Connect with us

“ተፀፅተናል!!”

"ተፀፅተናል!!"
ፌ/ፖሊስ ኮሚሽን

ዜና

“ተፀፅተናል!!”

“ተፀፅተናል!!”

በውጊያ ተሳትፈው የተማረኩ የአሸባሪው የትህነግ ቡድን ታጣቂዎች በፈፀሙት ድርጊት ተፀፀቱ።

ጦርነቱን አዲስ አበባ ላይ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሳለን ብሎ ሀገርን ለመናድ ጦርነት የለኮሰው አሸባሪ የትህነግ ቡድን ዓላማ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣በክልል፣በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽንና በሌሎች የፀጥታ አካላት በተቀናጀ ኦፕሬሽን መክሸፉ ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተካሄደው ውጊያ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሲያሳርፍባቸው የነበረውን ጠንካራ ክንድ መቋቋም አቅቷቸው የተማረኩ ታጣቂዎች የጦር መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደ ህዝብ እንዲቀላቀሉ እድል የተሰጣቸውና በውጊያው የተሸነፉ ሾልከው በድብቅ ወደ ተለያዩ ከተሞችና ቦታዎች ሰርገው በመግባት ለጥፋት ተልዕኮ ሲያሴሩ ከተለያዩ ስፍራዎች የተያዙ ምርኮኞች እንዲሁም የፌዴራል መንግስት የተኩስ አቁም ካደረገ በኋላ የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ለህዝብ ጥቅም ተብሎ የተሰጠውን የእፎይታ ጊዜ አልቀበልም በማለት በአማራ፣በአፋር ክልሎች ላይ በከፈተው ጥቃት በተደረገው ውጊያ የተማረኩ “ ቅድሚያ ለሀገራችን ኢትዮጵያ መስጠት እየቻልን የሽብርተኛውን የህወሃት ቡድን ዓላማ ለማሳካት በትግራይ ክልል በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በደረሰው ጥቃት ተፀፅተናል፣ከጥፋታችንም ተምረናል፣ድርጊቱ አንገታችንን አስደፍቶናል፣ባጠፋነው ጥፋትም ሠራዊቱ ይቅርታ ያድርግልን ” ሲሉ ተማፅነዋል፡፡

ምርኮኞቹ መፀፀታቸውን የገለፁት ሰሞኑን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ የተመራ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊቱና በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥበቃ ሥር የሚገኙ ምርኮኞች ያሉበትን ሁኔታ በጎበኙበት ወቅት ነበር፡፡

የሽብርተኛውን ቡድን እኩይ ዓላማ ተቀብለው በተለያዩ የውጊያ ግንባር ሲሳተፉ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂ ምርኮኞች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከአረብ ሀገራት ተመልሰው ከአሸባሪው የህወሃት ቡድን ጋር ለመቀላቀል እቅድ ይዘው ወደ ግንባር ሲጓዙ  የነበሩ በርካታ ወጣቶች በየግንባሩ በነበሩ በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣በፌዴራል ፖሊስና በክልል ልዩ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

ምርኮኞቹ በጥበቃ ስር ባሉበት ወቅት ከፖሊስ ደብቀው ባስገቧቸው ተንቀሳቃሽ ስልኮች የተለያዩ መረጃዎችን ሲያስተላልፉና ሲቀባበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ፖሊስ የገለፀ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ አሸባሪ ቡድኑ ለጥፋት ተልዕኮ ማስፈፀሚያ የሰጣቸው በርካታ ገንዘብ በእጃቸው ይዘው መገኘታቸውን ረዳት ኢንስፔክተር በረከት ገልፀዋል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ ሀገርን የማፍረስ ዓላማውን አንግቦ አስገድዶአቸው በውጊያው እንዳሰለፋቸው የተናገሩት ምርኮኞቹ የሀገር ደጀን የሆነው የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ሲጠብቁ በነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የተፈፀመው ጥቃት በወንድሞቻችን ላይ እንደተፈፀመ ያህል ነው የሚሰማን ሲሉ በመፀፀት ተናግረዋል፡፡

ከግል ህይወቱ ይልቅ ሀገርን በማስቀደም 27 ዓመታት ሙሉ የሀገራችን ዳር ድንበር ሲጠብቅ የኖረ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት ላይ የተፈፀመው ድርጊት አፀያፊ በመሆኑ  በተፈፀመው ድርጊት ተፀፅተናል ይቅርታ ይደረግልን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሀገር መከላከያ ሰራዊት እንደ አሸባሪው ህወሃት ጁንታ ቡድን ምርኮኞች ለፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ አላደረገም።ይሉቁም የፈፀሙትን ድርጊት ወደ ጎን በመተው ለሰው ልጅ የሚደረገውን ሰብዓዊ አያያዝ ሁሉ እያደረገ እንደሚገኝ ቡድኑ ተመልክቷል።

ይህንን በተመለከተ ምርኮኞቹም ሻዋር ሁለት ጊዜ፣ቁርስ፣ምሳ፣እራት እንዲሁም የመጠጥ ውሃ እናገኛለን፤ምንም የጎደለብን ነገር የለም።ሰብዓዊ መብታችን ባከበረ መልኩ ነው የተያዝነው በማለት እየተደረገላቸው ያለው ሰብዓዊ አያያዝ ገልፀው።ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እጃችንን ስንሰጥ በፍጹም ይሄ ይደረግልናል ብለን አላሰብንም ብለዋል።(ፌ/ፖሊስ ኮሚሽን)

 

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top