Connect with us

ዜናማ የሚሆነው ኦነግ ሸኔ ከኦሮሞ ጠላት ትህነግ ጋር አብሮ ባይቆም ነበር፤ ሲክድ የኖረውን በመግለጫ አመነው

የካይሮ ረጃጅም እጆች ….
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ዜናማ የሚሆነው ኦነግ ሸኔ ከኦሮሞ ጠላት ትህነግ ጋር አብሮ ባይቆም ነበር፤ ሲክድ የኖረውን በመግለጫ አመነው

ዜናማ የሚሆነው ኦነግ ሸኔ ከኦሮሞ ጠላት ትህነግ ጋር አብሮ ባይቆም ነበር፤ ሲክድ የኖረውን በመግለጫ አመነው

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

አንዳንድ ጊዜ ዜና መሆን የሌለበትንና የምናውቀውን ጉዳይ ለምን እንደ አዲስ ዜና አድርገን እንደምንቀባበለው አልገባኝም፡፡ ኦነግ ሸኔና ትህነግ እናትና ልጅ ብቻ ሳይሆኑ አሁንም ሸኔ የትህነግን ጡት የሚጠባ፣ ትህነግን ኦሮሞ ህዝብ ጫንቃ ላይ ለመጫን ተልኮ ጫካ የገባ ነው ሲባል ኖረ፤ ከዚያም አልፎ በሽብርተኝነት ጭምር ተፈረጀ፤ የደረሰው ኪሳራና ኦነግ ሸኔ የፈጸመው ጥፋት ሁሉ የተላላኪነት ነው ሲባል ከረመ፡፡ ይሄንን ሲክድ ከርሞ በመግለጫ አረጋገጠው፡፡

ይልቁንስ ዜና የሚሆነው ያልነውና ያማነው አልፎም በፓርላማ ጭምር ምለን የተነጋገርነው የኦነግ ሸኔን ትህነግነት የሚያፈርስ ዜና ብንሰማ ነበር፡፡ ለምሳሌ “ኦነግ ሸኔ ከኦሮሞ ህዝብ ጠላት ጋር አብሬ አልቆምም አለ” የሚል፡፡

ኦነግ ሸኔን የኦሮሞ ብልጽግና የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ነው የሚለው ወዶ አይደለም፡፡ ሐሜትና የስልጣን ሽኩቻ እንዳልሆነ ማሳያው የቡድኑ ፍላጎት ነው፡፡ ይህ ቡድን እንኳን ለኦሮሞ ህዝብ ጠላት ለራሱም ገራፊና አኮላሽ ተቀጥሮ የሚሰራ መሆኑን ሲያሳይ ከርሟል፡፡

ከዚህ ቀደም ጄነራል ባጫ ደበሌ በጥቅምቱ ጦርነት ኦሮሚኛ ተናጋሪ ሠራዊት ከህወሃት ጎን ተሰልፎ እንደነበር ይፋ አድርገዋል፡፡ ዛሬ ዜና የሚሆን አዲስ መረጃ የለም፡፡ መንግስት በተጨባጭ በወለጋ ደጋግሞ ይከሰት ከነበረው ጭፍጨፋና በብሔሮች መካከል እንዲነሳ የተፈለገውን እሳት የመለኮስ ዘመቻ ትህነግ ከመቀሌ አስተባብራዋለች ሲል ከሷል፡፡

አማራ ክልልም በተመሳሳይ ወንድማማቾቹ ቅማንትና አማራ በሰላም እንዳይኖሩ ቅጥረኞችን አሰማርታ እያመሰቺኝ ነው ሲል ተደምጧል፡፡ ትግራይ ቴሌቨዥን ለኢሮብና ለኩናማ ያልሰጠውን ሰዓት የቅማንት ነጻ አውጪ ነኝ ለሚል አፍራሽ መድቦ ወንድማማች ሲያጫርስ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ የነበረው ቀውስ ስውር እጅ ትህነግ ነው የሚለው ወቀሳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ የትህነግ አውራዎች ከተደመሰሱና ከታሰሩ በኋላ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ያገኘው ሰላም እና እፎይታ ነው፡፡

ትህነግና ኦነግ ሸኔ አብረው ሰሩ ዜና አይደለም፡፡ ኦነግ ሸኔ ዛሬም ፍላጎቱ ያንን ኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዲያ ያለ መራራ ስቃይ መከራና በደል ያደረሰ ቡድን መልሶ እዚያ ህዝብ ላይ መጫን ነው፡፡ እውነተኛ የኦነግ ታጋዮች የታገሉለትን ዓላማ እንዴት አርቆ መቀመቅ ሊከተው እንደፈለገ ከተግባሩ ከተረዳን ቆይተናል፡፡

ያም ሆኖ ግን ኦነግ ሥርቻ የለውም፤ የኦሮሞ ህዝብ ራሱ የሚታገለው ቡድን ነው፡፡ እንደ ትህነግ ዘርፌ ጉያህ ልግባ ቢል ያ ጠንካራ የገዳ ሥርዓት ናልኝ አይለውም፡፡ ለዚህ ነው ትህነግ ቅጥቅጥ ሸምበቆ ተደግፏል የምንለው፡፡ ጠንካራዋ በትርና ድጋፍ በኢትዮጵያዊነት በእኩልነትና በጋራ መኖር ነበረች፡፡ ያቺን ምርኩዝ ብቻዬን ካልያዝኩ አልፎም ክልነጠኳችሁ ያለ ቡድን አመጽ አንስቶ ሀገር አፈርሳለሁ ብሏል፡፡ ለዚህ ዓላማው ጫካ እየወረደ ቀለበት ያስራል፣ ጋብቻ ይፈጽማል፡፡ 

ትህነግ ወለጋም ሰው ቀጠረች ጎጃም፣ ጎንደርም መለመለ ወሎ ዓላማው ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ለማፈርስ ጥቂት ለሆዳቸው የሚገዙ ሌቦችን ማግኘት ይቻል ይሆናል፡፡ ድፍን ኢትዮጵያ ግን ከዳር ዳር ሀገሩን መታደግ የሚሻና የሚታደግ ነው፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top