Connect with us

ሰላምን ለማስከበር የአብረን እንቁም ጥሪ

Social media

ነፃ ሃሳብ

ሰላምን ለማስከበር የአብረን እንቁም ጥሪ

ሰላምን ለማስከበር የአብረን እንቁም ጥሪ
( ከአቶ ወርቁ አይተነው)

የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙት ወረራ፣ በሰዉና በቁስ ላይ እያደረሱ ያሉት ዘግናኝ ወንጀል መወገዝ ያለበት ድርጊት ነው። ይህ ድርጊት በተባበበረ ክንዳችን እንዲቆም ሰላም ወዳድ የሆነ ሁሉ ሊሳተፍበት የሚገባ አስቸኳይ ተግባር ነዉ፡፡

ጁንታዉ በሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ላይ በፈፀመዉ ክህደት ሀገራችን መልማት በሚገባት ጊዜ ጦርነትን መምረጡ ሳያንስ በፌደራል መንግስቱ የተወሰደዉን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በአማራ ክልል የሚገኙ ዉስን ወረዳዎችን በመዉረር ዝርፊያ፣ ግድያና ማፈናቀል እየፈፀመ ይገኛል፡፡

  • ህዝብ ከምንግዜዉም በበለጠ ተደራጅቶና ተግባብቶ፣ አቅመ ደካማ ሆኖ መሳሪያ ያለዉም መሳሪያዉን ለወጣቱ በመስጠት ይሄንን አሸባሪ ቡድን ጠራርጎ በማስወጣት ነፃነቱን ማስመለስ ይኖርበታል፡፡ የአማራ ህዝብ በቁመህ ጠብቀኝና ክላሽ እየተዋጋ፥ አሸባሪዉ ሃይል ደግሞ በታንክ፥ በዙ ፥ በሞርታርና ዲሽቃ ንፁህ የአማራ ገበሬዎችን እየጨፈጨፈ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም፡-

1. ሁሉም ወጣት በግንባር በመሰለፍ ወገኑን ከወራሪዉና አዉዳሚዉ ሃይል ጥቃትና ዉርደት እንዲከላከል፤

2. በሃገር ዉስጥና በሀገር ዉጭ የምትኖሩ ሀገር ወዳድ ዜጎች ይህንን ጁንታዉ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለዉን የዘር ማጥፋት በአገኛችሁት አጋጣሚና ሚዲያ ለዓለም እንድታሳዉቁ፤

3. ጁንታዉ በተቆጣጠራቸዉ አካባቢዎች ያላችሁ ወገኖች እየተፈፀመ ያለዉን ጭፍጨፋ ማስረጃ በመያዝ እንድታሳዉቁ፤

4. ከጁንታዉ ጎን የተሰለፋችሁ የትግራይ ወጣቶች ዉስኖች የፖለቲካ ፍላጎታቸዉን ለማርካት በሚዘዉሩት ጦርነት ወንድማማች በሆነዉ የአማራና የትግራይ ህዝብ መካከል ደም ከማፋሰስ በዘለለ ምንም ከማታተርፉበት ጦርነት በመዉጣት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በሰላም እንድትኖሩ፤

5. የአማራ ህዝብ ሆይ አሸባሪዉ ሃይል የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በሚነዛዉ የዉሸት ፕሮፓጋንዳ ሳትሸበር እየተፈፀመብህ ያለዉን የጅምላ ጭፍጨፋ በመመከት ለመጪዉ ትዉልድ በደማቁ የተፃፈ ታሪክና ዘላለማዊ ነፃነት እንድታወርስ፤

6. በዉጭ የምትኖሩ የትግራይ ባለሃብቶች ሆይ ባለፉት ጊዜያት ክፋ ደጉን በጋራ አይተናል፤ ዛሬም በመገዳደልና ሀገር በማፍረስ የሚመጣ ጥቅም ስለሌለ፥ ነገሮች ወደ ሰላም እንዲመጡ የበኩላችሁን ተሳትፎ እንድታደርጉ፤

ጥሪዬን እያስተላለፍኩ ወራሪዉ የትህነግ ታጣቂ በአስቸኳይ ከሰላም ወዳዱ የአማራ ህዝብ ወሰን ለቅቆ እንዲወጣ፤ ይህ ካልሆነም ወጣቱ ተደራጅቶ እንዲጠብቀኝ፤ እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሌትና ቀን በከባድ መሳሪያ ከሚደበደበዉ ህዝብ ጋር በግንባር ፊት ለፊት በመሰለፍ ማንኛዉንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኔን አረጋግጣለሁ፡፡

እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነዉ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

አቶ ወርቁ አይተነዉ

ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top