Connect with us

 የጁንታው አደገኛ የጦር ስህተቶችና መዘዛቸው !!

የጁንታው አደገኛ የጦር ስህተቶችና መዘዛቸው !!
Ethiopian press agency

ነፃ ሃሳብ

 የጁንታው አደገኛ የጦር ስህተቶችና መዘዛቸው !!

 የጁንታው አደገኛ የጦር ስህተቶችና መዘዛቸው !!

( ገለታ ገ/ወልድ- ድሬቲዩብ )      

አገሪቱን በግንባር ቀደምነት፣ የትግራይ ክልልንም በብቸኝነት ለ30 አመታት ገደማ የመራው ህወሀት/ወያኔ፣ አሁን የሽምቅ ተዋጊና ግብረ ሽበራ ውስጥ የገባ ሽፍታ ሆኗል ፡፡ ወደዚህ ህገወጥ ተግባር የገባው ተገፍቶና ተጨቆኖ ቢሆን በታዘነለት ፣ ይልቅንም በጉልበትም ጨፍልቄ ቢሆን ስልጣን ይዤ በፈለገኝ አኳሆን አገር ካልመራሁ ፣ ትፍረስ ትበተን በሚል እኩይ አላማ ተነሳስቶ መሆኑ ብዙዎችን በማሳዘን ላይ ይገኛል ፡፡

  በዚህ ፅሁፍም አሸባሪው ህወሀት ጦርነት በመለኮሱ በአገር ላይ በተለይ በትግራይ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳትና ግፍ በወፍ በረር ለመጠቃቀስ ይሞከራል ፡፡

ህወሀት አገር በመምራት ታሪኩ ራሱ ጭምር የገነባውን የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ  ፣ባደራጃቸው የውስጥ ምንደኞችና ታጣቂዎቹ ያጠቃ ጁንታ ነው ፡፡መግደል ብቻ ሳይሆን ፣በተሸከርካሪ መጨፍለቅና ገደል መክተትን የመሰለ ወራዳ ድርጊት ፈፅሟል ፡፡ የሴቶችን ጡት ሳይቀር ቆርጧል ፡፡ እሱ ሳያንሰው የማረካቸውን ሃላፊነት በጎደለው መንገድ አዋርዷል፣ መዘባባቸ አድርጓል ፡፡

 በተጨባጭ በጦርነቱ ሂደት እየታዬ እንዳለው በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ህፃናትና ታዳጊዎች  ወደትምህርት ቤት ሊሰማሩ ሲገባ ፣ ህውሀት  ወደጦርነት ረመጥ እንዲማገዱ እያደረገ ነው ፡፡ ሰሞኑን በሁሉም ግንባሮች ለሞት ፣ቁስለኝነትና ምርኮ እየተጋለጡ ያሉት በአብዛኛው ከ16 አመት በታች የሆኑ ናቸው ፡፡ ይህ ደግሞ አለም አቀፍ ህግንም የጠሳ ድርጊት ነው፡፡

አብዛኛው የትግራይ ህዝብ የህወሀትን የጥፋት መንገድ ወዶም ሆኖ ተገዶ እንደሚደግፍ የታወቀ ነው ፡፡ ( እዚህ ላይ ምንም መሽኮርመም አያስፈልግም ) ከዚያ አልፎ ግን በአሁኑ ሰአት ህወሀት ተዋጊዎችን እየመለመለ ያለው አስገድዶና የእርዳታ እህልን በመከልከል ጭምር በህዝብ ላይ ተፅኖ በመፍጠር ነው ፡፡ ይህ ነውሩም ቢሆን ፍፁም ከሰበአዊነት ያፈነገጠ የሽብር ድርጊት የሚባል ነው ፡፤

  የትግራይ ህዝብ እንደ ውሃ፣ኤሌክትሪክና ቴሌኮም የመሰሉትን “የቅንጦት” የሚመስሉ የህይዎት ግበአቶችን ይቅርና የእርዳታ እህል ፣ህክም፣ትምህርት ፣ በሰላም ውሎ የማደር… መብቶቹን አንዲገፈፍ ያደረገው አሸባሪው ሃይል ነው፡፡ በክልሉ እንኳንስ የመንግስት መዋቅር ይቅርና መከላከያና የፀጥጣ ሃይል እንዳይኖር በማድረግ፣ የክልሉን ህዝብ ከልማትም ሆነ ብልፅግና በማናጠብ ሌላ 50 አመታት ወደሆላ እንዲመለስ እያደረገውም ይገኛል ፡፡

  ከዚያ አልፎ ህወሀት ግብረ ሽበራና ወረራውን ወደ ጎረቤት ክልሎች በመሳፋት በአፋርና በአማራ ክልል ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል ፡፡ በአፋር ጋላኩማ በተሰኛ ጊዚያዊ መጠለያ ስፍራ ላይ መድፍ ተኮሶ ከ230 በበላይ ሴቶች ፣ህፃናትና አረጋዊያን ፈጅቷል ፡፡ ከወራት በፊት በማይካድራ በጅምላ ያስገደላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ አማራ ተወላጆች አንሰው ፣ በቅርብ ቀናትም በመርሳ፣ ላሊበላ ፣ በጋይንትና አካባቢዎቹ በጥይትና በመርዝ የገዳሏቸው ንፁሃን ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ፡፡

ህወሀት የቋመጠለትን ስልጣን በተሳሳተ ስሌት ለማግኘት በጀመረው የቀን ቅዥት ከአገራችን ህዝቦች ጋር ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት አገረ ኤርትራ ጋር ደም ተቃብቷል ፡፡ ገና ለገና በፈጠረው “ የተከበብኩ “ ስጋት ቀድሞ ወደ አስመራ ሚሳይል ተኩሶ እሳት ጭሯል  ፡፡ የኢትዮ- ኤርትራ የተቀናጀ ጦር ወደ ትግራይ ገብቶ በክልሉ ህዝብ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረገውም ይሄው ሃይል ነው ማለት ይቻላል ፡፡ በዚያ በቀል  በትግራይ ክልል ሺበልባ አካባቢ የሰፈሩ ንጹሃን የኤርትራ ስደተኞችንም ገድለዋል ፡፡

 ህወሀት ተስፋ ቆራጭ በሆነና የባንዳነት ድርጊቱ ከሱዳንና የእጅ አዙሩ የግብፅ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ አገር የወጋ ነው፡፡ ለአብነት ያህል 30 ሺ የሚደርሱ ተፈናቃዮች (በማይካድራ ዘር ማጥፋት የፈፀሙት ጭምር) ፣ቀድመው ሱዳን እንዲገቡ ያደረጎቸው የአላማ ተጋሪዎቻቸው ነበሩ ፡፡ ከካርቱም ወታደራዊ ክንፍ ጋር በፈጠረውት ቁርኝት የሱዳን ጦር ፣ በምእራብ አማራ ወረራ እንዲፈፅም ያደረገውና  እስከአሁንም ድረስ የተቀናጀ ውጊያ እያደረጉ ያለው ፡፡

ጁንታው በራሱ የፈፀመው ግፍና በደል አንሶት ፣ በአብዛኛው ኦሮሚያ (በተለይ በምእራብ ወለጋ ፣ጉጅና ምስራቅ ሐረርጌ) በርካታ ንፁሃንን የገደለ ፣ ሴቶችን የደፈረ ፣ ሀብት ያወደመውን ኦነግ ሸኔን ግብረአበሩ ማድረጉ የጦር ወንጀለንነቱ ማሳያ ነው ፡፡ ምንም እንኳን  መንግስት ሁለቱንም በአሸባሪነት የፈረጃቸው ቢሆንም ፣የሁለቱ ፀረ ሰላም ሃይሎች መቀናጀት የኢትዮጵያ ህዝብ አምርሮ እንዲታገላቸው የሚያደርግ ነው፡፡

በአጠቃላይ ህወሀት የአገራችን ብቻ ሳይሆን ፣ የዘመናችን የአህጉሩ አደገኛ የጦር ወንጀለኛ ነው ፡፡ እነዚህ የጠቃቀስናቸው  ብቻ ሳይሆኑ ነገ ታሪክ የሚያወጣቸው ጥፋቶቹም ዛሬ ለተደናገረው አለም ጭምር ተጨማሪ የወንጀል መረጃዎች እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top