Connect with us

አፍጋንን በቁጥር

#ካሣ_አንበሳው

ነፃ ሃሳብ

አፍጋንን በቁጥር

አፍጋንን በቁጥር

የአፍጋኒስታን የ20 ዓመት ታሪክ በቁጥር ምን ይመስላል? ለአመክሮና ለተዘክሮ ይሆን ዘንድ እነሆ:-

9/11 (2001 እኤአ) – የሽብርተኞች ጥቃትን ተከትሎ ጆርጅ ቡሽ Oct 7, 2001 አፍጋኒስታን ውስጥ ወታደራዊ ዘመቻ አስጀመረ፣

2014 (እኤአ) – ባራክ ኦባማ ጦርነቱ በይፍ እንደተጠናቀቀ አሳወቀ፣ “በድል ተጠናቋል” ነበር ያለው፣

19 – አሜሪካ በታሪኳ እረጅም ሁኖ የተመዘገበውን ጦርነት ለ19 ዓመታት አካሄደች፣

4 – አራት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች (ቡሽ፣ ኦባማ፣ ትራምፕና ባይደን) ከጦርነቱ ጋር ተነካክተዋል፣

800,000 – 20 ዓመት በሚጠጋው ወታደታዊ ዘመቻ ከ800,000 የአሜሪካ ወታደሮች ተሳትፈውበታል፣

2,352 – አሜሪካ ለቃ እስከወጣችበት ቀን ድረስ 2,352 የአሜሪካ ወታደሮች በሸማቂው ታሊባን ተገድለዋል፣

20,000 – ከ20,000 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች ቁስለኛ ሁነዋል፣

66,000 – በአሜሪካ ሞግዚትነት የተቋቋመው የአፍጋን መንግስት 66,000 ወታደሮች (የራሱን ዜጎች) ገብሯል፣ ሙት!

47,245 – በጦርነቱ የሞቱ ንፁሐን ዜጎች 47, 245 ደርሷል፣

51 – በዚህ ጦርነት ውስጥ 51 ሀገራት ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርገዋል፣ በኔቶ ስም መሆኑ ነው፣

1,144 – ከላይ የተጠቀሱት 51 የኔቶ አባል ሀገራት 1,144 ሰራዊታቸን ገብረዋል፣

441 – ህይወታቸውን ያጡ የእርዳታ ሰጪ ድርጅት ሰራተኞች ቁጥር 441 ነው፣

75 – ጦርነቱ የበላቸው ጋዜጠኞችና የሚዲያ ሰራተኞች ቁጥር 75 ደርሷል፣

51,191 – የአሜሪካን የሞግዚት አስተዳደርን የተቃወሙ 51,191 ንፁሐን ዜጎች ደመ-ከልብ ሁነዋል፣

2,261,000,000,000 – አሜሪካ በዚህ ጦርነት ያወጣችሁ ከ2 ትሪሊየን $ በላይ መሆኑ ተመዝግቧል፣

145,000,000,000 – ለጦርነቱ በቀጥታ ከወጣው በተጨማሪ ከ146 ቢሊየን $ በላይ አፍጋኒስትንን መልሶ ለመገንባት አውጥተናል ይላሉ፣ “ቀልዱን ተይ” አለ ጥላሁን ገሠሠ

300,000 – አሜሪካ ደረጃ አንድ ስልጠና ሰጥቼ ዘመን ያፈራው መሳሪያ አስታጥቂያቸዋለሁ ያላቸው የአፍጋን ወታደሮች ቁጥር 300,000 ናቸው፣ እንደ ባይደን ገለፃ ይህ የሰለጠነ እና የታጠቀ ሰራዊት ከአብዛኞው የኔቶ አባል ሀገራት የተሻለ ነው፣ በአስር ቀን ውስጥ ድምጥማጡ እንደጠፋ አስታውሱ፣

2,500,000 – በጦርነቱ ምክንያት ስደት የገቡ፣ ሀገራቸውን የለቀቁ፣ የተባበሩት መንግስታት የሚያውቃቸው የአፍጋን ስደተኜች ቁጥር ከ2,500,000 በላይ እንደሆነ ተመልክቷል፣

10 – የአሜሪካ መንግስት ነቅሎ ሲወጣ ታሊባን ካቡል ለመድረስ የፈጀበት ቀን 10 ቀን ብቻ ነው።

  1. #ካሣ_አንበሳው

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top