደረገው ጥረት ትኩረት እንደሚሰጠው ገልጸዋል፡፡

የህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት አባላቱም ቢሆን የተፈጥሮ ጥበቃና የብሔራዊ ፓርኮቻችን ጉዳይ አሁንም ትኩረትንና ቅንጅትን የሚፈልግ መሆኑን ገልጸው በተለይም በዚህ መልኩ አጋር አካላትና ባለድርሻዎች ሪፖርታቸውን አቅርበው ውይይት መደረጉና አሳታፊ መሆኑ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች ከሀገራችን የተፈጥሮ ቱሪዝም መዳረሻነት በሚልቅ መልኩ ለኢትዮጵያ ሥነ-ምህዳር ያላቸውን ጠቀሜታ አጉልቶ በማሳየት በኩል አሁንም ውስንነቶች እንዳሉና እንደ ሀገር የጋራ መግባባቱ ከፍ ማለት ያለበት ጥብቅ ቦታዎቹ የመጩው ትውልድ ህልውና መሆናቸው ላይ እንደሆነ በጉባኤው ተጠቁሟል፡፡ ጉባኤው ዛሬም የሚቀጥል መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዜናው ጋር ተያይዞ የተጠቀምናቸው ምስሎች ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘናቸው ናቸው፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top