Connect with us

በግብፅ እና ሱዳን 1959 ላይ በተፈረሙት ስምምነት የግብፅ እና የሱዳን የአባይ ውሃ ድርሻ

Social media

ነፃ ሃሳብ

በግብፅ እና ሱዳን 1959 ላይ በተፈረሙት ስምምነት የግብፅ እና የሱዳን የአባይ ውሃ ድርሻ

በግብፅ እና ሱዳን 1959 ላይ በተፈረሙት ስምምነት የግብፅ የአባይ ውሃ ድርሻ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን የሱዳን የውሃ ድርሻ ደግሞ 18.5 ቢሊዮን ነው፡፡

በዚሁ ዓመት በሁለቱ መካከል በተደረገው ስምምነት ውስጥ በግብፅ ብልጣ ብልጥነት ሰፍረው ሱዳን ድብን አድርጋ የፈረመችላት ገራሚ ገራሚ አንቀጾች አሉ::

ከነዚህ ገራሚ አንቀጾች ውስጥ አንደኛው ግብፅ የውሃ ችግር በገጠማት ጊዜ ሱዳን የግድ ውሃ በብድር መልክ ለግብፅ መስጠት እንዳለባት የሚደነግግ አንቀፅ ሰፍሯል:: ልብ አድርጉ ግብፅ ከሱዳን ውሃ ተበድራ ልትመልስላት::

ሁለተኛው ገራሚ አንቀጽ ግብፅ በሱዳን ውስጥ ባሉ ግድቦች ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ውሃ እንድታከማች የምል ነው::

ሶስተኛው ገራሚ አንቀጽ ሱዳን ካለ ግብፅ ፍቃድና እውቅና ውጭ ከላይኞቹ የተፋሰስ ሀገራት ጋር ምን ዓይነት የሁለትዮሽ ስምምነት ማድረግ አትችልም የምል ነው::

ከዚህ አንቀጽ አንፃር ብቻ ሱዳን ስንት ጊዜ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማድረግ እንፈልጋለን እያለች ስንት ጊዜ ሀሳቧን እንደቀየረች የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው::

እነዚህ ስምምነቶች ሱዳን ወዳ ብቻም አይደለም ተገዳ የሚታከብረው ስምምነቶች ናቸው::

በመሆኑም ከላይ አንደኛና ሁለተኛ ብየ ካስቀምጥኳቸው አንቀጾች ውስጥ በሰፈሩት አስገዳጅ ስምምነቶች የተነሳ ሱዳን በዓመት ከተሰጣት 18.5 ቢልየን ክውቢክ ሜትር ውሃ ውስጥ በየዓመቱ 6 ቢልየን ክውብክ ሜትር ውሃ ለግብፅ እየለቀቀች መቆየቷን እንደነ ፕሮፌሰር ሀሴን ሀሺም ዓይነት የሱዳን ሙሁራን ይናገራሉ::

እቺኛዋ እጅግ እግሯ የተሰረችው ሱዳን ናት እንግዲህ አስገዳጅ ስምምነት ሳይፈረም ውሃ መሙላትም ይሁን ግንባታ ማካሄድ አይቻልም እያለች ኑ አብረን እንታሰር ዓይነት የገደል ማሚቶ ሆና የግብን መሰሪ አካሄድ እየደገፈች የግብፅን ድምፅ የሚታስተጋባው::

ከዚህ አኳያ የግብፅን ብልጣ ብልጥ አካሄድ ቀድሞ በመንቃት አስገዳጅ ስምምነት ውል የእንፈራረም ጥያቄ በማክሸፍ እስከዚህ ድረስ ስላደረሱን ለኢትዮጵያ የአባይ ውሃ ተደራዳሪዎቻችን አድናቆተ የላቀ ነው::

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ለመውጭ ትልድ የሚያስቡ አርቆ አሳቢ ጀግኖች ነበሯት ዛሬም አላት ነገም ይኖራታል:: ኢትዮጵያ ብቻ ለዘለዓለም ትኑር!

#ሁሴን_አብደላ_ሁሴን

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top