Connect with us

በሙስና እና በኢኮኖሚ ወንጀሎች ብር 162 ነጥብ 7 ሚልየን የሚገመት ሃብት ተመለሰ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

ዜና

በሙስና እና በኢኮኖሚ ወንጀሎች ብር 162 ነጥብ 7 ሚልየን የሚገመት ሃብት ተመለሰ

በሙስና እና በኢኮኖሚ ወንጀሎች ብር 162 ነጥብ 7 ሚልየን የሚገመት ሃብት ተመለሰ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በ2013 በጀት አመት ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሃብት ወደ መንግስትና ሕዝብ እንዲመለስ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በ2013 በጀት አመት በወንጀል ፍሬ የተገኝን ሀብት ከማስመለስ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሃብት ወደ መንግስትና ሕዝብ እንዲመለስ ማድረጉን በተቋሙ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት  አቶ አለምአንተ አግደው ገለጹ፡፡ 

በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄነራል በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ  ሥር  በቅርቡ ተደራጅቶ በዋናነት  በአገር ኢኮኖሚና ደህንነት ላይ የሚፈጸሙ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ከባባድ ወንጀሎችን በአግባቡ ለመከላከል በአጥፊዎች ላይ ከሚጣለዉ ከእስር እና ከገንዘብ ቅጣት በተጨማሪ በወንጀል ያገኙትን እና ወንጀል ለመስራት የዋለን ፤ እንዲሁም በሕዝብና መንግስት ላይ የደረሰን ጉዳት  ለማካካስ  ሃብቱን በምርመራ ለይቶና በአግባቦ ይዞ በማቆዬት ሀብቱን ማስመለስ አይነተኛ የወንጀል መከላከል ዘዴ መሆኑን መነሻ በማድረግ፤ የሃብት ክትትል፣ ምርመራና ማስመለስ ሥራ የሚያከናዉን መሆኑን ዳይሬክተር ጀነራሉ ገልጸው፤ በ2013 በጀት ዓመትም  2,162,175,071.00 ብር የሚገመት ሃብት ለሕዝብና መንግስት ገቢ የሆነ ሲሆን 1,369,187,672 ብር ደግሞ ለሕዝብና መንግስት ገቢ ለማድረግ በተለያዬ ደረጃ በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተናግራዋል፡፡

ከዕግድ ጋር በተያያዘም መጠኑ 5,763,316,448 የሆነ ብር የወንጀል ፍሬ እና በወንጀል ለደረሰ ጉዳት ማካካሻ የሚሆን ሃብት በፍ/ቤት እንዲታድ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የተለያዬ መጠን ያለዉ ገንዘብን ጨምሮ፣ ብዛት ያላቸዉ ሕንጻዎች እና የተለያዩ ንብረቶችም  ለወንጀል መፈጸሚያ እንዳይዉሉ  ለመከላከል ሲባል ከተጠርጣሪዎች እጅ ወጠዉ በሦሰተኛ ወገን እንዲተዳደሩ መደረጉንም አቶ አለምአንተ ያነሱ ሲሆን ከአገር የሸሸ ሃብትን ለማስመለስም ከተለያዩ አገራት መንግስታትና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ 

በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ በአይነት ገቢ የተደረጉ ንብረቶችን ጨምሮ በሙስና እና በሌሎች የተደራጁ የኢኮኖሚ ወንጀሎች የተመዘበረ ሃብት በድምሩ ብር 162,715,071.00 በሃብት ማስመለስ ዳይክቶሬት ጄነራል አማካኝነት ወደ ሕዝብና መንግስት እንዲመለስ የተደረገ ሲሆን ከተመለሰዉ ገንዘብ ዉስጥ 68‚949‚567.52 ብር ሕወሃት በተባለዉ አሸባሪ ድርጅት ስም የተገኘ እና በሕግ አግባብ ወደ ምርጫ ቦርድ ገቢ የተደረገ ነዉ፡፡

በተጨማሪም ግምታቸዉ 2 ቢሊየን ብር የሆነ የትራንስ ኢትዮጵያ 179 የደረቅና ፈሳሽ ጭነት ከባድ ተሽከርካሪዎችን በፍ/ቤት የሕግ ትብብር ጥያቄ  ለጅቡቲ መንግስት በማቅረብ ማስመለስ ተችሏል ሲሉ አቶ አለምአንተ አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ዳይሬክተር ጀነራሉ በህገ-ወጥ መንገድ የተመዘበሩ እና የወንጀል ተግባር ለመፈጸም ጥቅም ላይ የዋሉትን ሀብቶች በማስመለስና በማሳገድ ሂደት መረጃ እና ጥቆማ በመስጠት ትብብር ላደረጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡(ፌ/ጠ/ዐቃቤ ህግ)

 

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top