Connect with us

ከሰብል ምርቶች እና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ወደ 88 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

ከሰብል ምርቶች እና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ወደ 88 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ
ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

ኢኮኖሚ

ከሰብል ምርቶች እና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ወደ 88 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

ከሰብል ምርቶች እና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ወደ 88 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

~ የጫት አፈፃፀም የተሻለ ሆኗል፣

በ2014 በጀት ዓመት የሐምሌ ወር የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ክትትልና ድጋፍ ከሚደረግባቸው የወጪ ምርቶች መካከል የሰብል ምርቶች እና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ በገቢ 81 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቀዶ 88 (108%) ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማሳካት ተችሏል፡፡ 

የቅባት እህሎች 103.25%፣ ጫት 143.17%፣ የጥራጥሬ ሰብሎች 84.80%፣ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን 49.50%፣ ባህር ዛፍ 196.40% እና የብርዕና አገዳ ሰብሎች 68.72% እንዲሁም የቁም እንስሳት 24.46% እንደቅደምተከተላቸው የዕቅድ አፈፃፀም በመቶኛ አሳክተዋል፡፡

በተመሳሳይ ወደ ወጪ ከተላኩት የሰብል ምርቶች በመጠን የቅባት እህሎች 67.36%፣ የጥራጥሬ ሰብሎች 72.87%፣ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን 47.89%፣ ጫት 150.23%፣ ባህር ዛፍ 91.47% እና የብርዕና አገዳ ሰብሎች 225.92% እንዲሁም የቁም እንስሳት 93.75%  የዕቅድ አፈፃፀም አስመዝግበዋል፡፡

በወሩ የሰሊጥ (1,177.69 ቶን) እና የጥራጥሬ ምርቶች (3,938.15 ቶን) ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማቅረብ መቻሉ የኤክስፖርት እቅድ አፈፃፀምን እና የኮንትራት ምዝገባዎችን እንዲሻሻል አድርጓል፡፡

ሰሊጥ እና የጥራጥሬ ምርቶች 13,022 ቶን ምርት ኮንትራት እንዲገባ እና ወደ ዉጪ እንዲልክ በመደረጉ ምክንያት በወሩ የተያዘዉን እቅድ አፈፃፀም በመጠን እና በዋጋ እንዲሻሻል አድርጎታል፡፡ 

ለላኪ ድርጅቶች በተደረገዉ ክትትልና ድጋፍ ላኪዎች በአነስተኛ መጠን ተይዞ የነበረዉን ምርት ኮንትራት እንዲገቡ እና ወደ ዉጪ ገበያ እንዲያቀርቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሲሆን ይህም በላኪዎች እጅ ያለው ምርት በወቅቱ 10,290 ቶን ምርት ተሟልቶ እንዲላክ በመደረጉ 13.45 ሚሊዮን አሜሪካን ዶላር ገቢ እንዲገኝ ከፍተኛ አስቷፅኦ ማድረግ ተችሏል፡፡

545 ቶን የሰሊጥ ምርቶች እና 256 ቶን የማሾ ምርት ይባክን የነበረዉን ምርት በማዳን ምርቱ ወደ ዉጪ እንዲላክ በመደረጉ 1.635 ሚሊዮን አሜሪካን ዶላር ገቢ እንዲገኝ አስችሏል፡፡ 

በወሩ 31,831 ቶን የሰሊጥ እና የጥራጥሬ ምርቶችን ወደ ዉጪ በመላኩ ምክንያት በወሩ 36.823 ሚለዮን አሜሪካን ዶላር ገቢ እንዲገኝ አስችሏል፡፡

( ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top