Connect with us

 አፈርስ ብለው የገነቧት !

አፈርስ ብለው የገነቧት !
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

 አፈርስ ብለው የገነቧት !

 አፈርስ ብለው የገነቧት !

(እስክንድር ከበደ~ ድሬቲዩብ)

አንድ አባት ተመስጦ የውጭ መጽሄት ያነባል፡፡ መጽሄቱ በጥናት የተደገፉ ጥልቅ ትንታኔዎች በተመስጦ ተገርሞ ያነባል፡፡ ይህ አባት በተመስጦ ሲያነብ የአምስት አመት ልጁ ትረብሸዋለች፡፡ አርፋ እንድትቀመጥ ደጋግሞ ቢነግራትም ልትሰማው አለፈለገችም፡፡ አባት አንድ መላ መጣለት፡፡ከሚያነበው መጽሄት የመጨረሻ ገጽ ላይ የአለም ካርታ የተሳለበት ውስብስብ ምስል የያዘ ገጽ በትናንሹ ቆራርጦ ለልጅ ሰጣት፡፡

“ምን ላድርገው አለችው?” ልጅቷ 

“እነዚህ ቀርጥራጭ ወረቀቶችን በመገጣጠም በገጹ ላይ የነበረውን የአለም ካርታ ምስል እንደነበረ አድርገሽ አምጪልኝ ” አለ አባት 

ልጅቷ ቁርጥራጭ ወረቀቶቹን ወደ ጓዳ ይዛ ገባች፡፡አባት የቀን ሙሉ ስራ እንደሰጣት እርግጠኛ ነበር፡፡በገጹ ለይ የሚታየውን ካርታ እስከ ውስብስብ ተራሮቹ እና የድንበር መስመሮቹ ሳይዛነፉ እንደነበረ ገጣጥማ ለመመለስ አንድ ቀን ወይም ከዛ በላይ እንደሚፈጅባት አባት ገምቷል፡፡ እሱ ለልጁ በሰጠው ከባድ ስራ ተደስቶ ወደ ንባቡ ተመለሰ፡፡ልጅቷ ግን ከጥቂተ ደቂቃ በኃላ ተመልሳ መጣች፡፡

“አቃተሽ አይደል ?” አላት

“በጭራሽ ገጣጠምኩት …” አለች ልጅቷ

በእርግጥም ምስሉን ገጣጥማ ካርታውን እንደነበረ ሰርታው መምጣቷ አባቷን አስገረመው ።ጀርባው የአንድ ሴትዮ ምስል ነበር፡፡ ከገጹ ጀርባ የሚታየውን የሴትየዋን ምስል ስገጣጥመው ከፊት ያለው የአለም ካርታ ልክ እንደነበረ መጣልኝ…” አለችው ትንሿ ልጁ፡፡ አባትዬ በጣም ተደስቶ አቅፎ ሳማት፡፡አንድን ችግርን ለመፍታት ግልባጭ ገጹን መመልከት አስፈላጊ መሆኑን አስተማረችው ፡፡

“እንዴት በቀላሉ ሰራሽው ?”

“ከፊት ለፊት ያለው የአለም ካርታ ሳየው ከባድ ሆነብኝ …ከጀርባው የአንድ ሰው ምስል ነበር፡፡ ከገጹ ጀርባ የሚታየኘውን ሴትዮ ምስል ስገጣጥመው ከፊት ያለው የአለም ካርታ ልክ እንደነበረ መጣልኝ…” አለችው ትንሿ ልጁ፡፡ አባትዬው በጣም ተደስቶ አቅፎ ሳማት፡፡አንድን ችግርን ለመፍታት ግልባጭ ገጹን መመልከት አስፈላጊ መሆኑን አስተማረችው ፡።

 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የቀድሞ ኢታማዦር ሹም ሌተና ጀነራል ጻድቃን ገ/ተንሳይ  ከህግ ማስከበር ዘመቻው  በፊት  ከኢትዮፎረም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደተናገሩት በኢትዮኤርትራ ጦርነት  ከመጀመሩ በፊት  የኤርትራ ሰራዊት 150ሺህና የኢትዮጵያ ሰራዊት ደግሞ 54 ሺህ  እንደነበር አብራርተዋል፡፡ ከቀድሞ  ኢታማዦር ሹም የተነገረ  መረጃ  በመሆኑ ተቀብለን እንፈትሸው፡፡  ይህ  መረጃ እንደሚሳየው የኤርትራ ሰራዊት ከኢትዮጵያው አቻው በሶስት እጥፍ  ያህል  ይበልጥ ነበር፡፡ ጀነራሉ በዚሁ ቃለምልልሳቸው ወረራው የተከሰተው  ኤርትራ  ይህንን ግምት ውስጥ አስገብታ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ 

የሚገርመው የኤርትራና የኢትዮጵያ መሪዎች አዲስ  ቅርርብ  የትግራይ ህዝብን ለማንበርከክ እንደሆነ የሚናገሩት ጀነራሉ፤ የባድመ ወረራን የቀለበሰው አብዛኛዎቹ አዛዦች የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውንና  የኔ ህዝብ  የሚሉት  የወታደራዊ ባህል ያለው በመሆኑ ብቻውን ኤርትራን ገጥሞ እንደሚሸንፍ በትእቢት ይናገራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት ስትገባ 54ሺህ ወታደሮቿን በምንያህል ብዛትና ፍጥነት እንዳሳደገች እንዲሁም በዛ ደምአፋሳሽ ጦርነት ከሁለቱ ወገኖች ምንያህል እልቂት እንደደረሰ ይዘሉታል፡፡ 

በሀገራችን  ይህንኑ ጦርነት  ተከትሎ  የሀገሪቱ 80 በመቶ  ሰራዊትና የጦር መሳሪያዎች አቅም  በሰሜን እዝ  ይገኝ እንደነበር ተደጋግሞ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ የክልሉ ልዩ ኃይል ፖሊስና ሚኒሻ እንዲሁም በሰራዊቱ ውስጥ የነበሩ የአካባቢው ተወላጅ ወታደሮችና ጡረተኛ የጦር መኮንኖች ተቀናጅተው  በሰሜን እዝ ላይ የከፈቱት ድንገተኛ ጥቃት  ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይሎች በአማራና በአፋር ልዩ ኃይሎች በመታገዝ  በከፈተው መጠነ ሰፊ የማጥቃት እርምጃዎች  ከሁለቱም ወገን በውል ያልተገለጸ  የሰው ኃይል ሙትና ቁስለኛ የሆነበት ብሎም የህዝብ መገልገያዎችና  የጦር መሳሪያዎች የወደሙበት  የሀገርን ህልውና የፈተነ ጦርነት ነው፡፡ 

በዚህ የእርስበእርስ ጦርነት ከሁለቱም ወገኖች ”ደምስሰናል ” ወይም ”ማርከናል”  ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ የህግ ማስከበር ዘመቻው  የጦር ጄቶችና ድሮኖች የተሳተፉበት መሆኑ ብቻ የጦርነቱ አስከፊነትና ደምአፋሳሽ  እንደሆነ መገመት  አይከብድም፡፡ 

 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  መከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከገባ በኋላ  አንድ ሁለት ጊዜ  በአደባባይ ንግግራቸው ወጣቶች በፍቃደኝነት መከላከያን በመቀላቀል በኩል  መቀዛቀዝ መኖሩን ጠቁመው ነበር፡፡ ባለፉት  ሶስት አስርት አመታት የሁሉም ክልሎች ወጣቶች  የመከላከያ ሰራዊት እንዲቀላቀሉ በየአመቱ  የሚደረግ ጥረት እምብዛም ሲሆን፤ ሆንብሎ መስፈርቶቹን ከፍ በማድረግና በልዩ ልዩ ምክንያቶች  በመደርደር የማግለል ሁኔታዎች እንደነበሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ያጤኑት አይመስልም ነበር፡፡

 ባለፉት ጥቂት አመታት ክልሎች ልዩ ኃይሎችን መልምለው በገፍ የማሰልጠን ስራዎች ሲያከናውኑ እንደስጋት መታየታቸው አልቀረም፡፡ በአንዳንድ ክልሎች አዲስ ምልምሎች፣የቀድሞ ወታደሮችና ልምድ ያላቸውን አዛዦች በመቅጠር  በፉክክር መልክ ማሰልጠንና ማስመረቅ የፖለቲካ አካሄዱ ዘውግ ዘመም በመሆኑ መፈራቱ አልቀረም፡፡ በሱማሌ ልዩ ኃይል ድጋፍና ሄጎ የተሰኙ ወጣቶች ተሳትፎ  በክልሉ በተከሰተው ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውና ንብረት መውደሙ  እንደ አንድ ምክንያት ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡

 በኋላ በትግራይ ክልልም ባለፉት ሶስት አመታት  በጡረታ የተገለሉ ፣ በሰራዊቱ እያገለገሉ ያሉ  የመደበኛ ጦሩ አባላት፣ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላትና ሚኒሻዎች በሰሜን እዝ ላይ የወሰዱት  ”መብረቃዊ” እርምጃ  የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት  ሶስት ምእራፎችን አስተናግዷል፡፡ የመጀመሪያው የደንብ ልብስ የለበሰ ተዋጊ ጋር መፋለም፣ ሁለተኛው ምእራፍ በቡድን  ደፈጣ የሚያካሂድ ተዋጊና ሶስተኛው ደግሞ በህዝቡ ውስጥ ገብቶ  በሰላማዊ ዜጎችን ሰብአዊ ጋሻ አድርጎ የሚወጋ ”ህዝባዊ ጦርነት”  ይጠቀሳሉ፡፡

ይህንን ”የህልውና ዘመቻ ”  የክልሎች ልዩ ኃይሎች ወደ አፋርና አማራ አጋርነታቸውንና አንድነትን በሚያሳይ መልኩ ሀገርን ከመበታተን ለመከላከል መዝመታቸው ፤ በሀገሪቱ እንደተዳከመ የሚቆጠረውን የኢትዮጵያዊ አንድነት መንፈስ እንዲያንሰራራ አደረገው፡፡ 

 ጦሩ  ከመቀሌ ከወጣ በኋላ ደግሞ አማጺያኑ  በአፋርና በአማራ  ”በሰርጎ ገብ” ደረጃ እና በፕሮፖጋንዳ የከፈቱት መጠነ ሰፊ ጦርነት  በቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል  ሰፊ ማህበራዊ ንቅናቄ እንዲፈጠር ብሎም ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ አያሌ ወጣቶች ወደ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ለመውሰድ በአስር ሺዎች ወደ  ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች መግባታቸው ለጠላትም ሆነ ለወዳጅ ትልቅ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል፡፡

 ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክልል የሀገራቸውን ሉአላዊነት ለማስከበር የሄዱ የተለያዩ ልዩ ሀይሎችና በወታደራዊ ስልጠና እየተሳተፉ ያሉ አያሌ  ፍቃደኛ ወጣቶችን   መፈጠራቸው  ፊት ለፊት ከሚታየው ተልኮ ይልቅ ከጀርባው ያለው ምንድነው ብሎ መፈለግ ያስፈልጋል። ከተበታተነው የሀገር ምስል ጀርባ ታላቋ ኢትዮጵያን መገጣጠምና በወጣቶቹ ዘንድ  እያተመ መጥቷል፡፡ 

በዚህ አጋጣሚ አሁን የሚሰለጥኑት ወጣቶች ከሰሜኑ የሀገራችን ጦርነት ባሻገር እዚህ  ወስብስብ ቀውስ ውስጥ ሀገሪቱን የዶሏትን የውጭ ጠላቶች በብቃት የሚመክት ዘመናዊ ሰራዊት የማጠናከር ከፍ ያለ ግብ መያዙን መገመት አይከብድም፡፡ አፈርስ ብለው  የገነቡት አንድነታችንን መሆኑን ማጤን ይጠይቃል፡፡ ይህቺ የማትሰበረዋ ኢትዮጵያ ናት፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top