Connect with us

ከሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ

ዜና

ከሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ የተሰጠ የአቋም መግለጫ
*******
ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ። የትም፣ መቼም፣በምንም!!

አገራችን ኢትዮጵያ ህልውናዋንና ሉዓላዊነቷን የሚፈታተን አደጋ ገጥሟታል፡፡ አሸባሪው የህወሓት ባንዳ ቡድን አገሪቱን ለማፈራረስና ለመበታተን በሙሉ አቅሙ እየተረባረበ ይገኛል፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ሲመራ በቆየበት በርካታ አመታት የራሱን ስግብግብ ፍላጎት ለማሳካት በየክልሎቹ የሞግዚት አስተዳደር ከመዘርጋቱ ባሻገር
አንዱን የቤት ልጅ ሌላውን የዳር ተመልካች የሚያደርግ የአገዛዝ ስርአት አስፍኖ ፤ በርካታ ህዝቦችን በአገራቸው ጉዳይ ከመወሰን ተገልለው እንዲቆዩ ያደረገ መሆኑ ፀሀይ የሞቀው አገር ያወቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ቡድኑ ይህን የተሳሳተ የፖለቲካ አመለካከት በመያዝ በአገራችን ሰፊ መልከአምድር ላይ የሚኖሩ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ አርብቶ አደር ዜጎች በሀገሪቷ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ውሰጥ ያላቸውን ሚና በመገደብ በዜግነት መብታቸው እንዳይጠቀሙ በማድረግ የራሱን ፍላጎት ሲያራምድ ቆይቶል ፡፡

ከዚህም አልፎ ህገመንግስቱን መሰረት ያላደረገ የፖለቲካ ስርዓትና የሞግዚት አስተዳደር በክልሎች እንዲቀመጡ አድርጎ ለ27 ዓመታት በብሔር ብሔረሰቦች ስም እየማለ የአንድ አገር ህዝቦች እርስ በራሳቸው እንዳይተማመኑና
እንዲጋጩ በማድረግ ለበርካታ ንፁሐን ዜጎች ሞት ፣ መፈናቀልና ንብረት መውደም ምክንያት የሆነ ተቆጥሮ የማያልቅ የግፍ ተግባር ሲፈፅምና ሲያስፈፅም መኖሩም የማይካድ ሀቅ ነው።

በአገራችን ለውጥ ከመጣ በኋላም ለውጡ ይዟቸው የመጣውን የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣ አሳታፊ የፖለቲካ ባህሪና ክልሎች ራሳቸውን በራሳቸው በነፃነት ማስተዳደራቸው ያልተዋጠለት ይህ አሸባሪ ባንዳ ቡድን ለውጡን ለመቀልበስ በማለም አፍራሽ ድርጊቶችን እየፈጸመ ይገኛል።

ስለሆነም የሱማሌ ብልጽግና ፓርቲ አሸባሪው የህውሓት ቡድን የህዝቦችን ወንድማማችነት ለመሸርሸርና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የያዘው ከንቱ ምኞት እንዳይሳካ የህዝባችንን አንድነት በማጠናከርና ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ደጀን በመሆን በንቃትና በትጋት መስራቱን እንደሚቀጥልና ኢትዮጵያን ለማዳን የሚደረገው ትግል የሚጠይቀውን ማንኛውም መስዋዕትነት ለመክፈልም ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ
ነሐሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም
ጅግጅጋ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top