Connect with us

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ታድሜ ዋልኩ

ሄኖክ ስዩም

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ታድሜ ዋልኩ

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ታድሜ ዋልኩ

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)
ታሪካዊቷ ከተማ ነኝ፡፡ የሠይፈ አርእድ ስስቱ፣ የነገሥታቱ የዓይን ብሌን፣ የሰመርነሐ ሰገነት፣ የኢየሱስ የታቦር አምባ፣ የጋፋት የጥበብ ምድር፤ ደብረ ታቦር፡፡

እንዲህ ያለ ከተማ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ደረት የሚያስነፋ ትናንት ያለው ነው፡፡ ስድስት መቶ አመት እንዲህ ባለው የመዲናነት ወግ ኖራለች፡፡

ዛሬም የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና ከተማ ናት፡፡ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መገኛ፡፡ ከፍ ያለ የትምህርት ማዕከልነት ብርቋ አይደለም፡፡ እንደውም የዝማሬ መዋስኢቱ ማስመስከሪያ የት ሆኖ፣ የድጓውስ ዩኒቨርሲቲ፣ ተክሌ አቋቋም የት ተቁሞ የት ሊካን፡፡ እንዲህ ባለ ምድር ያለው ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ እንግዳ ሆኜ ታድሜያለሁ፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባል እና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ምክትል ጠቅላይ አቃቢ ህግና የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ እና በርካታ ጥሪ የተረደገላቸው እንግዶች፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ የዕለቱ ሙሽራ ተመራቂዎችና ቤተሰቦቻቸው፤ ደብረ ታቦር ሐምሌ ሃያ አራት ቀን ሁለት ሺህ አስራ ሦስት፡፡

ዩኒቨርሲቲው እነኚህን ሲያስመርቅ ዛሬ ለስምንተኛ ጊዜ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ 2455 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡

ከዛሬ ተመራቂዎች የገረመቺኝ ጀግናዋ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ተማሪዋ የሺሃርግ አበጀ ቅጣው ናት፡፡ ከሁሉም ተማሪዎች ቀዳሚዋ የውጤት ባለቤትና ትጉሃ በላጭ በመሆን የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማቷን ከዕለቱ የክብር እንግዳ ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እጅ ተቀብላለች።

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በዚህ የምረቃ ዘመን አመቱን በጋራ ከእኛ ጋር የሰሩ በሚል እውቅና የሰጣቸው የሂዩማን ብሪጅ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር የክብር ዶ/ር አዳሙ አንለይን ሲሆን በአመቱ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ በመስራት ላከናወኑት ዘርፈ ብዙ ሥራ ልዩ የአጋርነት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በአሜሪካን ሀገር የሚገኘው “Educational Commission For Foreign Medical Graduates (ECFMG)” ባካሄደው ተከታታይ ግምገማ እና ምዘና ሂደት ሲሆን እውቅናው የህክምና ትምህርት ቤቱ ተመራቂ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ በአለም ዙሪያ ተቀባይነት እንዲኖረው ያስችላል፡፡

ይህ ዓለም አቀፍ እውቅና የህክምና ትምህርት ቤቱን ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ በቀጣይም በመስኩ ካሉ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትስስር ለመፍጠር ያግዛል ሲሉ ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ገልጸዋል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የታደምነው እንግዶች የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ተግባር ፈጽመናል፡፡ አረንጓዴው ዩኒቨርሲቲው ውብ ለማድረግ የራሳችንን ችግኞች አፍርተናል፡፡

ከትውልዱ ቀዳሚነትን በርሁ ያደረገው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜም የቲያትር ትምህርት ክፍሉ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ተማሪዎቹ የተማሩባት መዲና ደብረ ታቦር በቴዎድሮስ ራዕይ ነገን ቀድማ ያለመች የሥልጣኔ የጥበብ የእውቀትና የምርምር ቀደምት መዲና ነበረች፡፡ ዛሬም ያንን ራዕይ አስቀጥላለሁ ብሎ የተነሳው ዩኒቨርሲቲ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top